>

የዶክተር አብይ የቱርክ ጉዞን በተመከለተ የውጭ ሚዲያዎች የሰጡት አስተያየት (ሱሌማን አብደላ)

የዶክተር አብይን የቱርክ ጉዞ በተመከለተ የውጭ ሚዲያዎች የሰጡት አስተያየት 

ሱሌማን አብደላ

.


ቱርክያ በአረብኛ’
የጠቅላዩ ጉዞ የሚጠበቅ ነበር። ሀገሪቱ መንግስት አልባ እንድትሆን በመንግስት ላይ ትልቅ ጫና ተደርጎ ነበር። አለም ላይ የሶሪያ የየመን የሮሂንጋ አሰቃቂ ጦርነቶች ተደርገዋል። ሁላቸውም ሆነው የትግራይ ክልልን ያህል አጀንዳ አልሆኑም። የአለም ሚዲያዎች አንድም ቀን ተመሳሳይ አቋም ኖሯቸውም አያውቅም። በተቃራኒው እነዚህ ሚዲያዎች ኢትዮጵያ ላይ ባለው ጦርነት ተመሳሳይ አቋም ይዘው የትግራይን ጦርነት ካፍ ካፉ ላለማቀፉ ማህበረሰብ የሚያስኮመኩምት ነበር። ይህ በአጋጣሚ የተፈጠረ ነገር አይደለም ። እመሬት ላይ ያለው እውነታ ወይም የትግራ ህዝብ መጎዳት አስጨንቋቸውም አይደለም። ከዚህ የበለጡ ትልልቅ የጦርነት ወንጀሎችና ክስተቶች አሉ ። አላማው የሀገሪቱን መንግስት ለማፈራረስ የታሰበ የጋራ ዘመቻ ነበር። በምዕራባዊያን የተገፋው የኢትዮጵያ መንግስት ቱርክን እንደ አንድ ጠንካራ እስትራቴጂካዊ አጋር አድርጋ ኢትዮጵያን በፈለገችው መንገድ እናግዛለን ያሉት የቱርክ መሪ ብቻ ናቸው። እዚህ ላይ አብይ ቱርክ ከመምጣቱ 15 ቀን በፊት ከቱርክ መንግስት ድጋፍ አግኝቷል። ከዛ ቡኋላ ነው የቱርክና የኢትዮጵያ ግንኙነት እንዳዲስ የተፈጠረው።
.
የግብፁ ናይል ኦንላይን
የኢትዮጵያ መንግስት ወደ ቱርክ የሄደበት ጉዳይ ገራሚ ነው። አብይ ሀገሪቱ በጦርነት እየታመሰች ከሱዳን ጋር በድንበር ውዝግብ በገባችበት ሰአት ቱርክን ወዳጅ አድርጎ ድጋፍ ለማግኘት ቱርክ ሄዷል። እንዲሄድ ያደረገው ቱርክ ከግብጽ ጋር ቅሬታ ውስጥ ስላለች በቀጠናው የቱርክን ተፅዕኖ ለማሳደግ አሶቦ ነው። ለዛውም ነው ቱርክ ሮጣ በውሃ ጉዳይ ላይ አብረን ለመስራት ተስማምተናል ብላ መግለጫ የሰጠችው። ውሃውን በተመለከተ ከግብፅ ጋር አብሮ ለመስራት ያልፈገ መንግስት ከቱርክ ጋር አብሮ ለመስራት ስምምነት ላይ ደረሰ። በዚህ አካሄድ ወደፊት ቱርክና ኢትዮጵያ በአረቦች ውሃ ላይ ጦርነት አይከፍቱም አንልም።
.
ተፅዕኖ ፈጣሪው ጋዜጣ ዘ-ጆርዳን ታየምስ
የኢትዮጵያ መንግስት ወደቱርክ ያደረገው ጉዞ ብዙ ነገሮችን ሊቀይር ይችላል። ቱርክ የአለም ትኩረት የሆነውን የናይል መነሻን
መሰረት ያደረገ የኢኮኖሚና የፖለቲካ የወታደራዊ ጉዳዮች ላይ አብራ ለመስራት ከኢትዩጵያ ጋር የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርማለች። ይህ የጋራ ሰምምነት በቀጣይ ኢትዮጵያ ከምዕራባውያን ተፅኖ ለመላቀቅ የሚያስችላት ጥላ መስራት መጀመሯን ይጠቁማል። ሀገሪቱ ከገባችበት ጦርነት ከወጣች የቀጠናውን የኢኮኖሚ የበላይነት ለመረከብ ትንሽ አመት ይወስደባታል ብሏሎ። ለሀገሪቱ ትልቁ ፈተና ሙስና ነው ያለው ዘጆርዳን ታየምስ ከሙስና የፀዳች ኢትዮጵያ ከተፈጠረች አፍሪካ ውስጥ በውሃ ተብቷ ሀብታም የሆነችው አገር የውሃ ወርቋን አውጥታ መጠቀም ከጀመረች ድህነትን ታሪክ የማድረግ ሰፊ እድል አላት ብሏል ዘጆርዳን ታየምስ ጋዜጣ !
Filed in: Amharic