ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ
በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋ ኪራሙ ወረዳ ስኔ ዶሮ ፤ ኩቲ እና ሀሮ በተባሉ ቀበሌዎች በትናንትናው እለት ብቻ ከ60 በላይ ሰዎች በኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች መገደላቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል። መኖሪያ ቤቶችም በእሳት ተያይዘው ወድመዋል ። በሺ የሚቆጠሩ ነዋሪዎች ጥቃቱን ሸሽተው ሀሮ በምትባል የገጠር ከተማ ተጠልለው እንደሚገኙ ነው የሚናገሩት ።
ከአራት ቀን በፊት ስኔ ዶሮ በተባለች ከተማ ሰፍሮ የነበረው የክልሉ ልዩ ኃይል ከአካባቢው መነሳቱን ተከትሎ የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ወደ አካባቢው መግባታቸውን ነዋሪዎቹ ተናግረዋል።
በዚህ ጉዳይ ላይ ምላሽ እንዲሰጡኝ የኦሮሚያ ክልል መንግስት ባለስልጣናት ጋር ደውዬ ስለ ጉዳዩ ጠይቂያቸው ነበር ምላሽ ለመስጠት ፍቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል።