>

የጀነራል አሳምነው ፅጌ ደም ከንቱ አልቀረም! (አቻምየለህ ታምሩ)

የጀነራል አሳምነው ፅጌ ደም ከንቱ አልቀረም!

(አቻምየለህ ታምሩ)

ጀግኖች  የስማዳ  ወጣቶች የአሳምነውን ደም መልሰዋል፤   መኳንት ገ/ህይወት ለህውሀት መረጃ ማቀበሉ በትክክል ስለተደረሰበት ከታሰረበት ጣቢያ አውጥተው እረሽነውታል 
 
ከታች የምትሰሙት የሁለት ሰዎች የስልክ ንግግር በትናንትናው እለት የጎንደር ወጣቶች እርምጃ የወሰዱበት የብአዴን የደኅንነት ሹም የአገር መከላከያ ሠራዊትንና የአማራ ልዩ ኃይልን ወታደራዊ ሚስጥር አንዳችም ሳያስቀር ለፋሽስት ወያኔው አዋጊ ስልክ በመደወል አሳልፎ ሲሰጥ የሚሰማበት የድምጽ ማስረጃ ነው። ሹሙ ለፋሽስት ወያኔው አዋጊ በሚሰጠው ወታደራዊ ሚስጥር ሲናገር እንደሚሰማው የትውልድ አካባቢውን በከባድ መሳሪያ ሊደበድቡ ከትግራይ ለመጡት ወራሪዎች፣ ዘራፊዎችና ዘር አጥፊዎች ያልሰጣቸው ወታደራዊ ሚስጥር የለም። አንድ ሰው ተወልዶ ያደገበትና የኔ የሚለው ቀጠና በወራሪ ጠላት እንዲወድምና ወገኖቹ በጅምላ እንዲፈጁ እንዲህ አይነት ክህደት የሚፈጽመው ምን አይነት ተፈጥሮ ቢኖረው ነው? ማፈርና መሸማቀቅ ሲገባቸው ወጣቶችን ሲያንጓጥጡ ያየናቸው የብአዴን ኮልኮሌዎች የፋሽስት ወያኔው አስተኳሽ ለምን ተነካ ብለው ከጣራው በላይ የጮሁለትና ጥብቅና  የቆሙለት ከሀዲ  እንዲህ አይነት የፋሽስት ወያኔ አስተኳሽና የራሱ ሕዝብና የተወለደበት አካባቢ ደመኛ የነበረ ጠላት ነው።
ስለ ገ/ሒወት መኳንት  ተጨማሪ  መረጃ
ገ/ሒወት መኳንት ለህወሓት መረጃ ሲሰጥ ተይዞ በስማዳ ወረዳ የማጣራት ሥራ እየተሰራበት ነበር። ቤቱ ፍተሻ ሲደረግ ከህወሓት ጋር ግንኙነት የሚያደርግባቸው መገናኛ ሬዲዮ ተገኝቶበታል። በአንድ አካውንት ደብተር 32 ሚሊየን ብር ተገኝቶበታል።
ፖሊስ ሁኔታው ስላጠራጠራቸው የእጅ ስልክ በቴሌ በኩል ማጣሪያ ሲደረግ ከህወሓት አሸባሪ ቡድን ግንኙነት እንደሚያደርግ ሙሉ ለሙሉ መረጃ ፖሊስ እጅ ይገባል። እንዴት እንደሆነ ነገሩ ባልታወቀ ሁኔታ ገ/ሒወት የዛሬ 3 ቀን ከስማዳ ወረዳ ፖሊስ ጣቢያ ያመልጣል።
ገብረሒወት መኳንትን ከስማዳ ወረዳ አምልጦ አንጎት ከሚባል ቦታ ሲደርስ ወጣቱ ከሕግ ጋር በመተባበር ተይዞ እንደገና ወደ እስር ይገባል። ገብረሂወት መኳንትን ለሁለተኛ ጊዜ የማስመለጡ ድራማ  ግን አልተሳካም የማያዳግም እርምጃ ተወስዶበታል ። ገ/ህይወት መኳንንት #የብ/ጀነራል አሳምነው ጽጌን አስክሬን መጎተቱ ይታወቃል። ፎቶ ሰልፊ እየተነሳ በጄነራሉ አስክሬን ተሳልቋል። ገብረሂወት መኳንት ለእዚህ እኩይ ተግባሩ ብአዴን ለመኮነን ገብረሒወት መኳንት የስመዳ ወረዳ ጤና ዋና ሐላፊ ሹመት ሰጥቶታል። የሆነው ሆኖ አሁንም በሌሎች አመራሮች ማጣራቱ ይቀጥላል….”!
Filed in: Amharic