>

የሰሜኑን አገራችን ሁኔታ...!!! (ግርማ ካሳ)

የሰሜኑን አገራችን ሁኔታ…!!!

ግርማ ካሳ

ወያኔዎች ሳይታሰብ ነው ወረራ የፈጸሙት። “ወያኔ ዱቂት ሆናለች ፣ ከዚህ በኋላ ስጋት አትሆንም” ተብሎ ስለተዋሸ፣ የአብይ መግስትm ከትግራይ ክልል ሲወጣ ከባባድ መሳሪያዎችን በሙሉ ጥሎላቸው በመውጣቱ፣ በተለይም የአማራ ማህበረሰብ ራሱን እንዲያደራጅ፣ እንዲያጠናክር፣ እንዲያስታጥቅ ይፈለግ ስላልነበረ፣ ወያኔ በድንገት ጥቃት ስትፈጽም፣ በቀላሉ ሰፊ መሬቶች ለመያዝ ችላለች።
ሆኖም ግን ወያኔ እንዳሰበችው አልሆነላትም። የአፋር ማህበረሰብና የአማራ ማህበረሰብ ራሳቸውን  ለመከላከል ባደረጉት ትንቅንቅ የወያኔን ግስጋሴ መግታት ብቻ ሳይሆን አሁን መልሶ ማጥቃት የተጀመረበት ሁኔታ ነው ያለው።
ኢትዮጵያዊያን ከፍተኛ ግፊት በማድረጋቸውም ፣ አንደኛ በአቶ አገኘው ተሻገር የሚመራው እጅግ በጣም ደካማ የአማራ ክልል መንግስት፣ እነ ጀነራል ተፈራ ማሞ ወደ አማራ ክልል ልዩ ኃይል እንዲመጡ አድርጓል። በሕዝብና በታችኛው የአማራ ብልጽግና አባላት ተገዶ። አብን፣ አዴሃን የመሳሰሉ የተቃዋሚ ፓርቲ አባላትንም ያካተተ አንድ ወጥ አሰራር እንዲዘረጋ ተደርጓል። ከዚህም የተነሳ የአማራ ማህበረሰብ ሳይታሰብ ጥቃት የተፈጸመበት ቢሆንም ፣ ለጊዜው ያሉ ጥቃቅን ልዩነቶችን ወደ ጎን በማድረግ፣ በአንድነት በመንቀሳቀስ እየፈሰሰ ያለውን ደም ቢያንስ ለማስቆም ተችሏል።
የሕዝቡን ጥቅምና ደህንነትን በጭራሽ ከግምት ያላስገባውን፣ የትግራይ ገበሬዎች እንዲያርሱ በሚል፣ የአማራ ገበሬዎችና የአፍር አርብቶ አደሮች እንዲፈናቀሉ ምክንያት የሆነውን፣ የዶር አብይ አህመድ የብልጽግና ፓርቲ የተሳሳተ፣ ጸረ አፋር፣ ጸረ አማራ የፖለቲካ አመራርና የተናጥል የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲሰረዝ፣ ከፍተኛ የሆነ ሕዝባዊ ግፊትና ጫና በፊዴራል መንግስቱ ላይ በመደረጉ፣ የአብይ መንግስት የተናጥል የተኩስ አቁሙን ሰርዞታል። እጆቻቸው የታሰሩ የመከላከያ ሰራዊት አባላትም የአማራና የአማራ ኃይሎችን በመቀላቀል ሕዝቡን የመታደግ ስራዎችን መስራት ጀምረዋል።
ሳይታሰብ ወረራ በመፈጸማቸው ጊዚያዊ ድሎች ቢቀዳጁም ሕወሃቶች የህዝብን ኃይል ማሸነፍ እንደማይችሉ በቅርቡም ወረው ከያዟቸው ቦታዎች ሸሽተው በፍቃዳቸው ወይንም ተገደው እንዲሚወጡም ብዙ ጊዜ ጽፊያለሁ። አሁንም ያንን ነው የምናገረው።
ወያኔዎች ወረር/ጥቃት የፈጸሙት በስድስት ግንባር ነው። በሁለቱ ግንባሮች በወልቃይትና በአፋር ግንባር 100% ተሸንፈዋል ማለት ይቻላል። በተቀሩት አራት ግንባሮች፣ በዋገምራ፣ በጠለምት፣ በጋየንት/ደብረታቦርና በራያ/ወሎ ግንባሮች፣ ግስጋሲያቸውን ማስቆም ብቻ ሳይሆን በመልሶ ማጥቃት ከያዟቸው አንዳንድ ቦታዎች እንዲለቁ እየተደረገም ነው።
ይህ ጦርነት እብዶች የከፈቱት ጦርነት ነው። ወያኔ ይሄን ጦርነት በማድረጓ አምስት ሳንቲም ለራሷም ለትግራይ ሕዝብም የፈየደችው ነገር የለም። የትግራይ ህዝብ የበለጠ ለችግርና ለሰቆቃ እንዲጋለጥ፣ የትግራይ ልጆች እንደ ቅጠል በማያውቁት አካባቢ እንዲረግፉ ከማድረግ ውጭ። ማሸነፍ እንደማይችሉ እያወቁ በጥጋብና በትእቢት ተሞልተው ጦርነት ማወጅ እብደት ነው።
አሁንም የትግራይ ወገኖች፣ የበለጠ ጉዳት ከመምጣቱ በፊት ወረው ከያዟቸው ከሰሜን፣ ደቡብ ጎንደር፣ ጠለምት፣ ራያ፣ ሰሜን ወሎና ዋገምራ እንዲወጡ እጠይቃለሁ።ለራሳቸው ሲሉ።
ሜዳ ላይ ስላለው ሁኔታ፣ በሁሉም ግንባሮች አጠር ያለ ዘገባ እንደሚከተለው አቅርቤላቹሃለሁ፡
 
1) የደብረ ታቦር/ጋየንት ግንባር
በደብረ ታቦር/ጋይንት ግንባር፣ ወያኔዎች ደብረ ታቦርን ለመያዝ ያደረጉት ሙከራ ቀላል አልነበረም። እጅግ በጣም ከፍተኛ የሰው ኃይልና መሳሪያ ይዘው ነበር በደብረታቦር/ጋይንት መስመር የተንቀሳቀሱት። በጉና ተራራ፣ እንደ ደብረ ዘቢጥ፣ ንፋስ መውጫ ባሉ አካባቢዎች ጦርነቱ ሃይለኛ ስለነበረ አንዴ በአንዱ ሌላ ጊዜ በሌላው እጅ የወደቁበት ሁኔታ ነው የነበረው። ወያኔዎች ሲመቱ፣ ተጨማሪ የሰው ኃይል እየላኩ ከባድ ዉጊያ ነበር ሲያደርጉም ነበር፡፡ ኃይል በማጠናከር፡፡
ሆኖም ተጨማሪ ኃይሎች ቢልኩም ወያኔ እንኳን ደብረ ታቦርን ልትይዝ ከሌሎች አካባባቢዎች ለቃ እንድትወጣ እየተደረገ ነው። የሞቱት ሞተው፣ የተማረኩት ተማርከው ብዙዎች ትንሽ ትንሽ ሆነው በተለያዩ አቃጣጫዎች ተበታትነዋል።
ወደ ደብረ ታቦር ጋየንት ግንባር ተጨማሪ ኃይል እንዳያሰማሩ እነ ደብረ ታቦርን ከወልዲያና ከላሊበላ የምታገናኘው የጋሼና ከተማ ከነርሱ እጅ ወጥታለች። ከጋሸና እስከ ንፋስ መውጫ 71 ኪሎሜትር ነው። የመከላከያ ሰራዊት ጋሸናን ዋና ማእከሉ በማድረጉም በጋሸናና በደብረ ታቦር መካከል ያሉ የወያኔ ታጣቂዎች ሙሉ ለሙሉ እንዲቆረጡ ተደርጓል። የደብረ ታቦር/ጋየንት ግንባር በቅርቡ ወያኒዎች 100% ተሸንፈው አካባቢው ሙሉ ለሙሉ ከአሸባሪዎች የጸዳ ይሆናል የሚል ግምት ነው ያለው።
 
2) የራያ/ወሎ ግንባር
በራያ/ወሎ ግንባር በተለይም በነ ወልዲያ አካባቢ ጊዚያዊ ድል ወያኔዎች ቢያገኙም ተረጋግተው መቆየት የቻሉበት ሁኔታ የለም። ለአድፍጦ ጥቃት እየተጋለጡ፣ ወደ ደሴ የሚያደርጉት ግስጋሴ የተገታበት ሁኔት ነው ያለው። ከላይ እንደተጠቀሰው በቅርቡ ይዘዋቸው የነበሩ፣ በጣም ወሳኝ የሆኑ በጋይንትና ወልዲያ መካከል ያሉ እንደ ጋሸና፣ እስታሽ ያሉ ቦታዎች በመከላከያና የአማራ ሰራዊት እጅግ ወድቀውባቸዋል።
ከእስታሽ እስከ ወልዲያ ያለው 77 ኪሎሜትር ብቻ ነው። ከእስታሽ ወደ ወልዲያ በመንቀሳቀስ ፣ ወልዲያ አካባቢ ያለው የወያኔ ጦር ቀለበት ውስጥ መክተት አስቸጋሪ አይደለም የሚሆነው። ከዚህም ስጋት የተነሳ ወያኔዎች ወደነ ሃይቅና ደሴ ዘልቆ ለመሄድ አልደፈሩም።
እንደውም ከወልዲያ አካባቢ ወያኔ በአድፍጦ አጥቂዎች እየተመታች ከወልዲያ በስተደቡብ ካሉት እንደ መርሳ ካሉ ከተሞችም እየለቀቀች እንደሆነ እየሰማን ነው። ወልዲያም ከነርሱ እጅ ወጥታለች የሚልን ዜና አለ።
ወያኔዎች ወልዲያ አካባቢ የመቆየት አቅም ስለሌላቸውም ጦራቸው ከወልዲያ አካባቢ ወደ ሰሜን በማሸሸ ወደ ቆቦ ቢያመሩ ብዙ መገረም የለብንም።
3) የዋገመራ ግንባር
ላሊበላ ምን ላይ እንዳለች ብዙ መረጃ ማግኘት አስቸጋሪ ሆኗል። ምን አልባት ታሪካዊ ቅርስ ያለበት ከተማ እንደመሆኑ፣ ቅርስን ለመጠበቅ በሚል ወታደራዊ እንቅስቃሴ እዚያ አካባቢ ላለማድረግ ታስቦ ይሆናል።
ሆኖም ግን በሌሎች የዋገምራ አካባቢዎች ግን የተለያዩ ጦርነቶች እየተደረጉ ነው። ወያኔ ሰቆጣን ለመቆጣጠር ያደረገችው ተከታታይ ሙከራ አክልተሳካላትም። ከላሊበላ ወጣ ያሉ ወረዳዎች ከወያኔዎች የማጽዳት ስራዎች በስፋት እየተሰሩ እንደሆነ ግን የሚመጡ አንዳንድ መረጃዎች ይጠቁማሉ።
4) የጠለምት ግንባር
በጠለምት ግንባር አሁንም ወያኔ ጠለምትን ጨምሮ በርካታ ከደባርቅ በስተሰሜን ያሉ የሰሜን ጎንደር አካባቢዎች እንደያዘች ነው የሚሰማው፡፡  ሆኖም በዚህ አካባቢ ከፍተኛ ውጊያዎች እየተደረጉ ነው። ብዙ ጊዜ ወያኔ ሽንፈት ያጋጠማት ሲሆን፣ ተጨማሪ የሰው ማእልበል ወታደር እያሰማራች አሁንም በመተንፈስ ላይ ናት። በአጭሩ አሁንም በጠለምት መስመር ዉጊያ እየተደረገ ነው።
5) የወልቃይት ግንባር
በወልቃይት ግንባር ብዙ ዉጊያ የለም። ወያኔ ከ12 ጊዜ በላይ ሙከራ አድርጋለች፤ አስራ ሁለቱንም ጊዜ በመሸነፏ እዚያ አካባቢ ተስፋ የቆረጠች ይመስላል።
7) የአፋር ግንባር
ወያኔ በአፍር ክልል ዘልቃ በመግባት፣ ጭፍራ ከዚያም ሚሌን በመያዝ የአዲስ አበባ ጅቡቲን መስመር መዝጋት ነበር ሃሳቧ። ከዚያም አዲስ አበባ በኢኮኖሚ ለማነቅ፡፡  ጀነራል ጻድቃን ገብረትንሳኤም ይሄንን ነበር የተናገረው። ሆኖም ያ 100% ከሽፎባታል።
የአፋር ክልል ዞን 4 ካሉ 5 ወረዳዎች ወያኔ አራቱን ይዛ ነበር። ሆኖም የአፋር ልዩ ኃይሎችና የመከላከያ አየር ኃይል ባደረጉት ትንቅንቅ ወያኔ ወራ ይዛ ከነበረው የአፋር ክልል ዞን 4 ፣ በአራቱ ወረዳዎች አይቀጡ ቅጣት በመስጠት ተባራለች።
ከዚህ ጽሁፍ ጋር በተያያዘው ካርታ በአረንጓዴ የተከበቡት በወያኔ ስር ያልሆኑ ሲሆኑ፣ በቀይ አሁንም በወያኔ ስር ያሉ ናቸው፡፡ በብርቱካማ ቀለም ያሉት ደግሞ በማን ስር እንደሆኑ ግልጽ መረጃ ማግ ኘት ያልተቻለባቸው ናቸው፡፡ረዳዎች አይቀጡ ቅጣት በመስጠት ተባራለች።
Filed in: Amharic