>
5:26 pm - Friday September 15, 1330

የቀዝቃዛው ጦርነት እያንሰራራ ይሆን ?ምእራባውያን የአፍሪካውን ቀንድ እያጡት ይሆን ? (ደረጀ መላኩ - የሰብዓዊ መብት ተሟጋች)

የቀዝቃዛው ጦርነት እያንሰራራ ይሆን ?ምእራባውያን የአፍሪካውን ቀንድ እያጡት ይሆን ?

ደረጀ መላኩ ( የሰብዓዊ መብት ተሟጋች)

Tilahungesses@gmail.com


“Power had been sent to meet with Dr Abiy to ensure that he would comply with the US State Department’s essentially impossible and illogical demand that the Ethiopian Government cease combat operations against the TPLF.”

[Republished with permission from Defense & Foreign Affairs Special Analysis]

Formerly Defense & Foreign Affairs Daily
Volume XXXIX, No. 39 

እንደ ጎርጎሮሲያኑ አቆጣጠር ነሀሴ 4 ቀን 2021 ምሽት ላይ አዲስ አበባ ከተማን ለቀው ወደ ሀገራቸው የተመለሱት የተባበረችው አሜሪካ አለም አቀፉ ልማት ኤጀንሲ የስራ ሃላፊ የሆኑት ወ/ሮ ሳማንታ ፓወር ደስተኛ አልነበሩም ወይም በተልእኳቸው እርካታ አላገኙም ነበር፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ይዘውት የመጡትን የዋሽንግተን መልእክት በኢትዮጵያ ላይ በከፊልም ቢሆን ገቢራዊ ማድረግ ባለመቸላቸው ይመስለኛል፡፡ ለግዜውም ቢሆን ኢትዮጵያ ላይ ያሰቡትን ለመጫን አልተቻላቸውም ነበር፡፡ ወደፊት የሚሆነውን ግን አብረን የምናየው ይሆናል፡፡ በነገራችን ላይ የሲትዮዋ ወደ ኢትዮጵያ መምጣት ተራ ጉዳይ ወይም ስለ እርዳታ ለመነጋገር የታለመ አልነበረም፡፡ እኚህ ሴት ይዘው የመጡት የተባበረችው አሜሪካን መሪ መልእክት ለማድረስ ነበር፡፡

እኚህ የዚች ሃያል ሀገር ልኡክ የሆኑት የፖለቲካ ሰው ‹‹ በሰብዓዊነት ስም›› ለትግራይ ነጻ አውጪ ድርጅት መተላለፊያ ኮሪደር ስለሚከፈትበት መንገድ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ለመነጋገር ነበር፡፡ ግን የተሳካላቸው አይመስለኝም፡፡ ከመገናኛ ብዙሃን ዘገባ እንደተሰማው ከኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚንሰትር ዶክተር አብይ መሀመድ ጋር ተገናኝተው ለመነጋገር ቢፈልጉም እንዳልሆነላቸው ተሰምቷል፡፡ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ባለስልጣናት መሃከል የተወያዩት ከሰላም እና የጤና ሚንስትሮች ጋር እንደነበር ይነገራል፡፡

ይህ የሚስስ ሳምንታ ውድቀት ብቻ አይመስለኝም፡፡ በአዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲም ክሽፈት ይመስለኛል፡፡ ከዚህ ባሻግር የተባበረችው አሜሪካ ሁነኛ የፖለቲካ ሰው የሆኑት አንቶኒ ብሊንከን የሚራምዱት ግብጽን ያማከለ የውጭ ፖሊሲ የኢትዮጵያን መንግስት ከተባበረችው አሜሪካ ጋር እየለያየው እንደመጣ ማሳየም ነው የሚል የግል አስተያየት አለኝ፡፡

አንደ አንዳንድ የፖለቲካ ተንታኞች ጥናት ውጤት ከሆነ የተባበረችው አሜሪካ በቀዝቃዛው ጦርነት በአነሰ መልኩ በአፍሪካው ቀንድ ያላት ተጽእኖ እየቀነሰ መጥቷል፡፡ ነገር ግን ዛሬ የተባበረችው አሜሪካ ታሪካዊ ጠላታችን ግብጽ ኢትዮጵያ ላይ ለምትሰብቀው ጦር፣ለምትጎነጉነው ሴራ ተባባሪና ደጋፊ ናት፡፡ በአጭሩ የግብጽ አጋርና ደጋፊ ሀገር ስትሆን ከኢትዮጵያ ፍላጎት ደግሞ በተጻራሪው የቆመች ሀገር ስለመሆኗ በገቢርም በነቢብም እያሳየችን ነው፡፡ ከተሳሳትኩ ልታረም ዝግጁ ነኝ፡፡ ግብጾች ለዘመናት ያለቋረጡትን አባይን ከምንጩ የመቆጣጠር አቅድ ገቢራዊ ለማድረግ እንዲችሉ አሜሪካኖቹ በብዙ መልኩ አጋዥ ናቸው፡፡

የብዙ አመታት ወዳጃቸው የነበሩት አጼ ሀይለስላሴ በደርግ ወታደራዊ መንግስት ሲተኩ የተባበረችው አሜሪካ መሪዎች ዝምታን መርጠው ነበር፡፡ በነገራችን ላይ ለአጼ ሀይለስላሴ ስርአት መውደቅ ሁነኛውን ሚና የተጫወቱት በግዜው የነበሩት የዩነቨርስቲ እና ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች፣የታክሲ ሹፌሮች፣የሙያ ማህበራት እና የፖለቲካ ድርጅት መሪዎች የነበሩ ሲሆን ደርግ ብቻውን ስልጣኑን ሲቆጣጠር በኢትዮጵያ የዲሞክራሲ ስርዓት እንዲሰፍን ለመርዳት ፍላጎታቸው አልነበረም፡፡ ደርግን የጠሉት ኋላ ላይ የቀድሞዋ ሶቪዬት ህብረት ሁነኛ ወዳጅ ከሆነ በኋላ ነበር፡፡ በኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ፍላጎታቸው ባይሆንም የአገዛዝ ለውጥ እንዲኖር ውስብስብ ሴራቸውን ገቢራዊ ከማድረግ ግን አልቦዘኑም ነበር፡፡ የቀድሞዋ ሶቪዬት ህብረት ወደ ታሪክ ማህደር ውስጥ ከተዶለች ወዲህ ወታደራዊው መንግስት የሚረዳው መንግስት እንደሌለው እና የፕሬዜዴንት መንግስቱ ሀይለማርያምን  ወደ ዚምባብዌ ሀራሬ መሰደድን በቅጡ የተረዱት አሜሪካኖች በሰሜን ኢትዮጵያ አማጺ ቡድን የነበሩትን የትግራይ ነጻ አውጪ ድርጅት በመደገፍ ለስልጣን እንዳበቋቸው የአደባባይ ሚስጥር ነው፡፡ በነገራችን ላይ የነበረውን የስልጣን ክፍተት ለመሙላት በሚል በጆርጅ ደብሊው ቡሽ ቃለ ቡራኬ ተሰጥቷቸው የነበረው የትግራይ ነጻ አውጪ ድርጅት የፖለቲካ ፊትአውራሪዎች እንደ ጎርጎሮሲያኑ አቆጣጠርከ1990 እስከ 2018 ድረስ ኢትዮጵያን እንደ ሰም አቅልጠው፣ እንደ ብረት ቀጥቅጠው ገዝተዋል፡፡ , the TPLF, was then pushed into power by the US Administration of Pres. George H. W. Bush, to fill the vacuum, and the TPLF ruled until 2018.  

ዛሬ ባለው ተጨባጭ ሁኔታ ሃምሳ አመት እድሜ ያላቸው ፣ የአየርላንድ ተወላጇ በቀድሞው ግዜ (  እ.ኤ.አ. ከ2009-2017 ድረስ በፕሬዜዴንት ባራክ ኦባማ አስተዳደደር ግዜ ማቴ ነው፡፡ ) በተባበሩት መንግስታት የአሜሪካ አምባሳደር የነበሩት ሳማንታ ወደ ኢትዮጵያ የመጡት የሚከተሉትን የተጽእኖ መልእክቶችን ለኢትዮጵያ መንግስት ለማሳወቅ እንደነበር የፖለቲካ አዋቂዎች በጽሁፎቻቸው ላይ አሳውቀዋል፡፡

  1. የተባበረችው አሜሪካ በየአመቱ 1ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ለኢትዮጵያ በብድር ወይም በእርዳታ መልክ እንደምትለገስ  በማሳወቅ ጫና መፍጠር
  2. ፍጹም ምክንያታዊ ባልሆነ መልኩ የአሜሪካንን ፍላጎት ብቻ መሰረት በማድረግ የኢትዮጵያ መንግስት ከአሸባሪው ከትግራይ ነጻ አውጪ ድርጅት ጋር የሚያደርገውን ፍልሚያ እንዲያቆም የሚያስችል መልእክት ማድረስ እና የመሳሰሉት ነበሩ፡፡ ሁለቱም መልእክቶች ገቢራዊ ማድረግ የማይቻሉ ናቸው፡፡
    በነገራችን ላይ እንደ ጎርጎሮሲያኑ አቆጣጠር ከ1990 እስከ 2018 የማእከላዊ መንግስቱን ተቆጣጥሮ የቆየው የወያኔ-ኢህአዲግ አገዛዝ ቡድን  የወደቀው ሌሎች እንደ አስከፊ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ያሉት እንዳሉ ሆነው በዋነኝነት  በለየለት ዝርፊያ ምከንያት እና በመሪው አቶ መለስ ዜናዊ ሞት ምክንያት እንደነበር ብዙዎች የፖለቲካ ተንታኞች የሚስማሙበት ጉዳይ ነው፡፡

በመጨረሻም የአልባኒያ አክራሪ ሶሻሊስት ርእዮት አለም የመገንጠል ጥያቄ አቀንቃኝ የነበረው ቡድን ወደ ቀደመው ግብሩ፣ወደ የትግሉ መነሻ ክፍል ተመልሶ ሄዷል፡፡ ዛሬ ይሄ ቡድን ከኢትዮጵያ የፌዴራል መንግስት ጋር ጦርነት መግጠሙ የታወቀ ጉዳይ ነው፡፡ በነገራችን ላይ በመጀመሪያ ጦርነቱን የጀመረው የወያኔ ቡድን ነው፡፡ ጦርነቱ እንደተጀመረ የወያኔ ቡድን በማይካድራ ከተማ በንጹሃን ዜጎች ላይ የፈጸመው አስከፊ የሰብዓዊ መብት ጥሰት የሚዘነጋ አይደለም፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ በምእራባውያን ግፊት እና ድጋፍ ይህ ቡድን የሚያደርገው እኩይ እንቅስቃሴ ለኢትዮጵያ አንድነት እንደማይበጅ በርካታ የፖለቲካ ተንታኞች በየግዜው አበክረው የሚያስጠነቅቁት ጉዳይ ነው፡፡

በርግጥ ይህ የተባበረችው አሜሪካ በሚሰተር ብሊንከን አመሃኝነት የምታደርገው የፖለቲካ ጨዋታ ፣ በቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዜዴንት ዊሊያም ክሊንተን አስተዳደር ግዜ ከነበረው የፖለቲካ ጨዋታ ጋር ተመሳሳይነት ያለው ነው፡፡ እንደ ጎርጎሮሲያኑ አቆጣጠር 1990 ዩጎዝላቪያ ላይ ገቢራዊ ያደረገችውን የፖለቲካ ጨዋታ የግብጽን የቆየ ህልምና ፍላጎት ለማሳካት ማለትም የአባይን ወንዝ ከምንጩ ለመቆጣጠር  ኢትዮጵያ የተዳከመች እና የተከፋፈለች  ሀገር መሆን አለባት የሚል አደገኛ የፖለቲካ ጨዋታ ከጀመሩ አመታት ተቆጥረዋል፡፡

በሌላው የሳንቲሙ ግልባጭ እንደ ጎርጎሮሲያ አቆጣጠር ነሐሴ 4 2021  ሚስስ ሳማንታን ፓወር የአዲስ አበባን ጉብኝታቸውን ጨርሰው እንደሄዱ የአሜሪካው ከፍተኛ ባለስልጣን ብሊንከን ለሱዳኑ ጠቅላይ ሚንስትር  አብደላ ሃምዱክ ( Sudanese interim Prime Minister Abdalla Hamdok ) በላኩት መልእክት ወይም በስልክ እንደተነጋገሩት ሱዳን በኢትዮጵያ የውስጥ የፖለቲካ ጉዳይ ላይ ሚና እንዲኖራት በሚያስመስል መልኩ የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲደረግ ሱዳን ጥሪ እንድታደርግ አግባብተዋል፡፡ ሆኖም ግን ይሁንና የኢትዮጵያ መንግስት የአንድ ወገን የተኩስ አቁም ውሳኔ ቢያደርግም የትግራይ ነጻ አውጪ ድርጅት ተኩስ ማቆም ፍላጎት እንደሌለው ደግሞ ደጋግሞ አሳይቷል፡፡ በአጭሩ በጦርነቱ ገፍቶበታል፡፡

እንደ ፕሮፌሰር አክሎግ ቢራራ የመሰሉ የምጣኔ ሀብት ጠበብት በጥናታቸው እንደረሱበት ከሆነ የወያኔ ቡድን የማእከላዊ መንግስቱን ስልጣን በተቆጣጠረበት ሃያ ሰባት አመታት ውስጥ በብዙ ቢሊዮን የሚቆጠር የአሜሪካን ዶላር እንደዘረፈ ይነገራል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ በሰሜን ኢትዮጵያ የተከሰተውን ጦርነት በተመለከተ የምእራቡ አለም መገናኛ ብዙሃን ወገንተኝነታቸው ለምን ለወያኔ ቡድን ሆነ ብሎ መጠየቁ ተገቢ ሳይሆን አይቀርም፡፡ እዚህ ላይ አንድ ምሳሌ ላንሳ ከአለም መገናኛ ብዙሃን ዘገባ ለመረዳት እንደተቻለው የቀድሞዋ ዩጎዝላቪያ አካል የነበሩት ክሮሺያ ፣ቦስኒያ እናአልባኒያ ሙስሊሞች ( the Croatian, and Bosnian (and Albanian) ) ከዩጎዝላቪያ ለመገንጠል በተደረገው ውይይት ላይ የበላይነት ለማግኘት ሲሉ ለምእራባውያን መገናኛ ብዙሃን ከ 2 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር በላይ ወጪ እንዳወጡ ጥናቶች ያሳያሉ፡፡ ስለሆነም  የትግራይ ነጻ አውጪ ድርጅት የፖለቲካ ፊትአውራሪዎች እንዲህ አያደርጉም ብሎ መገመት ተላላነት ይመስለኛል፡፡ በሌላ የሳንቲሙ ግልባጭ ደግሞ ኢትዮጵያ ከህዝባዊት ቻይና፣ከሩሲያ ፌዴሬሽ እና ከቱርክ ጋር የምታደርገው የጠበቀ ግንኙነት የምእራቡን አለም መንግስታት እና መገናኛ ብዙሃኖቻቸውን ያሳስባቸዋል፡፡

እንደ ጎርጎሮሲያኑ አቆጣጠር ሐምሌ 12 2021 ኢትዮጵያ እና ሩሲያ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ አብረው ለመስራት ስምምነት አድርገዋል፡፡ የሩሲያ ጎረቤት እና አጋር የሆነችው የቀድሞዋ ሶቪዬት ህብረት አካል የነበረችው ቤልሩስ ሳትቀር ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር መልካም የውጭ ግንኙነት እንዳላት ይነገራል፡፡ እንደ ጎርጎሮሲያኑ አቆጣጠር መጋቢት 9 ቀን 2021 የሩሲያው ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ  (Russian Foreign Minister Sergey Lavro) ኢትዮጵያን የጎበኙ ሲሆን፣ የስልጣን አቻቸው የኢትዮጵያው ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር እና ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ሩሲያን እንደ ጎርጎሮሲያኑ አቆጣጠር ሰኔ 23 ቀን 2021 ሩሲያን ጎብኝተዋል፡፡

 የአሜሪካ መንግስት ፊቱን ያዞረበት የኢትዮጵያ መንግስት  ባወጣው መግለጫ ላይ እንደጠቀሰው የአንድ ወገን ተኩስ ማቆም ውሳኔ መድረሱን ገልጾ ካበቃ በኋላ የወያኔ ሀይል የአንድ ወገን የተኩስ አቋም ውሳኔውን በመጣስ በጦርነት በመቀጠሉ ምክንያት የተነሳ ከዚህ ቡድን ጋር ውይይት ለማድረግ እንደማይፈልግ በይፋ ተናግሯል፡፡ ሆኖም ግን ይሁንና በክልሉ ከሚገኙት ሌሎች በሰላማዊ ትግል ከሚያምኑት ጋር ውይይትና መነጋገር በትግራይ ክልል ሰላም ማምጣት ያችላል የሚል የግል አስተያየት አለኝ፡፡ ምንም እንኳን የምእራቡ አለም እና እንደ አልጀዚራ የመሳሰሉ መገናኛ ብዙሃን በኢትዮጵያ የመከላከያ ሃይል ላይ ስለደረሰው ጉዳት ብቻ ዘውትር ቢዘገቡም፣ ለደረሰው ሰብዓዊ ቀውስ  ወይም ጉዳት ሁሉ የማእከላዊ መንግስቱን ብቻ ተጠያቂ ቢያደርጉም በመሬት ላይ ያለው እውነት ለየቅል ነው፡፡ ለዚህ ሁሉ ምስቅልቅል በዋነኝነት ተጠያቂው ወራሪውና አሸባሪው ሀይል ህውሃት ነው፡፡ በዚች ሀገር ላይ የርስበርስ ጦርነት ቋያ የቀሰቀሰው ወይም የጀመረው ህውሃት ነው፡፡ ይህ የለየለት የከሃዲዎች ስብስብ ዘላቂ ጥላቻ በማህበረሰብ መሃከል እንዲኖር የመስራቱ ጉዳይ፣ከለየላቸው የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች ጋር የትብብር አንድነት በመመስረቱ ወያኔ በታሪክ ተወቃሽ መሆኑ ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡ ወያኔ ኢትዮጵያ መፈረስ አለባት በማለት አዱከበሬ ከሚመቱ ሀገራት ጋርም ጥምረት መፍጠሩ ሌላው መገለጫው ነው፡፡ በእኔ የግል አስተያየት በኢትዮጵያ እየደረሰ ላለው አስከፊ የሰብዓዊ ቀውስ በምንም አይነት መልኩ የኢትዮጵያ መንግስት ፣ ከወያኔ አጥፊ ቡድን እኩል ተጠያቂ አይሆንም፡፡ ወያኔ በፈጠረው ህገ መንግስት፣በሰራው የሀሰት የታሪክ ትርክት ( በሚከተሉት ርእዮት የተነሳ)፣ አንድን ህብረተሰብ በጠላትነት መፈረጃቸው ወዘተ ምንግዜም ቢሆን ተጠያቂ ነው፡፡ ወያኔ ሲነሳም፣ሲበላም፣ሲተኛም ዘውትር የሚያስበው አስኳል አላማው ኢትዮጵያን ማዳከም ነው፡፡ በህብረተሰብ ውስጥ የማይታረቅ እና ዘላቂ ቅራኔ ወይም ጥላቻ መፍጠርም የዚህ አረመኔ እና ጨካኝ ድርጅት ነው ወያኔ፡፡ከወያኔ የበለጠ የኢትዮጵያ ጠላት የለም፡፡ወያኔ የማይፈወስ የዘር ፖለቲካ በሽታ የተጠናወተው እኩይ ድርጅትም ነው፡፡ ከወያኔም አልፎ ሌሎች አክራሪ የጎሳ ፖለቲከኞችን ፈጥሮም የሚገኝ ነው፡፡ 

 በነገራችን ላይ ከወያኔ አጥፊ ቡድን ጋር ድብቅ ግንኙነት ሊያደርጉ ይችላሉ በሚል ምክንያት ወይም ከተፈቀደላቸው የሥራ ተግባር ውጭ ሲንቀሳቀሱ የተገኙ የሚከተሉት አለም አቀፍ ድርጅቶች በኢትዮጵያ መንግስት ውሳኔ ለተወሰኑ ወራቶች በኢትዮጵያ ምድር እንዳይንቀሳቀሱ መከልከላቸውን ከመገናኛ ብዙሃን ተሰምቷል፡፡

  1. ድንበር የለሽ የሀኪሞች ቡድን (the Dutch branch of Doctors Without Borders )
  2. (የኖርዌይ ስደተኞች ጉባኤ (the Norwegian Refugee Council) 
  3. የማካቱም ድርጅት (the Maktoum Foundation ) ይገኙበታል፡፡

ከላይ የተጠቀሱት እርምጃዎች እንዳሉ ሆነው ሳማንታ ፓወር የሰብዓዊ ቁስ መተላለፊያ “humanitarian corridor በሚል ምክንያት ኢትዮጵያን ከሱዳን ጋር በሚያዋስናት ድንበር አኳያ ወደ ትግራይ የሚወስድ መንገድ እንዲከፈት ላቀረቡት ጥያቄ የኢትዮጵያ መንግስት መልስ እሺታ ሳይሆን እምቢታ ነበር፡፡ ይህ አግባብ እና ተገቢ መልስ ነበር ብዬ አስባለሁ፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ ልኡል ኤርምያሰ ሳህለስላሴ ሀይለ-ስላሴ ( Ethiopian Crown Council Pres. Prince Ermias Sahle-Selassie Haile- Selassie ) ከቀድሞዋ ዩጎዝላቪያ መፈረካከስ ኢትዮጵያ ተምራ እንዴት አንድነቷን ማስከበር እንዳለበት አውጥተውት ወይም አዘጋጅተውት የነበረው ሰነድ ይበል የሚያሰኝ ነው፡፡

ከአንዳንድ አለም አቀፍ መገናኛ መረጃዎች ለመገንዘብ እንደሚቻለው የቫቲካን ካቶሊክ (The Vatican) እንደ ጎርጎሮሲያን አቆጣጠር 1990 ላይ የክሮሺያን የመገንጠል አላማ ትደግፍ ነበር፡፡ ዛሬ ደግሞ የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን የኢትዮጵያ አንድነት እንዲጠበቅ ለመርዳት ዝግጁ እንደሆነች በተደጋጋሚ ስተናገር ይሰማል፡፡ በእውነቱ ለማናገር መልካም ዜና ነው፡፡ ለማናቸውም ምእራባውያን የአፍሪካውን ቀንድ አካባቢ እያጡት ስለመሆኑ በማስታወስ የዛሬን ጽሁፌን እቋጫለሁ፡፡ ሰላም፡፡

The Vatican, in the 1990s, had supported Croatia in its attempt to secede. Now, Roman Catholic Pope Francis I has supported attempts to protect Ethiopian unity and Ethiopian Christendom. Other Christian leaders around the world are joining this defense of Ethiopian unity. Not only does it represent 3,500 years of Judeo-Christian history, Ethiopia also controls the lower Red Sea, one of the most critical sea routes in the world.

Filed in: Amharic