>

ከህወሃት ጋር እየተካሄደ ያለው ጦርነት ዜና የሸፈነው ከ300 በላይ አማሮች አሰቃቂ ጭፍጨፋ በምስራቅ ወለጋ፦ (ወንድወሰን ተክሉ )

ከህወሃት ጋር እየተካሄደ ያለው ጦርነት ዜና የሸፈነው ከ300 በላይ አማሮች አሰቃቂ ጭፍጨፋ በምስራቅ ወለጋ፦

ወንድወሰን ተክሉ

፠ ጋብ ብሎ የነበረው በወለጋ አማራን የመጨፍጨፉ ዘመቻ ተባብሶ ቀጥሏል ፤ ልዩ ሀይሉ ቀድሞ በየቤቱ የመሳሪያ ገፈፋ ያደርጋል ፤
 የምእራብ ኦሮሚያ ኮማንድ ፖስትም ይህንን ጭፍጨፋ ሊያስቆሙ አልቻሉም ሳይሆን ሊያስቆሙ አልፈለጉም፤ ወይም አልታዘዙም!!!
በምስራቅ ወለጋ ሆሮጉዱሩ በሚኖሩ የአማራ ተወላጆች ላይ በተከፈተ የጭፍጨፋ ጦርነት ከ300 በላይ አማሮች የተጨፈጨፉ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ የ72 ያህሉን ማንነት ለይቶ ለማወቅ መቻሉን ሰለባዎቹ ይናገራሉ።
መቀመጫውን በቀምት ያደረገና በብጄ/ል ባጫ ደበሌ የሚመራውና በጠምር ቢሮ በዶ/ል አልሙ ስሜ የፖለቲካ አመራር የሚመራው የምእራብ ኦሮሚያ ኮማንድ ፖስትም ይህንን ጭፍጨፋ ሊያስቆሙ አልቻሉም ሳይሆን ሊያስቆሙ አልፈለጉም።
ጭፍጨፋውን ከኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ጀምሮ እስካሁን ድረስ አንድም መንግስታዊ ሚዲያ አልዘገበውም።
መጅመሪያ ላይ በዚህ ሳምንት አጋማሽ የፌዴራሉ መንግስት ሂላኮፕተር በአካባቢው ላይ ተከታታይ የቅኝት በረራ ካደረገች በኋላ አካባቢው ሙሉ በሙሉ የኢንተርኔትና የስልክ አገልግሎት ሙሉ በሙሉ እንዲቌረጥ ከተደረገ በኋላ ጭፍጨፋውን ኦነግ ሸኔ ተብሎ በሚጠራ  ተጣቃ ስም መጠነ ሰፊ በሆነ ዘመቻ በማካሄድ ከ40ሺህ በላይ አማሮችን በማፈናቀልና ከ300 በላይ የሆኑትን በአሰቃቂ ሁኔታ ጨፍጭፎ በመግደል አማራን ከአካባቢው መንጥሮ የማጽዳቱን ዘመቻ በጸጥታ እየተፈጸመ ነው።
ጨፍጫፊው ታጣቂ ሚሊሺያ በኦነግ ሸኔ መጠሪያ የዳቦ ስም ይጥሩት እንጂ የጭፍጨፋው ሰለባ ተራፊዎች እንደሚገልጹት ከሄነ ግን «መከላከያውና የኦሮሚያ ልዩ ኋይል በጋራ ተባብረው እኛ ዘንድ ተደብቆ የቀረ ጥቂት መሳሪያ ገፍፈው ከነጠቁ በኋላ በአስቸኴይ አካባቢውን ለቃችሁ ወደ ሀገራችሁ(ወደ አማራ ክልል) ካልሄዳችሁ እኛ ልንከላከላችሁ እንችልም። ሽፍታው ከሀገሬ ይውጡልኝ ነው ያላችሁ ብለው በግልጽ አዘዙን። ብዙም ሳይቆዩ ታጣቂዎቹ መጥተው መጨፍጨፍ ሲጀምሩ ወታደቶቹና የኦሮሚያ ልዩ ህይል ሲያግዛቸው አየን እንጂ ዘወር እንካን ለማለት ሲሞክሩ አላየንም።» በማለት ጭፍጨፋው በኦሮሚያው ክልል ፕሬዚዳንት ሽመልስ አብዲሳና በአለቃው አቢይ አህመድ እቅድና ፕላን መሰረት እየተካሄደ ስለመሆኑ ያመላክታል።
በተለይ የአቢይ መራሹ የብልጽግናው መንግስት የሚመራው አቢይ አህመድ ፍላጎት እቅድና ፕላን መሆኑን የሚያረጋግጠው በእሱ ዋና አዛዥነት የሚታዘዘው የመከላከያ ሰራዊት ነቀምቴ ላይ የኬማንድ እዙ አቌቁሞ ባለበት ሁኔታ በቂ ወታደራዊ ኋይል እያለው ያለአንዳች የመከላከል ውጊያ በአይኖቹ ስር ይህንን መሰል ዘግናኝ እልቂት የፈጠረ ጭፍጨፋ ሲፈጸም በተመልካችነት መሳተፉ ነው።
ከ40በላይ በሆነ የስልጠና ዙር  ከመቶሺህ በላይ የክልሉን ልዩ ኋይል አሰልጥኖ ማደራጀቱ የሚነገርለት የሽመልስ አብዲሳ ልዩ ኋይል በዚህ ጭፍጨፋ ላይ ልክ እንደከዚህ ቀደምቶቹ ጭፍጨፋ በተመልካችነት ብቻ የተሳተፈ ሳይሆን የአማራ ተወላጆቹን መስሪያ በመግፈፍ አካባቢውን በሂሊኮፕተር ቃኝቶ ለጨፍጫፊው በማመቻቸትና የአማራ ተወላጆችን ቤት በመዝረፍ በማቃጠልና ከዚህ አካባቢ ውጡ ብሎ በማዘዝም በቀጥታ ተሳታፊነቱን በግላጭ ያሳየበት ጭፍጨፋ ነው የተፈጸመው።
የልዩ ኋይሉ እንቅስሤ በሙሉ በደመነፍስ የተደረገ አሊያም በግል ተነሳሽነት የተፈጸመ ሳይሆን በሚመሩት አዛዦቹ ቀጥተኛ የአድርግ ትእዛዝ ጠፈመና የሚፈጽም መሆኑና የዚህም ትእዛዝ ዋና ምንጭ ሽመልስ አብዲሳና አቢይ አህመድ መሆናቸውን ስናይ ጭፍጨፋውን የፈጸመውና እየፈጸመ ያለው አማጺው የኦሮሞ ነጻ አውጪ ሰራዊት ወይም ኦነግ ሸኔ የሚባለው ታጣቂ ኋይል ሳይሆን በዚህ ታጣቂ ቡድን ስም ፍላጎቱን እያስፈጸመ ያለውን የብልጽግናን መንግስት መሆኑን ነው ማወቅ የምንችለው።
የአማራን ክልላዊ መንግስት በመምራት የአማራን ህዝብ እወክላለሁ ባዩ የአገኘሁ ተሻገር አስተዳደር አይደለም ዛሬ በጦርነት ላይ ሆኖ ይቅርና በሰላሙም ጊዜ ቢሆን ስለሚጨፈጨፉት አማሮች ተቆርቁሮ ጥብቅና የሚቆም ሳይሆን ጨፍጫፊውን ባህርዳር እየጠራ አመስግኖ የሚሸልም ጸረ አማራ ባንዳ በመሆኑ ዛሬም እንደልማዱ ትንፍሽም ሳይል 7/24ሰዓት ስለወያኔ ሲያላዝን የምንሰማው ሆናል።
ይህ በህወት የተከፈተው ጸረ አማራ ወረራ በግንባር ያለውን ህዝብ ከመጉዳቱም ባሻገር ለሽመልስ አብዲሳና ለአቢይ አህመድ ይህንን አይነቱን አማራን ከኦሮሚያ የማጽዳቱን ጭፍጨፋ ዘመቻን ሳይሰማና ትኩረት ሳያገኝ እንዲፈጽሙት በማገዙ በኩል ትልቁን ጉዳት እያደረሰ መሆኑን  እያየን ነው።
ከጭፍጨፋው የተረፉትና ለመትረፍም ብለው አካባቢያቸውን ለቀው የተፈናቀሉት ቁጥር ከ40ሺህ በላይ የሆነ ሲሆን በየጫካው ተበትነው የወገን ያለህ እያሉ በመጮህ ላይ ናቸው።
መላው የአማራ ህዝብ ወረራ ተፈጽሞብኛል በማለት ሁለንተናዊ አትኩሮቱን በጸረ ወረራ የህልውና ጦርነት ዘመቻ ላይ ባደረገበት በዚህ ወሳኝ መጥፎ ጊዜ ወዳጅ መሳዩ የአማራ ህዝብ ጠላት የሆነው የትህነጉ ልጅ ኦህዴድ/ብልጽግና/ኦነግ ሸኔ ይህንን አጋጣሚ ተጠቅመው መጠነ ሰፊ የማጽዳት ዘመቻን እየፈጸሙና እያስፈጸሙ ያሉበት እጅግ የተረገመ ወቅት ሆናል።
እናም ይህን አስከፊ ሁኔታን ከግንዛቤ ውስጥ በማስገባት መላው የአማራ ህዝብ በኦሮሚይ ክልል በምስራቅ ወለጋ በማንነታቸው ምክንያት የጭፍጨፋ ዘመቻ በተከፈተባቸው ወገኖቹ ላይ ትኩረት በመስጠት ሁለንተናዊ የድጋፍ እጁን እንዲዘረጋ-ድምጽም ሆኖአቸው ያሉበትን ሁኔታ እንዲያስተጋባ በዚሁ አጋጣሚ እጅግ አበክሬ አሳስባለሁ።
Filed in: Amharic