>

ታሪክ ራሱን ሲደግም....!!! (ጌታቸው ሽፈራው)

ታሪክ ራሱን ሲደግም….!!!

ጌታቸው ሽፈራው

*…. ፀረ አማራው ትህነግ እንሰሳቶቹን እንኳን አልማራቸውም!
 
ታሪክ እንደሚነግረን በአፄ ቴዎድሮስ ጊዜ አፄ ዮሐንስ መይሣውን አሳልፎ ለመስጠት ከእንግሊዝ የተበረከተለት በርካታ የጦር መሣሪያ ነበር። ይህን የጦር መሳሪያም አክሱም ውስጥ በማከማቸት ምኒልክንና ተክለ ሃይማኖትን (አማራን) ለመምታት ሊጠቀሙበት አስበው በምሥጢር ይዘውት ነበር። ከዚህ ዕቅድ መሳካት በፉት በአጋጣሚ ሆኖ አፄ ዮሐንስ መተማ ላይ ተሰዋ። ከዚያም የሸዋው ምኒልክ ንግሥናውን ተረከበ። በዚህን ጊዜ የትግራይ መኳንንት ሦስት ቀን መከሩ። በምክራቸውም ከዚህ በኋላ ምኒልክን አሸንፎ ንግሥናውን መረከብ እንደማይችሉ አረጋገጡ። በአክሱም ተከዝኖ የነበረውን ከእንግሊዝ የተቀበሉትን ጦር መሳሪያ በሚመለከትም “ምኒልክ አንድ ቀን ደርሶበት መውሰዱ ስለማይቀር ሸዋ/አማራ ከሚጠቀምበት እናቃጥለው” ብለው በእሳት አንድደው አወደሙት። (ምንጭ “ደመላሽ የአርበኞች ታሪክ መጽሐፍ)
ይኸው ነው የእነርሱ ባሕርይ። በዘመን የማይቀየር ክፋት የተሞላበት ባህርይ። አሁን እያደረጉት ያለው አዲስ ነገር አይደለም። የአባቶቻቸው ልጆች መሆናቸውን ለማስመስከር ታሪክን እየደገሙት ነው። የሚገርመው በሰሞኑ ጦርነት ያደረጉት ይህን የሚመስል ነበር። በብዙ ቦታዎች ከባድ ሽንፈት ሲገጥማቸውና ዘርፈው ለመውሰድ እንደማይችሉ ሲገነዘቡ ንብረት ያወድማሉ ቤት ያቃጥላሉ። ከምንም በላይ እጅግ ዘግናኙ ድርጊታቸው ለእንስሳትም እንኳን ሳይራሩ በየቦታው በጭካኔ እየገደሉ ጥለዋቸዋል።
ፀረ አማራው ትህነግ እንሰሳቶቹን እንኳን አልማራቸውም!
አሸባሪው ትህነግ ሰውን ገድሎ፣ ንብረት ዘርፎና አውድሞም ብቻ አልበቃውም። ከግጦሽ የሚመለሱ እንሰሳቶችን ሳይቀር በጥይት ፈጅቷል።
በደቡብ ጎንደር ጋሳይ አካባቢ  ግጦሽ ውለው የሚመለሱ የቤት እንስሳትን ሳይቀር ተኩሰው መግደላቸውን የአካባቢው ነዋሪው ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ገልፀዋል።
የሽብር ቡድኑ አባላት የአርሶ አደሩን ንብረት በመዝረፍ በሬ፣ በግ እና ፍየል እያረዱ ከመብላት ባለፈ መንገድ ላይ ያገኙትን መግደላቸውን ገልፀዋል።
የቡድኑ አባላት ምንም አይነት ሰብዓዊነት ያልፈጠረባቸው አረመኔዎች ናቸው። ለእነርሱ የማይሆን ምንም ንብረት ሌላው እንዲጠቀምበት አይፈቅዱም። እነርሱ የማይመራት ሀገርም ተበትና እንድትፈራርስ ነው እየሰሩ ያሉት። ይህን ለማድረግም ከውጭ ጠላት ጋር ያለ ይሉኝታ ይተባበራሉ።
እንግዲህ እነዚህን ቆሞ ማየትም ሆነ መዘናጋት ምን ያህል ዋጋ እንደሚያስከፈል አውቀን ፍፃሜውን እናፍጥነው። ትንሽ እድል ከሰጠናቸው ሀገር አፍርሰውና ንብረት ዘርፈው አይበቃቸውም። ለእነርሱ የማይሆነውን ምንም ነገር በማውደም ባዶ ምድረ በዳ ይተውልን እና በርሃብ እንድናልቅ ነው አላማቸው። አይሳካላቸውም እንጅ ቢሳካላቸው ሙሉ ከተሞችን ዘርፈው ያቃጥሉታል። ገጠሩንም ያወድሙታል። ለእነዚህ ጊዜ መስጠት ኃጢአት ነው።
Filed in: Amharic