ሪፖርተር
የአሜሪካ መንግሥት ተራድኦ ድርጅት ዩኤስኤይድ ኃላፊ ሰማንታ ፓወር በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአሸባሪነት የተሰየመው የሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) ኃይሎች በአማራና አፋር ክልሎች ጥቃት መፈጸማቸውን እንዲያቆሙ፣ የአማራና የኤርትራ ኃይሎችም ከትግራይ ክልል እንዲወጡ አሳስቡ፡፡
ከሁለት ሳምንት በፊት በኢትዮጵያ ስላለው ጦርነትና የሰብዓዊ ዕርዳታ አቅርቦት ጉዳይ ለመነጋገር መጥተው የነበሩት ኃላፊዋ፣ የአሜሪካ መንግሥት ኢትዮጵያውያንን ለማጋዝ ቁርጠኛ እንደሆነ ሐሙስ ነሐሴ 13 ቀን 2013 ዓ.ም. ባወጡት መግለጫ አስታውቀዋል፡፡
ፓወር በትግራይ ክልል ጦርነት ከተቀሰቀሰ በኋላ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ውስጥ ለመጀመርያ ጊዜ የዕርዳታ ድርጅቶች በሚሊዮን ለሚቆጠሩ ዕርዳታ ፈላጊዎች የሚያቀርቡት ምግብ ሊያልቅባቸው እንደሆና ዩኤስኤይድን ጨምሮ የበርካታ ድርጅቶች የምግብ መጋዘኖች ባዶ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡
ተጨማሪ ያንብቡ: http://bit.ly/3zeb2ao