>

"ጻድቃንን ጨምሮ ከፍተኛ መኮንኖች ዋስትና ጠየቁ...!!!" (ኢትዮ 12)

“ጻድቃንን ጨምሮ ከፍተኛ መኮንኖች ዋስትና ጠየቁ…!!!”

ኢትዮ 12


የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር በአማራ ክልል ከወረራቸው አካባቢዎች ከፍተኛ ሰብአዊና ቁሳዊ ኪሳራ ደርሶበት እንዲለቅ፣ የሸሸውም ተከቦ አማራጭ አልባ መሆኑ በአማራ ክልል ባለስልጣኖችና በመከላከያ ከፍተኛ ሃላፊዎች እየተነገረ ባለበት በአሁኑ ሰዓት የዋስትና ጥያቄ መነሳቱ ተሰማ። ጻድቃን ከባልደረቦቻቸው ጋር ሰፊ ነግግር አድርገው “ጦርነት በቃን” ማለታቸው ተሰምቷል።

የኢትዮ12 ታማኝ የዜና ምንጭ እንዳሉት ትህነግ ከፍተኛ የሰው ማዕበል በማጉረፍ አማራ ክልልን ወሮ በከፍተኛ መስዋዕት ወደ ወለጋ በመግባት መንግስት ለመቀየር የጀመረው ዘመቻ ባለመሳካቱ ተስፋ መቁረጥ ነግሷል። በመሆኑም ጀነራል ጻድቃንን ጨምሮ ከፍተኛ መኮንኖች ዋስትና መጠየቃቸውና ይህንኑ ጥያቄ ወዳጆቻቸው ለመንግስት አቅርበዋል። ዋስትናው ምን ድረስ እንደሆነ ባይታወቅም፣ እነ ጻድቃን ነጻ የመሆን ጥያቄ እንዳላቸው ግን ታውቋል። ጥያቄያቸውን እነ ደብረጽዮን ይቀበሉት አይቀበሉት የታወቀ ነገር የለም።

ጻድቃን ወደ ያካማቹትን ሃብት ጥለው ወደ በረሃ ከወረዱ በሁዋላ በተደጋጋሚ ” ይህ እንዳይሆን በሰላም እንዲያልቅ ለምኜ ነበር” ሲሉ ይደመጣሉ። ከለውጡ በፊት ድህንነቱን፣ መከላከያውንና ፖሊስን ትህነግ እንደያዘ ቀጥሎ በአስተዳደር ረገድ ብቻ ለውጥ እንዲደረግ ሃሳብ አቅርበው እንደነበር አይዘነጋም። ከፍተኛ ባለሃብት የሆኑት ጻድቃን በሰው ማዕበል አማራ ክልልንና አፋር ክልልን በወረሩ ማግስት “ምጡቁ ጀነራል” በሚል ቢቢሲን ጨምሮ በርካታ ሚዲያዎች ሲያደንቋቸው ነበር።

ከትግራይ የሚሰማው ዜና ለዳግም የሰው ማእበል ጦርነት ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሰራዊት እየተዘጋጀ መሆኑንን ነው። ዝግጅቱ ቢኖርም እነ ጻድቃን “ጦርነት ይብቃ” የሚል ግምገማ አድርገዋል። መዕከላዊ መንግስት እያሰለጠነ ያለው ከ700 ሺህ በላይ መድበኛ ሰራዊትና ተመሳሳይ መጠን ያለው ጊዚያዊ ሃይል፣ ከከልል ልዩ ሃይልና ሚሊሻ ጋር ተዳምሮ የሚፈጥረው ሃይል ትህነግ ምንም ያህል እንዲራመድ ሰላማያስችለው ይመስልላ እንደ ጻድቃን ” በቃ” ማለታቸው ተሰምቷል።

በተመሳሳይ ከፍተኛ መሳሪያን ቴክኖሎጂ እየገነባ ያለው የኢትዮጵያ መከላከያ ሃይል ቀደም ሲል የነበረበትን የከባድ መሳሪያ ምድብተኞች እጥረት ያስተካከለ በመሆኑ ሙሉ ማጥቃቱ ከተጀመረ በቂያ የሰው ሃይልና ሎግስቲክ መዋጋቱ ብቻ ሳይሆን፣ የደጀን ሃይሉ በነላው አገሪቱ ተመሳሳይ አቋም መያዙና ትህነግ ከኦነግ ሸኔ ጋር የፈጠው ጥምረት በኦሮሚያ ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ፖለትኪአዊ ኪሳራ በማስከተሉ ለተፈጠረው ስጋትና ተስፋ መቁረጥ ዋና ምክንያት መሆኑ ተመልክቷል። ከዚህም በተጨማሪ በአማራ ክልል በህቡዕ ተጀምሮ የነበረው አንድ ለ200 አደዕጃጀት መጨንገፉ ተዳምሮ ትህነግን ከእርቅ ውጪ አማራጭ አልባ እንዳደረገው የመረጃው ሰዎች አስታውቀዋል። የትህነግ አመራሮች ሱዳን ከርመው ያደረጉት ድንበር የማስከፈት ንግግርም በሱዳን በኩል ደፍሮ ውጊያ ለመክፈት የሚያስችል ደረጃ አለመድረሱም ሌላ ተጨማሪ ምክንያት መሆኑ ታውቋል።

ከጦርነቱ ጎን ለጎን በእነ ዶክተር ደብረጽዮን መዝገብ በአገር ክህደትና ክፍተኛ ወንጀል የክስ ሂደታቸው እየታየ በመሆኑ መንግስት ህግ ከሚፈልጋቸው አካላት ጋር በጎን የሚደራደረው አንዳችም ጉዳይ እንደሌለ ማስታወቁ ተሰምቷል። ይሁንና እጃቸውን በሰላም ከሰጡ የፍርድ ሂደታቸውን ህግ በሚፈቅደው አግባብ ሊያቀሉ እንደሚችሉ ለአሻማጋዮቹ ምክረ ሃሳብ ተሰንዝሯል።

“እናሸንፋለን። አዲስ አበባን በሳምንታት ውስጥ እንቆጣጠራለን” በሚል በሰው ማዕበል ወደ አፋርና አማራ ክልል የተመመው የትህነግ ሰራዊት ለመገለጽ በሚከብድ ደረጃ መደምሰሱ አመራሩን ከፍሎ እያሟገተ እንደሆነ፣ ትግራይ ውስጥ ያለው የተባባሰ የኑሮ ሁኔታ፣ በዚህ አካሄድ እስከመቼ የሚሉና አሁን መንግስት ሃይሉን አጠናክሮ በሁሉም አቅጣጫ ሙሉ ማጥቃት ሲጀመር ምን ሊከሰት እንደሚችል ከግምት ውስጥ በማስገባት ነው የዋስትና ጥያቄው የተነሳው።

የዜና ሰዎች እንዳሉት ሳማንታ ፖወር ያቀረቡት ጥሪ ምን አልባትም ከዚህ ጋር እንደሚያያዝ ይናገራሉ። ሴትየዋ የትህነግ ሃይል በወረራ ከያዛቸው የአማራና የአፋር ክልል ይዞታዎች ለቆ እንዲወጣና ለድርድር እንዲቀመጥ ያሰሙት ጥሪ የዚሁ የዋስትና ጥያቄው አካል እንደሆነ የሚጠቁሙት የዜናው ባለቤቶች፣ ሳማንታ ልክ እነ ጻድቃን የተሰማቸው ዓይነት ስሜት ውስጥ ስለመሆናቸው አይጠራጠሩም።

ትህነግ የአማራ ክልል በስፋት ወሮ በነበረበትና አፋር ክልልን አልፎ ሊወጣ በተቃረበበት ወቅት አሜሪካንም ሆነች ሲትየዋ ዝምታን መርጠው እንደነበር ይታወሳል። የትህነግ ሃይል ከተመታና ከተደመሰሰ፣ እንዲሁም ቀሪው ሃይል ተከቦ አማራጭ አላባ በሆነበት የመጨረሻው ሰዓት ላይ ብቅ ያሉት ሳማንታና አገራቸው አሜሪካ፣ በተመሳሳይ መንግስትን በዕርዳታ ገዳቢነትና ከልካይነት መክሰሳቸው “ድርድር” ያሉትን ጉዳይ በጫና ለማስፈጸም እንዲረዳ ታስቦ እንደሆነ ዜናውን የሰሙ እየገለጹ ነው።

በተመሳሳይ ዜና በትግራይ ውስጥ የሚካሄድ ጦርነት በሌለበት መንግስትን ዕርዳታ አስተጓጎለ በሚል የከሰሱት ሳምንታ አዲስ አበባ በመጡበት ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ስላላነገሯቸው ” የአሜሪካንን ክብር ነክተዋል” በሚል መናገራቸውን የዲፕሎማቲክ ምንጮች ተናግረዋል። የምስራቅ አፍሪቃ ልዩ መልዕክተኛው ፊልትስማን አዲስ አበባ ሲመጡ በተመሳሳይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቱርክ ማምራታቸው በአሜሪካኖች ዘንድ “የተናቅን” ስሜት እንዳሳደረ ከአሜሪካ ዲፕሎማቶች ጋር የተነጋገሩ ኢትዮጵያዊያን ለኢትዮ12 ተናግረዋል።

እነዚህ ወገኖች እንዳሉት አሜሪካ “ኢትዮጵያ ከጠላታችን ኢራን ድሮን ገዝታለች” ሲሉም ቅሬታ ማሰማታቸውን፣ ይግልጻሉ። አየርላንድ፣ ኢስቶኒያ፣ ፈረንሳይ፣ ኖርዌይ፣ ብሪታኒያ እና አሜሪካ የትግራይ ጉዳይ በጸጥታው ምክር ቤት በዝግ እንዲመከርበት በጠይቁት መሰረት የፊታችን ሃሙስ ይካሄዳል። አሜሪካ በተለያዩ ጉዳዮችና ” ክብሬ ተነካ” በሚል እንዳሻት የምትነዳውን የጸጥታውን ምክር ቤት በመጠቀም ኢትዮጵያ ላይ ጫና ለማሳደር ማሰቧን እኒሁ ለዲፕሎማቶቹ ቅርብ የሆኑ ወገኖች አመልክተዋል።

በሌላ ዜና በአማራ ክልል ክፉኛ እየተመታ ያለው የትህነግ ሃይል አባል የነነሩ ሁለት ተዋጊዎች አማራ ክልል አንድ አርሶ አደር ቤት መውለዳቸው ታውቋል። ነብሰጡር ሴቶችን እንዳዩ ያስታወቁት የአማራ ክልል አርሶ አደሮች ባዩት መገረማቸውን ምስክርነት የሰጡት በአማራ ቲቪ በኩል ነው። እነዚሁ አርሶ አደሮች አዋጊዎችን ማርከው ለልዩ ሃይል ማስረከባቸውንም አስታውቀዋል። ስም ግን አልጠቀሱም።

Filed in: Amharic