>

ብርጋዴን ጄኔራል ተስፋዬ ሀ/ ማርያም የህይወት ተሞክሮ...!!! (ኑሬ ረጋሳ )

ብርጋዴን ጄኔራል ተስፋዬ ሀ/ ማርያም የህይወት ተሞክሮ…!!!

ኑሬ ረጋሳ 
*… በእኔ ዘመን የጨለማ ዘመን ነዉ ማለት እችላለዉ

ብርጋዴን ጄኔራል ተስፋዮ ሀ/ማሪያም ተወልደዉ ያደጉት በጉራጌ ዞን በቸሀ ወረዳ 20 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘዉ ሲሰ መንደር ዉስጥ ነዉ፡፡
የጦር ሜዳ ዉሎ የተሰኘዉን መጽሀፍ አሳትመዉ ለንባብ ያበቁናለሀገሪቱ ትልቅ አሻራ ያኖሩ ጀግና ናቸዉ፡፡
ከአርሶአደር ቤተሰብ ነዉ የተወለድኩት ትምህርትም የጀመርኩት በወረቀትና በእርሳስ ሳይሆን የኮባ ቅጠል ቆርጬ በእሳት ለብ አድርጌ እንደ ወረቀት በመጠቀም የአጋም እሾህ ጫፍን በእሳት አቃጥዬ እንደ እርሳስ በመጠቀም ነዉ ሀሁ ፊደል የቆጠርኩት፡፡
ከዚህ ተነስቼ ነዉ ደረጃ በደረጃ በእምድብር ከተማ ዛሬ የለም ከቤተክርስቲያኑ በስተ ሰሜን አቅጣጫ አንድ ህንጻ ነበር በጣሊያን ጊዜ የተሰራ ሲሆን በዚህ ህንጻ ስር ነበር መጀመሪያ የተማርነዉ አንደኛ፣ ሁለተኛ ሶስተኛ ክፍል የሚባል ክፍል አልነበረም በአስተማሪዎች ብቻ ነበር የሚለየዉ እና እንደዚህ ሆነን ነዉ ፊደልን የቆጠርነዉ፡፡
ብርጋዴን ጄኔራል ተስፋዬ ሀ/ማሪያም በ19 46 አመተ ምህረት በእምድብር ከተማ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ከ6ኛ እስከ 8ኛ ክፍል የተማሩ ሲሆን በ1948 አመተ ምህረት የ8ኛ ክፍል ፈተና መፈተናቸዉ ነግረዉኛል፡፡
ከሰኞ እስከ አርብ በእምድብር ከተማ ትምህርት እየተከታተሉ ቅዳሜና እሁድን ቤተሰብ ጋ በማሳለፍ ሰኞ ከለሊቱ 11 ሰአት ተነስተዉ ለሳምንት ቀለብ የሚሆናቸዉ ተሸክመዉ 20 ኪሎ ሜትር በመጓዝ ትምህርታቸዉን ተከታትለዋል፡፡
ተፈትነዉ እንደጨረሱም በዛን ጊዜ በኢትዮጵያ 5 አዳሪ ትምህርት ቤቶች ማለትም ተፈሪ መኮንን ፣ዊንጌት ፣ምንሊክ ፣ቀዳማዊ ሀ/ስላሴ እና የአንቦ እርሻ ልማት ትምህርት ቤቶች ነበሩ ጄኔራል ተስፋዬ ሀብተማሪያምም አንቦ እርሻ ትምህርት ቤት ገብተዉ ተከታትለዋል፡፡
በእኔ ዘመን የጨለማ ዘመን ነዉ ማለት እችላለዉ ስለትምህርት የምናዉቀዉ ነገር የለም እኔ ተምሬ ምን እንደምሆንና ለምን እንደምማር አላዉቅም በዛን ጊዜ ብቻ በእኛ በተማሪዎች መካከል መንፈሳዊ ቅናት ነበር የአካባቢ ልጅ አንድ ነገር ሲሰራ እኔስ ለምን አልሰራም በሚል መንፈሳዊ ቅናት መሰረት በማድረግ ነዉ የምንማረዉ፡፡
ተምረህ ዶክተር ፣መሀንዲስ ፣ጠበቃ ፣ኢኮኖሚስት ትሆናለህ ብሎ የሚያስረዳህ ሰዉ የለም እንደዉም በዛን ወቅት ስሙም አይታወቅም እኛም ሰምተንም አናዉቅም እንድንማር ብቻ ያደረጉን የቤተሰብ ግፊትና መንፈሳዊ ቅናት ነዉ፡፡
እኔ የሙያና የዜግነት ግዴታዬን በሚገባ ተወጥቻለሁ ብዬ ነዉ የምናገረዉ ይህንን ሳላደረግ ቀረሁኝ የምለዉም ነገር የለም አቅሜ በፈቀደ መልኩ የሙያና የዜግነት ግዴታዬን ተወጥቻለሁ ነዉ የምለዉ፡፡
በሙያዬ ብዙ ቦታዎች ስልጠና ወስጃለሁ የአየር ወለድ ስልጠና ትምህርት እዚሁ ኢትዮጵያ ዉስጥ ነዉ የተማርኩት ፣ እስራኤል ሀገር የኮማንዶ ትምህርት ፣ አሜሪካ ሀገር ስፔሻል ፎርስ ፣ሶሻል ላይ ሞስኮ ሄጄ ተምሪያለሁ እንዲሁም ህንድም ሀገር ሄጄ ሙያዬን በስልጠና ያዳበርኩት፡፡
የስራ ሀላፊነቴ ትንሽ ጠንከር የሚል ሲሆን የኮማንዶ አባል መሆን የህይወት መሰዋትነት በግልም በቡድንም ነዉ ግዳጅ የምትወጣዉ ይህ ደግሞ የህይወት ዋጋ ያስከፍላል ።
ለምሳሌ በኢትዮጵያና በሱማሊያ መካከል ከፍተኛ የሆነ ግጭት እንዲሁም ከሱዳንም ጋር በነበረዉ ግጭት በዲፕሎማሲ ለመፍታት ብዙ ተሞከረ 1969 አመተ ምህረት ላይ ነገር ግን ችግሩን ለመፍታት ብዙ ጥረት ተደርጎ መፍታት አልተቻለም፡፡
መፍትሄ ሊሆን የሚችለዉ ቲት ፎር ታት መሆን አለበት የሚል አቋም ይዘን ወደ መፍትሄዉ ገባን እነሱ ደግሞ ከጅግጅጋ ለጋፍር እስከ ጎዴ ድረስ እንደዉም አልፈዉ መጥተዉ እስከ ሜኢሶ ድረስ ያለዉ በፈንጅ አጥረዉት ነበር፡፡
ይህ መሰናከል ለሰራዊቱ እና ለህዝቡ መሰረታዊ የሆኑ ነገሮች ለማቅረብ በጣም ችግር ተፈጠረ አማራጩ አንድ ነገር ብቻ ነዉ ይህዉም የእነሱ ግዛት ክልል ዉስጥ ዘልቆ በመግባት እና ፈንጅ የመቅበር ስራ ግዳጁ ለእኔ ተሰጠኝ እኔ የምመራዉ ቡድን ድንበር አቋርጠን ሶስት ቀን ሌሊትም በመጓዝ ገብተን ከስር ወደዚህ ፈንጅ እየቀበርን መጣን በቀበርነዉ ፈንጅ ብዙ ሰዎች ተጎዱ ብዙ ንብረትም ወደመ ያኔ ወደሰላም መጡ ይህ ትልቅ ዉጤት ነዉ፡፡
ሌላዉ ትልቁ ችግር የነበረዉ ከኤርትራ ጋር በነበረዉ ግጭት ሱዳን ከፍተኛ ወታደራዊ ፣ ኢኮኖሚያዊ እና የፖለቲካዊ ድጋፍ ታደርግ ነበር ይህንንም በዲፕሎማሲ መንገድ ድርድር ተጀመረ ብዙ ተሞክሯል ግን አልተቻለም ነገር ግን ደቡብ ሱዳን መገንጠል እንደምትፈልግ በማወቅ እና እርዳታ እንደሚያስፈልጋት ፍንጭ በመረዳት ከዛ ስደተኛ ሆነዉ የመጡትን የመጀመሪያዉ መሪ ዶ/ር ጆን ጋራን የሚባል ነበር ዛሬ ላይ ያለዉን የደቡብ ሱዳን መንግስት በሁለት እግሩ እንዲቆም የደረኩት እኔ ነኝ ማለት እችላለዉ፡፡
የኢትዩጵያ አየር መንገድ በጠለፋ በጣም ከፍተኛ ችግር ገጥሞ ስለነበረ አንዳንድ ቦታዎች ላይ በረራ ያቆሙበት ሂደት ነበር ለሰራተኘ እንኳን ደሞዝ መክፈል ያልተቻለበት ሁኔታ ነበር እና የበረራ ደህንነት እንዲቋቋም መንግስት ሲወስን የዛን ደህንነት አባላትና አሰልጣኞች አብሮ እንዲጓዙ ያቋቋምኩት እኔ ነኝ፡፡
ለራስ ህይወት መሰረቱ ስነ- ስርአት ነዉ የሚሉት ብርጋዴን ጄኔራል ተስፋዬ ሀ/ማሪያም በኢትዮጵያ ምድር ዉስጥ ጥይት በሚፈነዳበት ቦታ ሁሉ እኔ ያልተሳተፍኩበት በጣም ጥቂት ሲሆን አብዛኛዉ በተሳተፍኩባቸዉ ቦታዎች በድል ወይም በስኬት ነዉ የተጠናቀቁት፡፡
በግልም በቡድንም የምሰራዉ ነገር አለ የመራሁትም ሰራዊት ዉጤታማ ነዉ ብለዉ የአየር ወለድ ጦር አዛዥ ነበርኩ የአየር ወለድ ጦር ግዳጅ በጣም ከባድ ነዉ እና ናቅፋ ላይ የተደረገዉ ዝላይ በአለም ላይ ተደርጎ ያልታወቀ እስካሁን ድረስ ያልተደረገና ወደ ፊት ሊደረግ ይችል ይሆናል ፡፡
አንድ ጦር 6 ወር በጠላት ተከቦ ሰርቫይቭ ያደረገ በአለምም የለም የኛ ሰራዊት ግን 6 ወር ድረስ ሲታገል ቆይቶ ሰብሮ በህይወት የወጣ ታሪካዊ የአየር ወለድ ሰራዊት ነዉ፡፡እንደዚህ አይነት ነገሮች ናቸዉ ልዩ የሚያደርገኝ፡፡
ማንም ሰዉ ብቁ አሰልጣኝ ካገኝ አየር ወለድ መሆን ይችላል እኔ መጀመሪያ ላይ የአየር ወለድ ስልጠና እስራኤሎች ናቸዉ ያሰለጠኑኝ በዛን ጊዜ ደግሞ በአየር ወለድ ጥሩ ስልጠና በመስጠት ይታወቃሉ የእኛ ሰራዊትም የሰለጠነዉ ከእስራኤሎች ነዉ፡፡
እኔ ተመርቄ የወጣሁት ማሰልጠኛ ማዕከል ሀረር ጦር ሚሊተሪ ተቋም ነዉ፡፡
በአለም ላይ አራት ታዋቂ ማሰልጠኛ ተቋም አሉ እነዚህም የእንግሊዙ ሳንድረስት ፣የአሜሪካዉ ዌስት ፖስት ፣የፈረንሳይ ሳንሰን እና የህንዱ ናሽናል አካዳሚ አሉ ሀረር ማሰልጠኛ ተቋምም በወቅቱ ከነዚህ የሚወዳደር ነበር በዚህ ተቋም 3 አመት ህንዶች ናቸዉ ያሰለጠኑን ፡፡
(ወድ አንባብያን የኚእህ ታላቅ ሰዉ የህይወት ተሞክሮን ከብዙ በጥቂቱ ነዉ የጻፍኩት…. )
Filed in: Amharic