>

መንግስትና ሸኔ ተናበው ፤ ኔትዎርክ ተዘግቶ ሚድያዎች ታፍነው ፣ የሚፈጸም የዘር ፍጅት...!!! (አበረ ካሳሁን)


መንግስትና ሸኔ ተናበው ፤ ኔትዎርክ ተዘግቶ ሚድያዎች ታፍነው ፣  የሚፈጸም የዘር ፍጅት…!!!

አበረ ካሳሁንባለፈው ሳምንት አሸባሪዋ ህወሓት በአፋር ክልል ውስጥ ህፃናትን ጨምሮ 200 አፋሮችን ገደለች። ዓለምም ተንጫጫ። ባንዲራም ዝቅ አለ። የክልል መንግሥታትም፣ ሃገር በቀል ፓርቲዎችም ግድያውን አወገዙ። እኛም አወገዝን። ኢቲቪም፣ ኦቢኤንም፣ ኢሳትም፣ ቢቢሲ አማርኛም ዘገቡት፣ አልጀዚራማ ድንኳን ሁሉ ጥሎ ነው እዬዬ ያለው።
በዚያው ሳምንት በምዕራብ ወለጋ ውስጥ #ከ300 በላይ አማሮች በአሸባሪው ኦነግ ታረዱ፣ ተቀሉ፣ ተገደሉም። ካህናትና ምእመናንም ተገደሉ። ነገር ግን ድርጊቱን ያወገዘ የለም። መንግሥት ጭራሽ ዜናው እንዳይወጣ አፈነው። ኔትወርክ አጠፋ። የሃገር ውስጦቹም። የሞተው፣ የተገደለውም ዐማራ ስለሆነ ባንዲራ ዝቅ አላለም። እነ ኢቲቪም፣ እነ ኦቢኤንም ትንፍሽ አላሉም። ዘሩ የሚጠፋው ዐማራ ስለሆነ ነው የተባለም ይመስላል።
የሀገሪቱ መሪ ዐቢይ አሕመድ #የአማራን ሞት እንደ ልማት እያዬው ይመስላል። ፓስተሮችም በወለጋ በኦነግ ከሚታረዱት ዐማሮች ይልቅ በአፍጋኒስታን በታሊባን ሞት ተፈረደባቸው ለተባሉ 200 ምዕራባውያን ዓለም አቀፍ የጸሎት ዐዋጅ ሲያውጁ ይታያል።
የአማራ የሆነ እንኳን ሰዉ ከብቱም በህወሓት መገደሉ አልቀረለትም። ይህንን የሱዳን ወረራና የህወሓት ጭፍጨፋ የዐቢይ አሕመድ ካድሬ አክቲቪስቶችም እየዘገቡት ነው። አክቲቪስቶቹም ሆነ ጋዜጠኞቹ ግን ለዐማራ አዝነው ሳይሆን ወያኔ ጎንደርን አልፋ ጎጃም ከገባች፣ ወሎን አልፋም ሸዋ ከገባች ለብልጽግናው መንግሥታቸው ስለምታሰጋ ነው።
በምሥራቅ ወለጋ ነቀምት ዞን ኪሩሙ ወረዳ ቂልጡ ዞን አቦ አሹ ኩየሳና በመርጋ ጂሬኛ ሰፍሮ የነበረው የኦሮሚያ ልዩ ኃይል ከላይ በመጣ ትእዛዝ ነሐሴ 11/2013 ዓም አካባቢውን ለቅቆ እንዲወጣ ይደረጋል። የኦሮሞ ልዩ ኃይል ከአካባቢው በወጣ ማግሥት ጀምሮ ከነሐሴ 12 -14 ድረስ ብቻ ከቂልጡ አቦ ልዩ ቦታው ጨፌ ሚካኤል እስከ  ለኮ ኪዳነ ምህረት ድረስ የሚኖሩ በቁጥር 249 ዐማራዎች በሁለት ቀን ውስጥ ተጨፍጭፈዋል።
ሲረዶሮ በቀበሌ 01 የሚኖሩ ዐማራዎችን ” የኦነግ ሠራዊት መንግሥት የለም አሁን ሀገር የማስተዳድረው መንግሥት እኔ ነኝ” በማለት ህዝቡን ሁሉ ስብሰባ በመጥራት ለስብሰባ የወጡትን በቁጥር 60 የሚሆኑ ወንድና ሴት ዐማራዎችን በጥይት ደብድቦ፣ በስለትም አርዶ ገድሏል።
በተመሳሳይ ቦታ ላይ ነሐሴ 12/2013 ዓም የቅዱስ ሚካኤልን በዓል ለማክበር የተሰበሰቡ በቁጥር 27 ኦርቶዶከሳውያን ካህናትና ምእመናን ዐማራዎችን በሚዘገንን ሁናቴ አርደዋቸዋል።
ከሲረዶሮ ወደ አጎራባች ቀበሌ በመሸሽ ጎራ በተባለ ቦታ አግተው ያዟቸውን 100 አረጋውያን #የዐማራ ነገድ አባላት የሆኑ እናቶች እና ህፃናትን ጭምር በአሰቃቂ ሁኔታ ገድለዋል።
በዚሁ ቀበሌ ወይናዱ በተባለ ቦታ አንድ አንድ ዓይነ ስውርን የሆነ ማየት የተሳነው ዐማራ በእሳት ሲያቃጥሉ ያዩና እሱን ለማውጣት ወደ እሳቱ የገቡ 3 ሰዎችን በጥይት ደብድበው ገድለዋል።
በአሱኩሳየ አንድ የ80 ዓመት ዕድሜ ባለፀጋ አዛውንት ከጠባቂያቸው 2 ህፃናት ጋር በአሰቃቂ ሁኔታ ሲታረዱ በዚሁ ቦታ 30 ዐማራዎች በጥይትና በስለት  ተገድለዋል።
በቂልጡ አቦ ቀበሌ የሟቾች ቁጥር እስከ አሁን ድረስ ያልታወቀ ሲሆን በዚሁ ቦታ ቤተ ክርስቲያን ወድሞ ካህናትም ታርደዋል። ይህ ሁሉ የሆነው ነሐሴ 12/2013 ዓም ነው በማግስቱ እንዲሁም በወለጋ  ኪረሞ በነሐሴ 13/2013 ዓም 55 ዐማራዎች  ተጨፈጨፉ  የኦሮሚያ መንግስት ዝም አብይም ዝም ባለስልጣናት በሙሉ ዝም ይህ ማለት አቀናባሪዎቹ እነሱ ናቸው ።
Filed in: Amharic