>

"ይህ ግድያ የሚቆመው ከአማራ የጸዳች ኦሮምያ ስትፈጠር ነው..."ብላችሁ ቁርጡን ንገሩን!!! (መስከረም አበራ)

“ይህ ግድያ የሚቆመው ከአማራ የጸዳች ኦሮምያ ስትፈጠር ነው…”ብላችሁ ቁርጡን ንገሩን!!!
መስከረም አበራ

ሰሞኑን በወለጋ ምድር 300 አማሮች በኦነግ ተገድለዋል። የወያኔን-ኦነግ ጥምረት ያስፈለገው አማራው ‘ክልልህ ነው’ በተባለለትም ‘መጤ’ በተባለበትም ምድር ሁሉ ሳይሞት እንዳያድር  ነው! ወለጋ (ምናልባትም ሙሉ የኦሮሚያ) አማራ “free zone” እስከምትሆን ግድያው ይቀጥላል። ይህ ዛሬ የተጀመረ ነገር አይደለም በሶስት አመት የኖርንበት ልማድ እንጅ….
የአማሮች ነፍስ ከአፈር ደማቸው ከእጅ እጣቢ ውሃ በረከሰበት ወለጋ በተባለ የሞት ምድር አማሮች የሚጎነጩት መራራ የሞት ፅዋ ለማንም ምኑም አይደለም። በዚህ ጉዳይ ላይ የተለያዩ የፖለቲካ ኃይሎች ያላቸውን አቋም በጥቂቱ ለማየት ቢሞከር
 * ወለጋን የሚያስተዳድረው ብልፅግና ፓርቲ የአማሮች ከአካባቢው መፅዳት ከኦነግ ጋር በፈገግታ የሚተያይበ መግባቢያ ቋንቋው ነው።
* የአማራ ወኪል ነኝ የሚለው የአማራ ብልፅግና ደግሞ እንኳን ዛሬ ያልተዘጋጀበትን የጦርነት  በሚመራበት ቀውጢ የውጥረት ጊዜ ቀርቶ ያኔ በሰላሙ ጊዜም ገና ለገና ደሃ አማራ በድሽቃ  ሞተ ብሎ ከዋናው ተቆጣጣሪ የኦሮሞ ብልፅግና ጋር የሚቀያየምበት ምክንያት የሌለው “ብልህ” ፓርቲ ነው።
* ህብረ-ብሄራዊ ነን ባይ ተቃዋሚ ፓርቲዎችም (ከባልደራስ በቀር) በማንነቱ ስለሚገደለው አማራ ስሙን ጠቅሶ ነገሩ እንዲቆም መስራት አንድም ከኢትዮጵያዊነት ከፍታ የሚያወርዳቸው ሁለትም ከመንግስት ጋር የሚያቀያይማቸው ሶስትም አማራ ከሚባለው ህዝብ ጋር የተለየ የፍቅር እንደሌላቸው የሚያስመሰክሩቀት ነውና ምንም ሊሉ አይችሉም።
* የመንግስት ተከፋይ አክቲቪስቶች እና ሚዲያዎች ደግሞ በወለጋ ኦነግ የሚገድለው አማራ ጉዳይ የአልባሽ አጉራሻቸውን መንግስት ወንበር የመነቅነቅ ጉልበት ስለሌለው በዚህ ላይ የሚያጠፉት ጉልበት አይኖርም። ይልቅስ ወያኔ ስለሚገድለው አማራ ማውራቱ ወያኔ የመንግስትን ስልጣን ለመነቅነቅ የምታደርገውን ሩጫ ለመግታት ስለሚጠቅም በወለጋ ከሚረግፈው የንፁሃን አማሮች ነፍስ ይልቅ በወያኔ ስለተሰረቀው የአማራ  አብሲት ማውራቱ የበለጠ አስፈላጊና አንገብጋቢ ጉዳያቸው ነው፨
 * ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተቋማት ደግሞ ለአማራው ሞት  “Less Human”  ናቸው።  በሃገር ውስጥ ማንም ነገሬ ብሎ ያልያዘውን ጉዳይ እነሱ ይንገበገቡበት ዘንድ አይጠበቅም ፤ ባለቤት ያቀለለውን ማን ይቀበለዋል?????
ስለዚህ በወለጋ አዘቦት የሆነው የአማሮች ሞት የሟች እና የቤተሰቡ ጉዳይ ብቻ ሆኖ ይቀጥላል፣በዚህ መንገድ የቀጠለ ሃገር  ይኖር ይሆን????……
Filed in: Amharic