>

‹የጸጥታው ምክር ቤት የትግራይን ጉዳይ አያለሁ ማለቱ ለአሸባሪው ህወሓት ከለላ ለመስጠት ነው›› (ፕሮፌሰር አደም ካሚል የታሪክ ተመራማሪ)

‹‹የጸጥታው ምክር ቤት የትግራይን ጉዳይ አያለሁ ማለቱ ለአሸባሪው ህወሓት ከለላ ለመስጠት ነው›
ፕሮፌሰር አደም ካሚል የታሪክ ተመራማሪ



(ኢ ፕ ድ)
የተባበሩት መንግሥታት የጸጥታው ምክርቤት የአንድን አገር የውስጥ ጉዳይ ማየት ባይችልም የትግራይን ጉዳይ አያለሁ ማለቱ ለአሸባሪውን ህወሓት ከለላ ለመስጠት የተሰላ ሴራ እንደሆነ የታሪክ ተመራ ማሪው ፕሮፌሰር አደም ካሚል አስታወቁ።

ፕሮፌሰር አደም የተባበሩት መንግሥታት የጸጥታው ምክርቤት የትግራይን ጉዳይ ለማየት የጠራውን ስብሰባ አስመልክተው በተለይም ለአዲስ ዘመን እንዳስታወቁት፤ የጸጥታው ምክር ቤት ማየት ያለበት የዓለምን ጸጥታና ደህንነት ችግር ላይ የሚጥል ጉዳይን እንጂ የአንድን አገር የውስጥ ጉዳይ አይደለም።

አስከአሁን ምክር ቤቱ በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ለመምከር ለስምንተኛ ጊዜ ቀጠሮ መያዙን ያመለከቱት ፕሮፌሰር አደም፣ ይህ የሆነውም በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ግፍ ሲፈጽም ለቆየው አሸባሪው ህውሓት ከለላ ለመስጠት እንደሆነ ጠቁመዋል።

ኢትዮጵያ ሌሎች ከችግሮቻቸው ከመታደግ ውጪ በማንም ጉዳይ ጣልቃ ገብታ እንደማታውቅ ያስታወቁት ፕሮፌሰር አደም፣ ለዚህም ደግሞ ሱዳንን በሰላም አስከ ባሪ ኃይል መደገፏና እንድትረጋጋ ማድረጓን አመልክተ ዋል።

ጥቁር የተባለ ሁሉ ነፃነቱን እንዲያገኝና ከቀኝ ግዛት እንዲወጣ አድርጋለችም። ይህንን የሠራች አገር ደግሞ በምንም ተአምር ሰውን ልትጎዳ አትችልም። ማንም ሊወነጅላትም አይችልም። ስለሆነም የተባበሩት መንግሥታት የጸጥታው ምክርቤት የትግራይን ጉዳይ አያለሁ ብሎ መነሳቱ አግባብነት እንደሌለው አስታውቀዋል።
https://www.press.et/ama/?p=54425

Filed in: Amharic