>

ቻይና  አሜሪካንን ወረፈች...!!! ደጀኔ አሰፋ

ቻይና  አሜሪካንን ወረፈች…!!!
ደጀኔ አሰፋ

አሜሪካ በአፍጋኒስታን ውስጥ የፈፀመችው ግፍ እና ሰቆቃ ይታወቃል!!!! ያም ሆኖ ግን አሜሪካ በታሊባን ተሽንፋ በታላቅ ውርደት ከአፍጋኒስታን ተባራለች!!!!
ይህን ተከትሎም በዛሬው ዕለት በቻይና ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር የኮምኒኬሽን ዲፓርትመንት ቃልአቀባይ የሆኑት ሊጃን ዝሆ፣  አሜሪካ በአፍጋኒስታን ለአመታት የፈፀመቻቸውን ኢሰብአዊ ሰቆቃዎች እና ግድያዎችን በአሃዝ በመዘርዘር ካጋለጡ በኃላ አሜሪካንን በግልፅ ወርፈዋል!!!! ቃልአቀባዩ ይህን ብለዋል
አሜሪካ በአፍጋኒስታን ውስጥ
– ከ 10 ሚሊዮን በላይ ዜጎችን ስደተኛ አድርጋለች
– ከ 20 በላይ አሸባሪ ድርጅቶች እንዲፈጠሩ አድርጋለች
– ከ 1600 በላይ ህፃናት በኔቶ መራሹ የአየር ጥቃት እንዲገደሉ አድርጋለች
– ከ 174,000 በላይ አፍጋኖችን (70,000 የአፍጋን ወታደሮችና ፖሊሶች እና ከ 47,000 በላይ ንፁሃን) ተገድለዋል:: ካሉ በኃላ….
ታዲያ ይህን ሁሉ ወንጀሎች ከፈፀመች በኃላ፣ አሉ የቻይናው ቃለ አቀባይ ሚስተር ሊጃን፣
“ታዲያ ይህን ሁሉ ወንጀሎች ከፈፀመች በኃላ አሜሪካ በደም የተጨማለቀ እጇን በጥቂት ጠርሙሶች ውሃ ሁሉንም ኃጢአቶች ታጥባ መሄድ ያምራታል?? በይ ከእንግዲህ #የሰብአዊ መብት እያልሽ የምትነዥውን ፕሮፓጋንዳሽን አቁሚ፣ ዓለም ከእንግዲህ አይገዛውም!!!” በማለት “ለማያውቁሽ ታጠኝ” አይነት መልዕክትን እጅግ ግልፅ በሆነ ሁኔታ ቻይና የአሜሪካንን አስመሳይነት የቻይናው ቃልአቀባይ ኮንነዋል!!!! ከዚህ ወዲያ አሜሪካ የሰብዓዊ መብት እያለች የምትጠቀምበትን የአስመሳይ የፖለቲካ ቋንቋዋን እንድታቆም ቻይና አስጠንቅቃለች!!!! “Just STOP your #humanrights propaganda, the world won’t buy it anymore!” ብለዋታል!!!!!
ሃያሏ ቻይና ለአመታት ድምጿን አጥፍታ ከሰራች እና እድገቷን እና ምጥቀቷን ካረጋገጠች በኃላ አሜሪካንን ከመወረፍ አልፋ ማስጠንቀቅ ከጀመረች ወራቶች ተቆጥረዋል!!!! አሜሪካ በአንፃሩ የዓለም ወራዳ ሃገር ለመሆን ቁልቁለቷን አጋምሳለች!!!! በየአቅጣጫው ውርደቷን እየጠጣች እንደ ፀጉራም ውሻ አለ ሲሏት ጥርስ አልባ ልትሆን ጥቂት የቀራት ይመስላል!!!! በታሊባን የደረሰባት እጅግ አሳፋሪ ሽንፈት ዓይነተኛ ማሳያ ነው!!! በዚያ ላይ ቻይና እና ራሽያንን ማስቆም ቀርቶ ጠንካራ ምላሽ መስጠት እንኳን የማትችል ሆና የዳገት ያህል ከብዷት ሰንብታለች!!!! አሁን የአሜሪካ ጉልበት እና ድንፋታ ምናልባት ባላደጉ ሃገራት ላይ እንጅ በቻይና ራሽያ ቱርክ እና መሰል ሃገራት ላይ እምባዛም ከሆነ ትንሽ ቆየ!!!! ጊዜው በፍጥነት እየተቀየረ ነው!!!! ቻይና በመጭዎቹ አጭር ጊዜያት የልዕለ ኃያልነቱን መንበረ ስልጣን ትረከባታለች!!!!! ራሽያ የቻይና ሁነኛ አጋር መሆኗ ደግሞ ጊዜውን ያሳጥረዋል!!!!! ከአሸናፊ ወገን ያድርገን!!!! እንዲህም እንዲያም ብሎ ያሻግረን
Filed in: Amharic