>

ኢትዮጵያ አሸነፈች,,,(ኤርምያስ ቶኩማ)

ኢትዮጵያ አሸነፈች,,,,,

    
ኤርምያስ ቶኩማ


ወዳጆቼ ዛሬ አንጀቴ ቅቤ ነው የጠጣው!!! ህወሃትን ወደስልጣን መልሰው ኢትዮጵያን መዝረፍ ይፈልጉ የነበሩ ኢምፔሪያሊስቶቹ አሜሪካና እንግሊዝ አንገታቸውን ደፍተዋል፤ የጭቁኖች መከታ ራሺያና ቻይና ለኢትዮጵያ ተሟግተዋል፤ ኬንያና ህንድም ከኢትዮጵያ መንግስት ጎን ነን ብለዋል። ስብሰባውን ቀንጨብ ሳደርገው እንዲህ ነበረ

ራሺያ ምን አለች መሰላቹህ

ሰኔ ላይ በዴሞክራሲያዊ መንገደድ የተመረጠና አቅም ያለው መንግስት በኢትዮጵያ ስላለ ችግሩን ራሳቸው ኢትዮጵያውያን ይፈቱታል ብላለች። በተጨማሪም ህወሃት አፋርና አማራ ላይ ስላደረሰው ግፍ ተናግራለች።

ቻይና ደግሞ እንዲህ አለች

“በሰብአዊ እርዳታ ስም እርዳታ ሰጪዎች የኢትዮጵያ ሉዓላዊነት ላለማክበር መሞከርን ቻይና በፍፁም አትቀበለውም። የአለም ሀገራት በሙሉ ከኢትዮጵያ መንግስት ጎን ሊሆኑ ይገባል፤ ኢትዮጵያ ችግሯን ለመፍታት ራሷ በቂ ነች፤ በእርዳታ ስም ችግር ለመፍጠር የሚሞክሩ ቡድኖች የተመድን ህግ ሊያከብሩ ይገባል፤ ከኢትዮጵያ መንግስት ጎን ነን።”

ህንድም እንዲህ ብላለች

“የኢትዮጵያ መንግስት የተኩስ አቁም ፈፅሞ ህወሃት አፋርና አማራ ክልል ላይ ወረራ መፈፀሙ ችግር ፈጥሯል። የኢትዮጵያ መንግስት ችግሩን ለመፍታት የሚያደርገውን ጥረት እንደግፋለን። ችግሩን ለመፍታት የኢትዮጵያ መንግስት በቂ ነው።”

ኬንያ ቀጥላ እንዲህ አለች

“የኢትዮጵያ ችግር የብሄር ፖለቲካ ነው፤ የዚህ ጠንሳሽ ደግሞ ህወሃት ነው። ኢትዮጵያ ላይ የሚጣልን ምንም አይነት ማዕቀብ አንደግፍም”

በመጨረሻም የሀገራችን ልጅ አምባሳደር ታዬ እንዲህ አሉልሃ

ሀገሬ ነገሽን ልወስንልሽ የሚሏትን በሙሉ አትቀበልም

ወዳጆች እነአሜሪካ ዶክተር አብይ አሻንጉሊት ሊሆንልን አልቻለም ብለው ሀገሬን ለመበታተንና ስብሰባ ሲጠሩ ይህቺ ታላቅ ሀገር ግን ምንም ሳይኖራት በስብሰባው አሜሪካና እንግሊዝን አንገት አስደፍታ ወጥታለች። ተዓምር ነው። የራሺያ፣ የቻይናና የህንድን ውለታ የአሜሪካና የእንግሊዝን ክፋት ለዘመናት አንረሳውም።

Filed in: Amharic