>

ያየነውን እንመሰክራለን የሰማነውን እንናገራለን...!!! '' (አብርሃም በላይ)

ያየነውን እንመሰክራለን የሰማነውን እንናገራለን…!!! 

አብርሃም በላይ


  ያሉ ችግሮችንም ሳናጰለቋቁስ እናሳውቃለን አዎ መቄት ሰሜን ወሎ ችግር ላይ ነው ።**

የሰሜን ወሎ ህዝብ ጽንፈኛውና ሰይጣናዊ ዓላማን አንግቦ ከ30 ዓመታት በላይ በምድረ-ኢትዮጵያ እንደአሻው ሲናኝ የቆየው የአሸባሪው ህወሃት ቡድን  እኩይ ተግባሩን  አርግዞ ይህንኑ እኩይ ተግባሩን ወልዶ ለመሳም ሲል ውርደትን እና የሀገር ክህደትን ከፈጸመባት ወርሃ-ጥቅምት አንስቶ ህዝቡ እንደ ህዝብ የጸጥታ መዋቅራችንም እንደ ጸጥታ መዋቅር  አመራሩም እንደ አመራር ሁሉም በየመክሊቱ ውዷን ህይዎቱን ጨምሮ  መክፈል ያለበትን መስዋዕትነት ሁሉ እየከፈለ ከቆየ ድፍን 10 ወራትን ሞልቷል ።  ይህችን የትላንትናዋን አነሳን እንጂ ቀደም ሲልም ቢሆን ህወሃት መንበረ-ስልጣኑን ከጨበጠበት ክፉ ዘመናት  አንስቶ በኢትዮጵያ ምድር የደረሱ ግፍና ሰቆቃዎች ሁሉ    ሰሜን ጎንደር የመተማና ቋራ   የታች አርማጭሆ የወልቃይትና የሁመራ ህዝብ ሰቆቃ ካልበለጠ በስተቀር እንደ ሰሜን ወሎ የተጎዳ አካባቢ የለም ። ታዲያ ይህ ህዝብ አሁንም ቢሆን ህወሃት ሂሳቤን አወራርዳለሁ ብሎ እንደዛተ እንዳይቀር ያለ የሌለ አቅሙን ተጠቅሞ ሂሳቡን ለማወራረድ ሲጥርበት ይሰትዋላል ። እርግጥ ነው በክልላችን ህዝብ ልዩ ሃይልና የመከላከያ ሠራዊታችን በርካታ መስዋዕትነት የተገኙ ድሎችን አልክድም ዳሩ ግን አሁንም ይህንን ህዝብ ልንደርስለት አልቻልንም ። ለአብነት ያህል እኔ አሁን የምገኝበት የመቄት ወረዳ ህዝብ ከፍተኛ የሆነ ችግር ውስጥ ገብቷል ።
አርሶ አደሩ ነጋዴው የመንግስት ሠራተኛው ከመደበኛ ስራው ወጥቶ ራስን ወደ መከላከል ወደ ጫካ ገብቷል ( ቤቱ ንብረቱ ልጆቹ ተበትነዋል )
የሰብል ማሳዎች በሰብል አልተሸፈኑም ቢሸፈኑም በወጉ አልታረሙም።
ሴቶችና ህጻናት  የሞቀ ቤታቸውን ለቀው መኖሪያቸውን መካነ-መቃብርና ዋሻ ካደረጉ ዋል አደር ብለዋል ርሃብና ውሃ-ጥም አልቻል ብሏቸው ወደ ቀያቸው የተመለሱ በታጣቂ ቡድኑ እንግልትና ዘረፋ እየተሰቃዩ ነው ።
የህክምና ተቋማት በመዘጋታቸው የህክምና አገልግሎትም ባለመኖሩ ታክሞ መዳን አልተቻለም ።
ሟቾችን አልቅሶ መቅበር አልተቻለም ።
መብራትና ውሃ ኔትወርክ ባለመኖሩ ደካማዎች ወፎጮ አስፈጭተው መመገብ አልቻሉም ።
ለክረምት የተዘጋጀው የቤት አስቤዛ( እንደ ዱቄት በርበሬና ሽሮ ) የተቦካውን ሊጥ ሳይቀር ተዘርፈዋል።
ለዘመናት ያከማቸውን ሃብትና ንብረት እየዘረፉት ይገኛሉ
ትልልቅ ተቋማት የጁንታው መካነ-መቃብር ሆነዋል።
በአጠቃላይ ለመቄት እና አካባቢው ብሎም ለሰሜን ወሎ  የተናበበ የተቀናጄና ከዕለት ጥቅሙ ይልቅ ሀገራዊ ክብሩ የሚያሳስበው ቆራጥና ጀግና ትዕዛዝ ሰጭና  ትዕዛዝ ተቀባይ የደህንነትና የጸጥታ መዋቅር ሊደርስለት ይገባል ።
ከጦርነት አንጻር አካባቢው ያለበት ሁኔታ የጠላት ጦር ከመቄት ወረዳ ደብረ-ዘቢጥ አፋፍ  ላይ ከባድ መሳሪያ ጭምር አጥምደው ከወደ ጋይንት በኩል መጥቶ ጨጨሆ አካባቢ የሰፈረውን የወገን ጦር እየተጠባበቀ ነው ።
የመከላከያ ሃይላችን እና ልዩ ሃይላችን ከተለያዩ አካላት የሚሰጡ መረጃዎችን በመጠቀም ከወደ ዋድላ ደላንታ ወልዲያ በኩል መጥተው ከጨጨሆው ጦር ጋር ተናቦ ይህንን ሊጥ ሽሮና ዱቄት ተሸካሚ ስግብግብ ጁንታ  የዶግ-አመድ ካላዳረግነው እኔ በማውቀው ልክ ከደ/ዘቢጥ እስከ ጋሸና ከዛም አልፎ ጠላት ወሮናል ።
ያለን ተስፋ የወረዳችን ህዝብ ስግብግቡን ጁንታ ለመፋለም ባለው ቁርጠኛ አቋም በርካታዎቹን እንደ ቅጠል እያረገፈ በምትኩ ክላሾችን በመታጠቅና ወገኖቹን በማስታጠቅ ላይ ስለሆነ  ለልዩ ሃይላችና ለመከላከያ ሰራዊታችን ደጀንነቱን እያሳየ ነው በዚህም ህዝብ ያልደገፈው ሰራዊት መጨረሻው መሸነፍ ነውና  አሸናፊ መሆናችን አይቀርም ።
ስግብግቡ ጁንታ በሀገራችን ህዝብና በዓለም መንግስታት ( ከሴረኛዋ አሜሪካ ውጭ ) እየተጠላና እየተናቀ ስለመጣ የውጭ ግንኙነታችንም የተሻለ እየሆነ ስለመጣ እናሸንፋለን ።
በመጨረሻም አሁን ላይ የወረዳችን መቄት የዞናችን ሰሜን ወሎ የክልላችን ህዝብ በኢኮኖሚውም ሆነ  በማህበራዊ ጉዳዮቹ ላይ እየደረሰበት ያለ ግፍና ሰቆቃ እየከፋ መጥቷልና   ጉዳዩን ከማበለቋቆስ ወጥተን ችግር ውስጥ መሆናችንንም በአደባባይ በማውጣት ከዚህ አስከፊ ሁነቶች እንውጣ

ተጻፈ ሃምሌ 20/2013 መቄት -ፍላቂት

Filed in: Amharic