>

የዐማራ ብልግና አመራሮች 30 መት የካዱት ወሎ ህዝብ ሰቆቃ ለማን ይነገራል??? (ወንድወሰን ተክሉ)

የዐማራ ብልግና አመራሮች 30 መት የካዱት ወሎ ህዝብ ሰቆቃ ለማን ይነገራል???

(ወንድወሰን ተክሉ)

የወሎ ህዝብ የ30 ዓመት ቅኝ ግዛት እስከመቼ ይቀጥላል??
የብአዴን ግፎች በወሎ ህዝብ ላይ
– መሰረታዊ ልማት እንዳያገኝ ተደርጓል
– በዳስ ት/ቤቶች እንዲማር ተደርጓል
– ወንበር በሌለው በፈራረሰ የእንጨት ት/ቤት ተማሪዎች በድጋይ ላይ ተቀምጠው እንዲማሩ ተደርገዋል
– የዋግ ኽምራና የላሊ በላ ህዝብ የአስፓልት መንገድ እንዳይኖረው ተደርጓል
– ከአዲስ አበባ ወደ መቀሌ የሚወስደው የአስፓልት መንገድና ከወልድያ ባህር ዳር ከሚወስደው የአስፓልት መንገድ ውጭ ያሉ የቀበሌና የወረዳ መንገዶች የፒስታ መንገዶች ናቸው
– የወሎ ህዝብ መሳሪያ እንዳይታጠቅ በማድረግ ህዝቡ ተፈጥሯዊ እራስን መከላከል እንዳያደርግ ተደርጓል
– የመከላከያ ሰራዊቱና የዐማራ ልዩ ሀይል ያለምንም ጦርነት ወደ ዋጃ እንዲሸሺ ሲገረግ የዐማራ አመራሮች ተባባሪ ነበሩ
– ከዋጃ ዞብል የገባው የህወሀት ሰራዊት ያለምንም ጦርነት ቢሆንም ዞብል ተራሮች ላይ ከፍተኛ ጦርነት ከተደረገ በኋላ ዞብልን ሲቆጣጠሩ በአንድ ቀን ምሺት መከላከያ ሸሺቶ ወልድያ ሲገባ በአሻጥር ነበር
– ህወሀት ደጋውን ስትቆጣጠር ያለምንም ጦርነት ሲሆን ብአዴን ምንም ነገር አላለም
– ህወሀት ከሳንቃ እስከ ወልድያ የአንድ ቀን ጦርነት አድርጋ ወልድያን ከተቆጣጠረች በኋላ መከላከያው ከወልድያ እስከ ውርጌሳ ሸሺቶ የሄደው ያለምንም ጦርነት በአንድ ቀን ነበር ብአዴኖች ምንም ነገር አላሉም
– የወሎ ህዝብ ንብረቱ ተዘርፎ እየተጫነ እንዲወሰድ ሲደረግ የትግራይን መንገድ ክፍት በማድረግ ነበር
– የወሎ ህዝብ ንብረቶችና ቅርሶች ትግራይ ከገቡ ከ ሀያ ቀን በላይ ሁኗቸው ሳለ የብል*ግና አመራሮች ህዝባችንን ሲያደናግሩት ጁንታው የዘረፈዉን ንብረት ይዞ እንዳይወጣ ከበባ በማድረግ ንብረታችሁን አድኑ እያሉ እያሉ መቀደዳቸዉን ቀጥለዋል

– የወሎ ህዝብ እስከ ውጫሌ ያለው ተፈናቅሎ በደሴና በኮምቦልቻ ተከራይተውና ት/ቤቶች ላይ ተጠልለው ከስምንት መቶ ሺህ ህዝብ በላይ ተፈናቅለው በደሴ ህዝብ እየተረዱ ችግራቸውን ቻል አድርገው በስቃይ እየኖሩ ነው
– ከግማሺ ሚሊዬን ህዝብ በላይ ተፈናቅሎ የብል*ግና መንግስት ምንም አይነት እርዳታ እንዲቀርብለት አላደረጉም
– ህወሀት በያዙት የወሎ መሬቶች ላይ የሚኖሩ የወሎ ህዝብ የጅምላ ጭፍጨፋ እየተፈፀመባቸው አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሺን ጋዜጠኛ ያቀረበው የብአዴን አመራር የነበረ ጎጠኛ የወሎ ህዝብ ገና አልሞቱም ብሎ ተናገረ
– የወሎ ህዝብ በከሚሴና በወለጋ በኦህዴድ መንግስት የዘር ጭፍጨፋ እየተፈፀመበት በዐማራ ህዝብ ግብር ደመወዝ የሚከፈላቸው ጋዜጠኞችና ለህዝቡ የተቋቋሙ የሚዲያ ጣቢያዎች የወሎን ህዝብ የዘር ጭፍጨፋ እንዲዘገብ አይፈልጉም ዘግበውም አያውቁም
– የወሎ ህዝብ ሰብሉ በአንበጣ መንጋ እየወደመ አብይ አህመድና ደመቀ መኮነን በህፃን መጫወቻ ሲጫወቱ ነበር
 
የወሎ ህዝብ በመንግስት ያልተፈፀመበት በደል የለም ካሁን በኋላ ግን የብአዴን ጎጠኛ አመራሮች አሰራራቸውን የማያስተካክሉ ከሆነ ከስህተታቸው ተምረው ለወሎ ህዝብ በሁሉም ነገር ፍታሀዊ የልማት አገልግሎት እንዲያገኙ የማያደርጉ ከሆነ የወሎ ህዝብ ክልል የመሆን መብቱን መጠየቁ አይቀሬ ይሆናል::
 
የብልፅግና መንግስት የዘር ፖለቲካዉንና የክልል መንግስትነት መብትን ከህወሀት ወርሶ አስቀጥለዋለሁ ህገ-መንግስቱም አይቀዬርም እስካለ ድረስ የወሎ ህዝብም የመልማት መብቱንና በህይወሀት የመኖር መብቱን በልጆቹ ትግል ያስከብራል
 
እንደኔ ፍላጎት ከሆነ 
* ህገ መንግስቱ መቀዬር አለበት
* የዘር ፖለቲካ መጥፋት አለበት 
* ያለው የብል*ግና መንግስት ታግዶ የሺሺግር መንግስት መደረግ አለበት
* የብርሀኑ ነጋ ፓርቲ አመራሮች ከፖለቲካ ትግል መታገድ አለባቸው ለሀራችን አደጋ ፈጣሪ ናቸው
 
የዐማራ ህዝብ እንደ ህዝብ አንድነቱን እንዲቀጥል ከተፈለገ የዐማራ ጥላቶች መሳሪያ ሁኖ የሚያገለግለው የዐማራ ብል*ግና አመራሮች የክልሉን ወንበር በክብር ለቀው ዐማራን ለሚወክሉት የአብን አመራሮች ማስረከብ አለባቸዉ!!!!
Filed in: Amharic