*በፈጠራችሁ አምላክ! ድሮኗን እርሷት…!!!”
ጌታቸው ሽፈራው
*… እናም እባካችሁ “ድሮን” “ድሮን” እያላችሁ የሕዝቡን ድልብ አቅም አታኮላሹ። የሰማይ ነፋሪት መና ጠባቂ አታድርጉት። ጀግነቱን አትስለቡት* !!!
የአንድን ማህበረሰብ የጀግነት ባህል፣ የአሸናፊነት ስነ-ልቦና፣ ብሔራዊ ኩራት፣ የአልበገር ባይነት፣ የራስ አቅምንና የዓላማ ጽናትን በሚሰልብ መልኩ የድል አድራጊነትን አልፋና ኦሜጋ ለዘመን አመጣሽ ቴክኖሎጂ (ድሮን) መስጠት ነውር ነው። ፀያፍ ነው። አሳፋሪ ነው።
ሕዝባዊ ጦርነትን አሸናፊ የሚያደርገው የጦርነቱ ምክንያት፣ አላማው፣ ግቡና መዳረሻው ግልፀኝነት ሲሆን፤ ይህን ለማስፈፀመ የሚፈጠረው የሕዝባዊ ኃይል ተሳትፎ፣ አደረጃጀትና ሁለንተናዊ የአመራር ስርዓት ሲነርጂ መፍጠር ሲችል ብቻ ነው።
ህውሃት አስኳል የሆነበት የትግራይ ኃይል የአፋርና የትግራይን መሬት በወረራ ተቆጣጥሯል። ወራሪነቱ የጊዜ ጉዳይ ካልሆነ በስተቀር የተሸናፊነቱ ምክንያት ነው። በዚህ ምክንያት ወራሪውን በጉልበት ከተቆጣጠረበት ጠራርጎ ለማስወጣት የሚቀረጽ አላማም የጦርነቱን ፍትሐዊነት ያረጋግጣል። አማራም ሆነ አፋር የሚፈጥሩት ሕዝባዊ ኃይል በአግባቡ ከሰለጠነ፣ ከተደራጀ፣ ከታጠቀና የአመራር ስርዓት ካገኘ ወራሪውን ሃይል ከክልላቸው ጠራርጎ ከማስወጣት ባሻገር ለቀጣዩ አይቀሬ የጠረጴዛ ላይ ውይይትና ድርድር <የሃይል ሚዛን> በራስ አቅም መፍጠር ይቻላል።
እናም እባካችሁ “ድሮን” “ድሮን” እያላችሁ የሕዝቡን ድልብ አቅም አታኮላሹ። የሰማይ ነፋሪት መና ጠባቂ አታድርጉት። ጀግነቱን አትስለቡት። ዓብይ አህመድ በተጠና መንገድ እንዳደረገው በጊዜውና በሰዓቱ እንዳይነቃ፣እንዳይደራጅና እንዳይታጠቅ አታዘናጉት።
በዚህ አጋጣሚ ከቀድሞ የስራ ባልደረባዬ ሲሳይ አጌና አንደበት ዘወትር የማትጠፋው “ወታደራዊ ድል የሚለካው በእግረኛ ነው” የሚለውን አባባል ማስታወስ እፈልጋለሁ። ዛሬ ሳይንሱን ገልብጦት፣ አመለካከቱን ቀይሮት ካልሆነ በስተቀር!!
*በድል ዜና እንዳትዘናጋ!*
“ድሮን ስራ ጀመረች” ወዘተ የሚሉ ዜናዎችን ፌስቡክ ላይ እያየሁ ነው። መልካም ዜና ነው። መከላከያ ሰራዊታችን አቅም አገኘ ማለት ነው። አሸባሪው ትህነግን ለመምታት ተጨማሪ አቅም ተገኘ ማለት ነው። የአሸባሪው ትህነግ ደጋፊዎች ሲንጨረጨሩ የነበሩትም አሸባሪው ኃይላቸው በድሮን ይደበደባል ብለው ነው።
ነገር ግን! (ነገር ግንን ጠበቅ አድርገህ ያዝልኝ! የሚጠቅምህ ይሄ ነው!)
ድሮን ላይ ብቻ ተስፋ አታድርግ። እንዲያውም መልካም ዜና የተባለውን ሰምተህ፣ እንዳልሰማህ እለፈው። መልካም ዜናው አይጎዳህም። የሚጎዳህ መጥፎው ነውና መጥፎ ዜና እንዳይሰማ በርትተህ መስራትክን ቀጥል። በድል ዜና እንዳትዘናጋ፣ መጥፎው ዜና እንዳይመጣ ድሮን ስራ ጀመረች ሲባልም እርሳት።
አሸባሪው ትህነግ ከ5 ሚሊዮን የትግራይ ሕዝብ መካከል እስከ አንድ ሚሊዮን ገብሮም ቢሆን አንተን መጨፍጨፍና መዝረፍን እንደ ትልቅ ድል ይቆጥረዋል። ይህ ባይሳካለት በቀጣይ ሁለት ሚሊዮን፣ ሶስት ሚሊዮን የትግራይ ሕዝብንም አስፈጅቶ አንተን ቢጎዳ ትርፍ ያገኘ ይመስለዋል። ትግሬ ከምድረ ገፅ ጠፍቶ አንተን የሚያጠፋ ከመሰለው ያደርገዋል!
ጌታቸው አሰፋን ጨምሮ 50 የማይሞሉ ወንጀለኞች እንዳይያዙበት ነውኮ ይህ ሁሉ ችግር እንዲመጣ ያደረገው። አንተን ለመጉዳትማ ትግሬ ባዶ ቢቀር አይቆጨውም!
ስለሆነም የትግሬን ወጣት በለው አዛውንት እያሰለጠነ ያዘምታል። በድሮን ተመታ በመድፍ አያገባውም። ያለቀው አልቆ አንተን መጉዳት ነው አላማው። በዚህ ወቅት ያለው ታጣቂ ቢያልቅበት፣ አመትም ሁለት አመትም ፈጅቶ 2 ሚሊዮን የሚደርስ ሕዝብ መአበል አድርጎ አዝምቶ ዘርፎህ ጨፍጭፎህ ይሄዳል!
*ልብ አድርግ* !
ትህነግ ማለት ድብረፅዮን፣ ወይም ጌታቸው ረዳ ብቻ አይደለም። ትህነግ ማለት ክፉ አስተሳሰቡ ነው። አመራሩ ቢያልቅ፣ ተዋጊው ቢመታ አስተሳሰቡ ክፉኛ ተሰራጭቷል። ይህን አስተሳሰብ ይዞ ማገዶ የሚሆን ወጣት የሚያሰለጥን ተስፋ ያጣ ጀኔራል ቁጥሩ ቀላል አይደለም። አጥፍቶ ለመጥፋት የወሰነ በርካታ ኮ/ል፣ ብዙ ሻለቃ፣ ብዙ ባለሌላ ማዕረግ አላቸው። የድሮዎቹ ወያኔዎች 17 አመት ከሸፈቱት ባልተናነሰ ሸፍቶ አንተን የሚያጠፋ ከመሰለው ወደኋላ የማይል ብዙ የነቀርሳው ተሸካሚ ሞልቷል።
ሕልውናህን የሚያስጠብቀው ድሮን ሳይሆን ራስህ ነህ። የሚጠብቅህ የራስህ ጥንካሬ ነው። ከድሮን በላይ ሁሌም በራስህ ተማመን። በጥልቆ ስናይፐር የቀማ ስነ ልቦናህን አበርታ፣ በድንጋይ ክላሽ የማረከ ስነልቦናህን አጠናክረው። አንድ ሆኖ 11 አሸባሪ የረፈረፈው ጀግንነትህ ነው የሚያዋጣህ! 37 ክላሽና አምቡላንስ የቀማውን የዋግሹም ልጅ አይነት ልብ ነው ከትህነግ የጥፋት ድግስ የሚያድንህ!
አዎ ድሮን ብዙ ያግዛል። ደስም ሊያሰኝህ ይገባል። ግን የአሸባሪው ትህነግ ኃይል አልቆ እንኳን ሕልውናህ አይረጋገጥም። በድሮን ተመትቶ ቆላ ተንቤን ተደብቆ የከረመ ኃይል ነው በግብፅ፣ ሱዳንና ምዕራባዊያን ሀገራትና የእርዳታ ድርጅቶች ታግዞ እንደገና የወረረህ! ዘግናኝ ጭፍጨፋ፣ ልክ ያጣ ዘረፋ የፈፀመብህ በድሮን ተመትቶ ተበታትኖ የነበረ ኃይል ነው። ወልዲያን ያወደማት፣ ቆቦን ያራቆታት፣ ሰቆጣን የመዘበራት፣ ጋይንትን የዘረፈው፣ ማይጠምሪን ሰቆቃዋን ያበዛው፣ ላሊበላን የሚያክል ምልክት የደፈረው፣ ወገንክን የጨፈጨው ወራሪ ትናንት በድሮን የተደበደበ ነው! ነገም ተደብድቦ፣ ጠፋ ከተባለ በኋላ ብዙ ማገዶ የሚሆን ትግሬ ወጣት አግተልትሎ ሊያጠፋህ እንደሚመጣ እንዳትዘነጋው!
እየወጋን ያለው ዓለም አቀፍ ኃይል ጭምር ነው። ድሮን ስራ ጀምሮም ነገ የሚያመጣውን አናውቅም። ማዕቀብ በለው ሌላ ጣልቃ ገብነት እቅዳቸው ውስጥ ያለ ነው። ትህነግ እንዳይጎዳ ብዙ ይሰራሉ። አንተም ድሮኗን ረስተህ፣ ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ወገኖች ጋር ተባብረህ፣ መከላከያ ሰራዊትና ልዩ ኃይሉን እየተቀላቀልክ፣ ፋኖን እያጠናከርክ ራስክን አጠናክር። ልዩነት ሲኖር እያጠበብክ፣ የእልህና ግንፍልተኝነት ፖለቲካን ወዲያ ጥለህ፣ አንድነትህን እያበረታህ የራስህ ጥንካሬና ዝግጅት ላይ ትኩረት አድርግ!
እየተዋጋህ ያለው በድሮን የሚመታ ብቻ አይደለም። የእርዳታ ድርጅቱን፣ ግብፅን፣ ምዕራባዊያን ሀገራትን በድሮን አትመታም። የራስክን ጅላጅል በድሮን አትመታም። “ድርድር” ቅብጥርጥስ እያለ የሚያዘናጋህ፣ በተጨፈጨፉት ወገኖችህ ደም፣ በተዘረፈና በወደመው ንብረትህ ላይ “ድርድር” እያለ የሚቀልደው ሌላ አስጠቂህ ነው። ሀገርህና የአንተ ሕልውና ላይ ለመወሰን በዚህም በዛም እየመጣ ያለው ብዙ ነው። ይህን ኀይል የምትታገለው በድሮን አይደለም። በራስህ ጥንካሬ ነው። አሸባሪው በሚሳኤል፣ በታንክ ተደበደበ ብለህ ሳትዘናጋ፣ ቆላ ተንቤን ገባ ቃሊቲ ሳያዘነጋህ የጀመርከውን አጠናክረህ ዳግመኛ የማትወረርበት ደረጃ ላይ ስትደርስ ብቻ ነው ጠላትህን ሳትገጥመውም ጭምር ድቅቅ የምታደርገው!
ደመና እና ጭጋግ በነበረ ጊዜ፣ ደመናና ጭጋግ ሰበብ ሆኗል። ድሮንም፣ ጀትም አይመታም እየተባለ ሲነገርህ ነበር። አንተ ማተኮር ያለብህ ብርድ፣ ዳመና፣ ዝናብ ፀሐይ ሳይል ሕልውናህን የሚጠብቅልህ ላይ ነው። ይህን የምታደርገው ራስህ ነህ። መሳርያ ኖረህ አልኖረህ ከተደራጀህ፣ ከቆረጥክ፣ አንድነትክን ከጠበክ ጠላትን መክተህ ራስክን ትጠብቃለህ። ትኩረትህ የራስህ አቅም ላይ ይሁን!
የአሸባሪው ትህነግ አደገኛው፣ ገዳዩ፣ ዘራፊው፣ ጨፍጫፎው መሳርያው ብቻ አይደለም። አስተሳሰቡ ነው። የተከፈተብን ጦርነት ሕዝባዊ ጦርነት ነው። በሰርጎ ገብ፣ በአሻጥር፣ በቅጥረኝነት፣ በከተማ ሽብርተኛ ጭምር የተከፈተብን ጦርነት ነው። ይህ ጦርነት በከባድ መሳርያ ብቻ አይፈታም። ለአመታት የሚዘልቅ ዝግጅት፣ ጥንቃቄ፣ ትኩረት ያስፈልጋል።
ድሮን ደግሞ ለአመታት ቆሞ ሕልውናህን ሊያስጠብቅ አይችልም። ስራ ላይ ከዋለ እንኳን ከተጠቃህ በኋላ ጭምር ነው ሊደርስ የሚችለው። የአንተ መዳኛህ መሳርያ ብቻ አይደለም። ስነ ልቦናህ፣ ጀግንነትህ፣ ትኩረትህ ነው። አለመዘናጋትህ ከየትኛውም ዘመናዊ መሳርያ ባልተናነሰ ይጠብቅሃል።
በድሮንም በለው በሌላ መሳርያ የታገዘው ፀረ ትህነግ ዘመቻ የአንተ አይደለም አላልኩም። የአንተው ነው፣ የሀገርህ ነው። ኩራበት። ተደሰት። ነገር ግን ይህን ድል ዘላቂ እንዲሆን፣ አሸባሪው ትህነግ ዛሬ ጠፍቶ ነገ የሚነሳ እንዳይሆን በራስህ ላይ ስራ።
የድል ዜናው፣ የድሮን ድብደባው (ካለ) ፈፅሞ ሊያዘናጋህ አይገባም። የገጠመህ አደጋ በከባድ መሳርያ ብቻ የሚፈታ አይደለም። ረዥም ጊዜና ሳትዘናጋ በምታደርገው ዝግጅት የሚፈታ ነው።
ድሮኗን ለጊዜው እርሳት፣ ተጨማሪ ዝግጅት ላይ ትኩረት አድርግ!
የድል ዜናው የጀመርከውን እንድትቀጥል እንጅ “አበቃለት” ብለህ እንድታቆመው ሊያደርግህ አይገባም።
ይህን የምልህ!
“ድሮኗ ስራ ጀመረች” ሲባል የሚሰማህን ደስታም ለመከልከል አይደለም። ከጠላትህ ክፋት፣ ከደረሰብህ ወረራ አንፃር ብትደሰት ትክክል ነህ። ግን ባለፈውም “ላይነሳ ተደመሰሰ” ተብሎ ተደስተህ ነበር። ሌላ ስህተት ይበቃል። “ሊያልቅለት ነው” ብሎ የራስን ዝግጅት መቀነስ፣”አለቀለት” ብሎ መዘናጋት ዋጋ ያስከፍላል። አስከፍሏል።
ድሮን ስራ ጀመረች ስላሉህ እንዳትዘናጋ! “ይቅናት” ድሉ ድልህ ነው! የድል ዜና ስትሰማ የጀመርከውን እንዳትተው! ዳግመኛ እንዳትሸወድ! የገጠመህ በምድር ላይ የአንተን ያህል ጠላቴ ብሎ የሚፈርጀው ሌላ ኃይል የሌለው ደመኛ፣ ነቀርሳ ጠላት ነው!
#እንዳትዘናጋ
#ተደራጅ
#ሰልጥን
#ዝመት
#መክት