>

ህወሀት ወያኔ 92 ሚሊዮን ብር መድቦ ለጥፋት አላማው ያሰማራው  የቅማንት ኮሚቴ...!!! (አቻምየለህ ታምሩ)

ህወሀት ወያኔ 92 ሚሊዮን ብር መድቦ ለጥፋት አላማው ያሰማራው  የቅማንት ኮሚቴ…!!!

አቻምየለህ ታምሩ

*…. ፋሽስት ወያኔ ከ92 ሚሊዮን ብር በላይ ጥሬ ገንዘብ ዓመታዊ ባጀት መድቦ፤ 605 ክላሽንኮቮችን፣ 40 የቡድን መሳሪያዎችን፣ 5272 ቦንቦችንና ሌሎች በርካታ የጦር መሳሪያዎችን አስታጥቆ የሚያንቀሳቅሳቸው የቅማንት ኮሚቴና ቅዴፓ! 

የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በኅዳር ወር መቀሌን ከተቆጣጠረ በኋላ በፋሽስት ወያኔ ይፋዊና ስውር ቢሮዎች ውስጥ በርካታ ፍተሻዎች ተካሂደው ነበር። በተካሄዱት ፍተሻዎችም ያልተገኘ የፋሽስት ወያኔ የ47 ዓመታት ገመናና ሚስጥራዊ ሰነድ አልነበረም ለአገርና ሕዝብ የሚቆረቆሩ የአገር ቤት ወዳጆቻችንም ከሚስጥራዊ ሰነዶቹ መካከል የተወሰኑትን አጋርተውን አንዳንዶቹን ለመመልከት ችለናል።

በእጃችን ከገቡት የፋሽስት ወያኔ ሚስጥራዊ ሰነዶች መካከል ፋሽስት ወያኔ ከ92 ሚሊዮን ብር በላይ ጥሬ ገንዘብ ዓመታዊ ባጀት መድቦና እልቆ ቢስ የጦር መሳሪያ አስታጥቆ የሚያንቀሳቅሳቸው የቅማንት ኮሚቴና ቅዴፓ የሚባለውን ፓርቲ የወንጀል ስምሪት የሚያጋልጡ ሰንዶች ይገኙበታል።

አሳዛኙ ነገር በአቃቤ ሕግና ፌዴራል ፖሊስ ተብዮዎቹ እጅ ላይ የሚገኙንት እነዚህ  የፋሽስት ወያኔ የወንጀል ሰነዶች እስከ ዛሬ ድረስ ለሕዝብ ይፋ አለመሆናቸው ብቻ ሳይሆን ፋሽስት ወያኔ በሺዎች የሚቆጠር ክላሽንኮቭ፣ ቦንብ፣ የቡድን መሳሪያ፣ ሌሎችን የጦር መሳሪያዎች አስታጥቆና በሺዎች የሚቆጠሩ ተዋጊ አባላቱን አሰልጥቶ በጎንደር ላይ ያሰማራው ቅዴፓ የሚባለው ፓርቲ ዛሬም ድረስ ብርቱካን ሜዴቅሳ በምትመራው የምርጫ ቦርድ መዝገብ ሰላማዊ የፖለቲካ ፓርቲ ተብሎ ተመዝግቦ መገኘቱ ነው።

የሆነው ሆኖ ከታች የሚታዩት ገጾች የቅማንት ኮሚቴና ቅዴፓ የሚባለው ፓርቲ ከፋሽስት ወያኔ ጋር የተዋዋሉትን የሚያሳይ ሲሆን ሰነዱ አማራን ማኅበራዊ እረፍት የመንሳት ፋሽስት ወያኒያዊ ተልዕኮ ተሰጥቷቸው የሚንቀሳቀሱት የቅማንት ኮሚቴና ቅዴፓ የሚባለው ፓርቲ ከመስከረም 1/2013 ዓ.ም. – እስከ መስከረም 1/2014 ዓ.ም. ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ እውን  እንዲያደርጉት መቀሌ ድረስ ተገኝተው የተቀበሉትን ስምሪትና ይህን ሰይጣናዊ አላማ በጦር መሳሪያ ለማስፈጸምም  ፋሽስት ወያኔ የመደበላቸውን ከ92 ሚሊዮን ብር በላይ  የሚሆን ጥሬ ገንዘብ ዓመታዊ ባጀትና 605 ክላሽንኮቭ፣ 40 የቡድን መሳሪያ፣ 5272 ቦንቦችን ጨምሮ ሌሎች እልቆ ቢስ የጦር መሳሪያዎችን አስታጥቆ ወደ ጎንደር እንደላካቸው የሚያሳዩ ናቸው።

ማሳሰቢያ፡-

ሰነዱ የተገኘው አቃቤ ሕግና ከፌዴራል ፖሊስ ከሚባሉት ቢሮዎች ሲሆን እኔ ዘንድ የደረሰው ለአገርና ሕዝብ በሚቆረቆሩ ወገኖቼ አማካኝነት ነው። እነዚህ ወገኖች ያጋሩኝ ሰነዶች በርካቶች ናቸው። በደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል ፊርማ ለነ ያየሰው ሽመልስ የተቦጨቀውን ረብጣ ገንዘብና ለሌሎች የፋሽስት ወያኔ ጉዳይ አስፈጻሚዎች የተሰጠውን ዳጎስ ያለ የብር መጠን የሚያሳዩ ሌሎች የመቀሌ ሰነዶችን ይዘን በሌላ ጊዜ እንመለሳለን።

Filed in: Amharic