>

"ንግስተ ነገስት ዘኢትዮጵያ ነኝ" ባዩዋ እህተማሪያም (ወይዘሮ ስንዱ) ከአምስት ባልደረቦቿ ጋር ታሰረች...!!! (ቶማስ ነጋሽ)

“ንግስተ ነገስት ዘኢትዮጵያ ነኝ” ባዩዋ እህተማሪያም (ወይዘሮ ስንዱ) ከአምስት ባልደረቦቿ ጋር ታሰረች…!!!
ቶማስ ነጋሽ

ንግስተ ነገስት ዘኢትዮጵያ ነኝ” ባዩዋ እህተማሪያም (ወይዘሮ ስንዱ) ሰሞኑን ሁመራ ላይ ከ3 ወንዶችና 2 ሴቶች ጋር በቁጥጥር ስር ውላለች። በቁጥጥር ስር በዋሉበት ወቅት “እህተማርያም የኢንቨስትመንት ስራ አለኝ የሚል ምላሽ የሰጠች ሲሆን አንደኛው ደግሞ የህክምና ዶክተር ነኝ ብሏል።
እህተማርያምን በተመለከተ የአካባቢው መሬት አስተዳደር በስሟ የተመዘገበ ኢንቨስትመንት ሆነ ውክልና የተሰጣት ኢንቨስትመንት አለመኖሩን አረጋግጧል። ዶክተር ነኝ ያለው ሰውየ ደግሞ እሰራበታለሁ ያለው ሆስፒታል ላይ ሲጣራ ምንም አይነት ቅጥርም ሆነ ሌላ የስራ ግንኙነት እንደሌለው ተረጋግጧል።
ሰዎቹ ከዚህ ቀደም የወልቃይት ጠገዴ ፖሊስ በቁጥጥር ስር አውሏቸው እንደነበር ታውቋል። ሰዎቹ ከሁመራ ወደ ሉጉዲ እንዲሁም ሃምዳዊት ይመላለሱ እንደነበር ተጨባጭ መረጃዎች አሉ። ማይካድራ አካባቢም እንዲሁ። ሃምዳዊት ደግሞ ጨፍጫፊው የህወሃት ሳምረ ቡድን የተከማቸበት ቦታ ነው። ይቺን ያዙልኝ።
አደባይና ሉጉዲም የኢንቨስትመንት ስራ አለን እያሉ ሲንቀሳቀሱ ነበር ተብሏል። እነዚህ ቦታዎች ደግሞ ከወቅቱ የፀጥታ ሁኔታ ጋር ተያይዞ ለኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ የማይታሰብ ነበር። ማይካድራ ምን ሲሰሩ ነበር? ብለንም እንጠቅ።
ከሴትዮዋ ጋር የተያዘው አንደኛው ግለሰብ ደግሞ ከህወሃት ሰፈር የተገኘ ሰው ነው ተብሏል። ነጥቦችን ማገናኘት ነው።
ሌሎች እረዳቶቿ ደሞ በሰላዲንጋይ ፃድቃኔ ማርያም እንደሚገኙ ፍንጮች እያመለከቱ ሲሆን የተሟላ መረጃ እንደደረሰን በምስል አስደግፈን የምናቀርብላችሁ ይሆናል።
ሌላው ደግሞ
ይቺ ሴትዮ አዲስ አበባ እየተነቀሳቀሰች በነበረችበት ወቅት “ሰላይ” እንደነበረች አንዳንድ ምንጮች ይጠቁማሉ። እንዲህ ያሉ ሰዎችን ጠበቅ አድርጎ መያዝ እንደሚገባም አስፈላጊ ነው።
Filed in: Amharic