>

  ከ92 ሚሊዮን ብር በላይ ለጥፋት የሚውል በጀት የተመደበለት የቅማንት ኮሚቴ ነገር  (ክፍል 2 - አቻምየለህ ታምሩ)

  ከ92 ሚሊዮን ብር በላይ ለጥፋት የሚውል በጀት የተመደበለት የቅማንት ኮሚቴ ነገር
ክፍል 2
አቻምየለህ ታምሩ

ፋሽስት ወያኔ ከ92 ሚሊዮን ብር በላይ ጥሬ ገንዘብ ዓመታዊ ባጀት መድቦ፤ 605 ክላሽንኮቮችን፣ 40 የቡድን መሳሪያዎችን፣ 5272 ቦንቦችንና ሌሎች በርካታ የጦር መሳሪያዎችን አስታጥቆ የሚያንቀሳቅሳቸው የቅማንት ኮሚቴና ቅዴፓ! [ክፍል ፪] 
ትናንትና በክፍል አንድ ባቀረብሁት ጽሑፍ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በዚህ ዓመት ኅዳር ወር ላይ መቀሌን ከተቆጣጠረ በኋላ በፋሽስት ወያኔ ግልጽና ስውር ቢሮዎች ውስጥ በተካሄዱ ፍተሻዎች ከተገኙ ሰነዶች መካከል የተወሰኑትን አጋርቼ ነበር።
በትናንትናው ጽሑፌ ካጋራኳቸው የፋሽስት ወያኔ ሚስጥራዊ ሰነዶች መካከል የቅማንት ኮሚቴንና ቅዴፓ የሚባለው ፓርቲ ከ92 ሚሊዮን ብር በላይ ጥሬ ገንዘብ ዓመታዊ ባጀት ተመድቦላቸውና 605 ክላሽንኮቮች፣ 40 የቡድን መሳሪያዎች፣ 5272 ቦንቦችና ሌሎች በርካታ የጦር መሳሪያዎች እንዲታጠቁ ተደርጎ አማራን ማኅበራዊ ረፍት ለመንሳት ከፋሽስት ወያኔ ተልዕኮ ተቀብለው ወደ ጎንደር የተሰማሩበትና ተልዕኳቸውም  ከመስከረም 1 ቀን 2013 ዓ.ም. – መስከረም 1 2014 ዓ.ም. ባለው አንድ አመት ጊዜ ውስጥ ለመፈጸም መስማማታቸውን የሚያሳየው ውል አንዱ ነበር።
በዛሬ ውለት የማጋራው መቀሌ ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካዔል ቢሮ የተገኘ ሰነድ ደግሞ  የቅማንት ኮሚቴና ቅዴፓ የሚባለው ፓርቲ ፋሽስት ወያኔ የመደበላቸውን ከ92 ሚሊዮን ብር በላይ ጥሬ ገንዘብ ዓመታዊ ባጀትና 605 ክላሽንኮቮችን፣ 40 የቡድን መሳሪያዎችን፣ 5272 ቦንቦችንና ሌሎች በርካታ የጦር መሳሪያዎችን ከፋሽስት ወያኔ ፈርመው የተቀበሉት የቅማንት ኮሚቴና ቅዴፓ የሚባለው ፓርቲ አባላትን ስም፣ ፊርማና የስልክ ቁጥራቸውን ሳይቀር በእጃቸው የጻፉበትን ሚስጥራዊ ሰነድ ነው።
እነሆ የሰዎቹ ስም ዝርዝር ከነ ሙሉ አድራሻቸው! እነዚህ ሰዎች ናቸው እንግዲህ ከፋሽስት ወያኔ የተመደበላቸውን ከ92 ሚሊዮን ብር በላይ ጥሬ ገንዘብ ዓመታዊ ባጀትና 605 ክላሽንኮቮችን፣ 40 የቡድን መሳሪያዎችን፣ 5272 ቦንቦችንና ሌሎች በርካታ የጦር መሳሪያዎችን ከመቀሌ ተረክበው ወደ ጎንደር የተሰማሩት!
በቀጣይ የምናወጣው በደብረ ጽዮን ገብረ ሚካዔል ተፈርሞ ለነያየሰው ሽመልስ እንዲከፈል  የተደረገውን በሚሊዮኖች የሚቆጠር ጥሬ ገንዘብ የሚያሳየውን ሰነድ ነው።
Filed in: Amharic