>
5:21 pm - Saturday July 21, 3934

ኢትዮጵያዊነትማ እንደ አፋር ነው! (አቻምየለህ ታምሩ)

ኢትዮጵያዊነትማ እንደ አፋር ነው!

አቻምየለህ ታምሩ

አገር የሚጸናው፣ ብሔራዊ ክብር የማይደፈረው፣ የሕዝብ ሉዓላዊነት የሚከበረው እንደ አገርና ሕዝብ የማንደራደርባቸው ነገሮች ሲኖሩን ነው። በአገር አንድነት፣ በብሔራዊ ክብርና በሕዝብ ሉዓላዊነት ላይ የሚቃጣን ማናቸውንም ሙከራ የሚታገስ፤ አይቶ እንዳላየ የሚያልፍና በግልጽም ሆነ በስውር በአገር አንድነት፣ በብሔራዊ ክብርና በሕዝብ ሉዓላዊነት ላይ የሚቆምር  መሪንና በመንግሥትነት የተሰየመ ቡድንን የሚታገስ ሕዝብ አንድነቱ የጸና፣ ብሔራዊ ክብር ያለውና ሉዓላዊነቱ የማይደፈር አገር ባለቤት ሊሆን አይችልም።
የአገርን አንድነት፣ ብሔራዊ ክብርና ሉዓላዊነት ማስጠበቅ ያሚቻለው ከጠላት ጋር የቆሙ  የውስጥ ባንዶችን ያለ ምህረት መቅጣት ሲቻልም ነው። አባቶቻችን የጥቁር ሕዝብ የነጻነት ጮራና የተስፋ አርአያ የሆነች አገር ትተውልን ያለፉት የውስጥ ባንዶችን ያለ ምህረት በመቅጣታቸው ነው። የውስጥ ባንዳን የሚታገስ ሕዝብ በጠላቶቹ የሚፈራ፣ በወዳጆቹ የሚከበርና ሉዓላዊ የሆነ አገር ሊኖረው አይችልም።
በዚህ ረገድ የአፋር ሕዝብ ከሰሞኑ ከውስጡ በበቀሉ ባንዶች ላይ ያሳለፈው ሕዝበ ውሳኔ እጅጉን የሚያስደምም ብሔራዊ ተግባር በመሆኑ አገራችንን የምንወድ ሁሉ ልንኮራበት ይገባል። የክልሉ ሕዝብ ባደረገው ጉባዔ ኢትዮጵያን ለማፍረስ ሲዖልም ቢሆን እንገባለን ካሉት ከፋሽስት ወያኔ ጋር አሰላለፋቸውን ያስተካከሉ የአፋር ክልል የቀድሞ ባለስልጣናትን የአፋር ደመኛና የኢትዮጵያ ጠላት ናቸው በማለት በአሸባሪነት እንዲፈረጁ ካደረገ በኋላ በተገኙበት እርምጃ ይወሰድባቸው ዘንድ ውሳኔ አስተላልፏል። ይህ የአፋር ሕዝብ ቆራጥነት የአገርና ሕዝብ ጉዳይ ግድ የሚለው ኢትዮጵያዊ ዜጋ ብቻ ሳይሆን ብሔራዊ ስሜት ያለው ሰው ሁሉ ሊቀናበት የሚገባው የአገር መውደድ ተምሳሌት ነው።
ስለኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት አብዝቶ የሚጨነቅ ቢኖር ልክ እንደ አፋር ሕዝብ ኢትዮጵያን ለማፍረስ ሲዖልም ድረስ ቢሆን ለመሄድ ከተማማለ የአገር ጠላት ጋር የተሰለፉ የውስጥ ባንዶችንና የአገርና የሕዝብ ጠላቶችን ለማጥፋት ቆራጥና ቆምጫጫ እርምጃ ይወስዳል።
ፋሽስት ወያኔን እየመሩ ከኮረም እስከ ጋይንት ድረስ ያመጡ የፋሽስት ወያኔ አስተኳሽ የሆኑ የብአዴን ሹማምንት መሆናቸውን በድምጽ ጭምር የተያዘ ማስረጃ ስላለ አጠያያቂ አይደለም። ደቡብ ጎንደር ከፋሽስት ወያኔ የግፍ ወረራ በጀግኖቻችን ተጋድሎ ነጻ ሊሆን የቻለው እነዚህ የፋሽስት ወያኔ አስተኳሽ የነበሩ የብአዴን ሹማምንት በአማራ ወጣቶች ያለ ምህረት በመመንጠራቸው ነው።
የፋሽስት ወያኔ አስተኳሽ የሆኑ የብአዴን ሹማምንት ከጥቅም ውጪ ከተደረጉ በኋላ በተደረገው ተጋድሎ የደቡብ ጎንደር ከፋሽስት ወያኔ የግፍ ወረራ ነጻ መውጣት ፋሽስት ወያኔ አሁንም ድረስ በግፍ ወርሮ በያዛቸው አካባቢዎች እየተደረገ ያለው የኅልውና ተጋድሎ  ከግብ እንዲደርስ ካስፈለገ ሊወሰዱ ስለሚገባቸው እርምጃዎች የሚያስተምረን ብዙ ነገር አለ።
ፋሽስት ወያኔ በሰሜን ጎንደር፣ በሰሜን ወሎና በዋግ አካባቢዎች በግፍ የወረራቸውን አካባቢዎች ነጻ ለማውጣት ብዙ ሙከራዎች የተደረጉ ቢሆንም ከፍተኛ መስዕዋትነት እየተከፈለባቸው እየተደረጉ የሚገኙት ሕዝባዊ ተጋድሎዎች አካባቢዎቹን ከፋሽስት ወያኔ አንበጣ ሠራዊት ወረራ ሙሉ በሙሉ ነጻ ማውጣት አልቻሉም። ይህም ሊሆን የቻለው የተመታውና የተደመሰሰው ወራሪ ኃይል አቅጣጫና መስመር ቀይሮ፤ ወራሪ አስበጣ ሠራዊቱን አብዝቶ ተመልሶ እየመጣ ሌላ ዙር ወረራ እያካሄደ በመሆኑ ነው።
የተደመሰሰውና የተመታው የፋሽስት ወያኔ ወራሪ አንበጣ ሠራዊት ኃይሉን አሰባስቦ፣ አቅጣጫና መስመር በመቀየር በወገን ላይ ወረራ ለመፈጸመ ተመልሶ በመምጣት ላይ የሚገኘው የብአዴን የውስጥ አስተኳሾች በደቡብ ጎንደር እንዳደረጉት ሁሉ አካባቢያቸውን ለመዝረፍ፣ ለማውደምና በወገናቸው ላይ የዘር ማጥፋት ለመፈጸም ወረራ ለሚያካሄደው አንበጣ ሠራዊት የወገንን ኃይል አሰላለፍና መረጃ አንዳች ሳያስቀሩ [በአስተኳሽ ብአዴናውያን ቋንቋ “ሙሉ OP በመስራት”] አሳልፈው እየሰጡት በመሆኑ ነው።
ከሩቅ ያለ ጠላት የውስጥ አስተኳሽ ሳይኖረውና የተሟላ መረጃ ሳይዝ በማያውቀው አካባቢ፣ ያውም በጠላትነት ፈርጆ ሊያጠፋውና አለኝ የሚለውን ሒሳብ ሊያወራርድ በሚዘምትበት ሕዝብ ላይ ተደጋጋሚ ወረራ ሊፈጽም አይችልም።
ስለዚህ በሰሜን ጎንደር፣ በሰሜን ወሎና በዋግ ግንባሮች እየተደረገ ያለውን ጸረ ፋሽስት ወያኔ ተጋድሎ ባጭር ጊዜ በድል ለማጠናቀቅ ደቡብ ጎንደር ግንባር እንደተደረገው ሁሉ የፋሽስት ወያኔ አስተኳሽ የሆኑ የብአዴን ሹማምንትን ከጥቅም ውጭ ማድረግ ያስፈልጋል።
ልክ እንደ አፋሮች ቆራጥ በመሆን በሰሜን ጎንደር፣ በሰሜን ወሎና በዋግ ዞኖች የሚገኙት የፋሽስት ወያኔ አስተኳሽ የሆኑ የብአዴን ሹማምንት ከአገልግሎት ውጭ ማድረግ እስካልተቻለ ድረስ በነዚህ ሰዎች እየታገዘ አገር ሊያፈርስና በአማራ ላይ የዘር ማጥፋት እያካሄደ ያለውን የፋሽስት ወያኔ አንበጣ ሠራዊት አይቀጡት ቅጣት ቀጥቶ በግፍ ከወረራቸው አካባቢዎች   በአጭር ጊዜ ውስጥ ጠራርጎ ማስወጣት አይቻልም።
ከፍ ሲል እንደቀረበው የአገርን ሉዓላዊነትና የሕዝብን ክብር ማስጠበቅ የሚቻለው ልክ እንደ አፋሮች በቅድሚያ የውስጥ ባንዳን ያለ ምህረት መመንጠር ሲቻል ነው። ከሩቅ የሚመጣ ጠላት አካባቢ ያልሆን አካባቢ ለመውረር የሚመጣው ከአካባቢው ሁነኛ ሰዎች በሚያገኘው አስተማማኝ መረጃ አካማኝነት ነው።
ወራሪ ጠላት የውስጥ ሰው ሳይዝና ሁነኛ ከሆነ አካል አስተማማኝ መረጃ ሳያገኝ በሆነ አቅጣጫ ወይም መስመር ወረራ ለመፈጸመ ከሩቅ ድረስ አይመጣም። ፋሽስት ወያኔም በደቡብ ጎንደር እንዳደረገው ሁሉ ሰሜን ጎንደር፣ ሰሜን ወሎና ዋግን የወረራው የብአዴን ሹማምንት ከውስጥ በሚያቀብሉት አስተማማኝ ሚስጥራዊ መረጃ እየታገዘና በነሱ መንገድ መሪነት ነው። እነዚህን የፋሽስት ወያኔ አስተኳሽና መንገድ መሪ የብአዴን ሹማምንት መመንጠር እስካልተቻለ ድረስ በነሱ መንገድ መሪነትና አስተኳሽነት አካባቢዎቻችን የወረረውንና በተደጋጋሚ እየወጋን ያለውን ተኳሹን ፋሽስት ወያኔን በቀላሉ መደምሰስ አንችልም።
Filed in: Amharic