>

የፍትህ አደባባያችን....?!?  (ጋዜጠኛ መአዛ መሀመድ)

የፍትህ አደባባያችን….?!?

 ጋዜጠኛ መአዛ መሀመድ

*…. ፌደራል ፖሊስ አቶ ታዲዮስ ታንቱን አላሰርኩም አለ!!!
*….የገላን ከተማ ፖሊስ መምሪያ ፍርድ ቤት አያዝዘኝም ብሏል!!!
 
ከሰኔ 25 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ በእስር ላይ የሚገኙትን አቶ ታዲዮስ ታንቱ ይዞ እንዲቀርብ ለዛሬ ነሐሴ 27 ቀን 2013 ትዕዛዝ ተሰቶ የነበረው ፌደራል ፖሊስ ከእኔ ዘንድ የሉም የሚል ምላሽ ሰቷል። አቶ ታዲዮስንም ከቤታቸውም አልወሰድኩም ብሏል። የፌደራል ፖሊስ መታወቂና ልብስ የለበሱ ፖሊሶች ሌሊት 5 ሰዓት ላይ እንደወሰዷቸው ባለቤታቸው ለችሎት ትናግረዋል።
 ይህንን የፌደራል ፖሊስ ምላሽ ተከትሎ አቶ ታዲዮስ ታስረው የሚገኙበት የከላን ከተማ ፖሊስ መምሪያ አቶ ታዲዮስ በግቢያቸው መገኘት አለመገኘታቸውን፤ በግቢያቸው የሚገኙ ከሆነም ለምን እና በማን ትዕዛዝ እንደታሰሩ ዛሬ ነሐሴ 28 ቀን 2013 ዓ.ም ቀርቦ እንዲያስረዳ የፍርድ ቤት ትዕዛዝ የተላከለት የገላን ፖሊስ መምሪያ ፍርድ ቤት አያዝዘኝም በማለት መጥሪያውን ሊያደርሱ የሄዱትን የአቶ ታዲዮስ ባለቤት ወ/ሮ ፀጋ ሞገስን እና ልጃቸውን መልሷቸዋል። ፍርድ ቤትም  ሳይቀርብ ቀርቷል።
ዛሬ በነበረው ቀጠሮ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አቶ ታዲዮስ የሚገኙበት የገላን ከተማ ፖሊስ መምሪያ ኃላፊው ቀርበው እንዲያስረዱ ድጋሜ ትዕዛዝ መስጠቱን እና ለጷግሜ 3 ቀን 2013 ዓ.ም መቀጠሩን ጠበቃቸው አዲሱ ጌታነህ ነግሮኛል።
Filed in: Amharic