>

“የትግራይ ክልል ስለ ህወሓት ክፉ ታስባለህ ተብሎ ደብዛ የሚጠፋበት ክልል ነው...!!”  (አቶ አታክልቲ ኃ/ሥላሴ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር)

“የትግራይ ክልል ስለ ህወሓት ክፉ ታስባለህ ተብሎ ደብዛ የሚጠፋበት ክልል ነው…!!”
 አቶ አታክልቲ ኃ/ሥላሴ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የመቀለ ከተማ የቀድሞው  ከንቲባ
(ኢ ፕ ድ) 

አሸባሪው የህወሓት ቡድን ስልጣን ላይ በነበረባቸው ባለፉት 27 ዓመታት በትግራይ ክልል ህዝብ ላይ ሲያደርስ የነበረውን ግፍና ጭቆና አደባባይ ወጥቶ ለመቃወም ይቅርና “ስለ ህወሓት ክፉ ታስባለህ” ተብሎ የምትታሰርበትና ደብዛህ የሚጠፋበት ክልል እንደነበር የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የመቀለ ከተማ ከንቲባ አቶ አታክልቲ ኃ/ሥላሴ አስታወቁ።
አቶ አታክልቲ በተለይ ለአዲስ ዘመን እንዳስታወቁ ፤ አሸባሪው የህወሓት ቡድን ስልጣን ላይ በነበረባቸው ባለፉት 27 ዓመታት ከማንም በላይ በትግራይ ክልል ህዝብ ላይ ግፍና ጭቆና ሲያደርስ ነበር። ህዝቡም የሚደርስበትን ግፍና ጭቆና አይደለም አደባባይ ወጥቶ ሊቃወም “ስለ ህወሓት ክፉ ታስባለህ” እየተባለ ጨለማ እስር ቤት ውስጥ እየተጣለ ደብዛው የሚጠፋበት ሁኔታ ነበር።
አሸባሪው ቡድን ስልጣን ላይ በነበረበት ወቅት የትግራይን ህዝብ በአንድ ለአምስት አደራጅቶ ወጥሮ ይዞ “እገሌ ምን ያስባል” እየተባለ ህብረተሰቡ እርስ በርሱ ከጀርባው እንዲጠራጠርና እንዲፈራራ በማድረግ ህዝቡ አንድ ሆኖ ቆሞ የሚደርስበትን ግፍና መከራ እንዳይቃወም ሲያደርግ እንደነበርም አስታውቀዋል።
በዚህም ህዝቡ በአንድ ለአምስት አደረጃጀት ተወጥሮ ተይዞ አይደለም አደባባይ ወጥቶ ሃሳቡን በነፃነት ሊገልጽ፤ ቃላትም ሳይተነፍስ በጥርጣሬ ብቻ ጨለማ እስር ቤት ውስጥ እየተጣለ አያሌ ወጣት ደብዛው መጥፋቱን ጠቁመዋል።
አሸባሪው ቡድን ስልጣን ላይ በነበረበት ወቅት የትግራይ ህዝብ ከሌለው ክልል ህዝብ በባሰ ሃሳቡን በነፃናት እንዳይገልጽና አማራጭ ሃሳብ እንዳይቀርብለት አፈና ሲደረግበት ከመኖሩ ባለፈ አሁን ላይ ጁንታው ህዝቡን መያዣ አድርጎ እጅ ተወርች አስሮ በአገሪቱ ከመጣው ፖለቲካዊ ለውጥ ተቋዳሽ እንዳይሆን እየሠራ ነው። ሕፃናትን ሳይቀር በጦርነት እየማገደ ህዝቡን በረሃብ እየቆላ ይገኛል ብለዋል።
Filed in: Amharic