>

"ጦርነቱን በእነሱ አውድማ ላይ ማድረግ አለብህ!...ጦርነቱን ከተከዜ ማዶ ማድረግ አለብህ!! እንዘግበዋለን!!"  ጋዜጠኛ ዜናነህ መኮንን

 
“ጦርነቱን በእነሱ አውድማ ላይ ማድረግ አለብህ!…ጦርነቱን ከተከዜ ማዶ ማድረግ አለብህ!! እንዘግበዋለን!!”
 ጋዜጠኛ ዜናነህ መኮንን
  ጋዜጠኛ ዳንኤል ገዛህኝ

 

*…. የህውሐትን አደገኛም፣አስቸጋሪነትን ሲያመላክት “ወያኔ አፈር ልሶ ሊነሳ ይችላል …”ይሄ ምንም የሚያጠራጥር ጉዳይ አይደለም በማለት ያስረዳል። ለዚህ ደግሞ የረጅም ጊዜ ልምዱንም ይጠቅሳል። ፍልስጤም እና እስራኤሎችን ያነሳል። ” ስለዚህ ” በማለት ይቀጥላል…”ስለዚህ በጠላት በኩል ዝምብለን አታሞ የምንመታበት አይደለም ምክንያቱም በዚያ በኩል ሱዳን አለች ሌሎችም ሀይሎች አሉ ስቴትም አለች”…አሜሪካንን ማለቱ ነው።
 
ኢትዮ-ትግራይ ጦርነት እልቂት እና ኢኮኖሚያዊ ኪሳራን እያስከተለ አንድ አመት ሊሞላው በጣት የሚቆጠር ወራት ቀርተውታል። ቀደም ሲል የኢትዮጵያ ጦር የተናጠል ተኩስ አቁም Unilateral Ceasefire በማድረግ በአብዛኛው ለጦርነቱ ከቶ የነበረውን ሰራዊት ከጦር ቀጠናዋ ትግራይ በማውጣት ግልጽ ወዳልሆነ ስፍራ እንዲሰፍር ተደርጓል። ይህ ሲሆን ጉዳዩ ብዙ ጥያቄዎችን አስነስቷል።
የኢትዮጵያ መንግስት የተናጠል ተኩስ አቁም ሲያደርግ የቅርብ ከበባ የጦር ቀጠና ስፍራ Buffer Zone በመከለል ሰራዊቱ ለምን የትግራይን ሀይሎች ቀጣይ እንቅስቃሴ ለምን ለመጠባበቅ ተሳነው ?
የትግራይ ሀይሎች የደቡብ ጎንደርን፣ የሰሜን ወሎን እንዲሁም ተጎራባች የምእራብ ክፍሎችን እንደ አዲ-አርቃይ ያሉትን ወሳኝ ስትራቴጂክ ቦታዎችን እስኪጠጉ አፋጣኝ ወታደራዊ መኮንኖች እንደሚሉት “ጠብሰቅ” ያለ ወታደራዊ እርምጃ መውሰድ ለምን አልተቻለም?
ሌላው የትግራይ ሀይሎች በክፍለጦር አደረጃጀት በተለይ በአፋር ግንባር በመድፍ ባትሪ የተቀናጀ በባለ ሰንሰለት ታንክ  ፓናርድ የሚርመሰመስበት ጦርነት ሲከፍቱ ኢትዮጵያ መቋቋም ለምን አቃታት ?
በመጀመርያ ደረጃ በጦርነቱ ሙሉለሙሉ የተሸነፈው እና “ተቆራርጦ፣ተሰነጣጥቆ፣ተበታትኖ” በተለይ ቆላ ተንቤን የመሸገው ሀይል ትግራይን ሙሉ ለሙሉ ለቆ በዋሻ እና በተራራዎች አለት ስር ለወራት ሲወሰን በአብዛኛው የታጣቂው ሀይል የተወሰነው በአነስተኛ የእጅ መሳርያዎች እንደሆነ ይታመናል። ለዝያውም ያለበቂ ደጅን ሎጀስቲክ። ታዲያ የኢትዮጵያ መንግስት እራሱ በትግራይ የነበረውን ከባድ መሳርያ ለምን የትግራይ ሀይሎች እንዲታጠቁ ትግራይ ውስጥ ለምን ጥሎ ወጣ ? እነ ደብረ ታቦር በጀነራል መድፍ፣ አፋር በታንክ መቀጥቀጡን ልብ ይሏል።
ከበቂ በላይ ሀይል ያደራጀው የኢትዮጵያ ጦር ኢትዮጵያን ለማተራመስ ለቆረጠው በይበልጥም ጦርነቱን ወደ አማራ እና አፋር መሬቶች ለመውሰድ እቅድ ለነደፈው የትግራይ ሀይሎች እቅድ ለምን ተሸነፈ። የድል ዜና እየተስሰማ ያለው ከብዙ እልቂት ቁሳዊ እና ሰብአዊ ውድመት በሁዋላ ቢሆንም ።ይህን ያህል ዋጋ መክፈል ለምን አስፈለገ ?
እንደ አንድ ተራ ኢትዮጵያዊ ዜጋ ይህንን እጠይቃለሁ።
በሌላ መስመር “ጦርነቱ ለምን ወደ ትግራይ አይመለስም?” ሲል በብርቱ የሚጠይቀው ህብር ሬድዮ፣ ሀሳቡን በሌላ አቅጣጫ ዜናነህም ትኩረት ሰጥቶ ይተነትንበታል።
ጋዜጠኛ ሀብታሙ የኢትዮጵያ ሰራዊትን መረጃ ለህውሐት በማቀበል ኪሳራ መድረሱን አስታውሶ፣ መንግስት የሰራውን ስህተት እና መዘናጋት የትግራይ ሀይሎች ዳግም እንዳያንሰራሩ ተደርገው ተመተዋል መባሉን ያነሳል።
“የጦርነቱ ሁኔታ እየሰፋ ሄዶዋል። የሚሠጠው መግለጫ እና መሬት ላይ የሚሆነው የሰማይ እና የምድር ያህል የተራራቀ ነው። በሚሰጠው መግለጫም የተነሳ ህዝቡ ነቅቶ እንዳይጠብቅ ሆኖ በአፋር እና በአማራ ከባድ ውድመት አስከትሏል። ይሁን እና ይበልጥ ጉዳት ማስከተል የሚፈልገው የህውሐት ሀይል ከፍተኛ ጉዳት እየደረሰበት ነው። መንግስት በሌተናንት ጄኔራል ባጫ በኩል እንኳን ደስ አላችሁ እስከማለት ተደርሷል። ህውሐት ከፍተኛ ጥፋት አድርሷል። ስለዚህ ጦርነቱ እዚህ ደርሷል እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት ተደርሷል እንደዚህ አይነት ድምዳሜ ውስጥ መድረስ ይቻላል ወይ?…”
በማለት ነው አመራማሪ  ሞጋችጥያቄ የሚያቀርበው የህብር ሬድዮ ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ሀብታሙ አሰፋ።
 ተወያዩ አንጋፋው ጋዜጠኛ፣ የመካከለኛውን ምስራቅ ፓለቲካ አብጠርጥሮ በመተንተን የሚታወቀው ዜናነህ መኮንን ነው። ብርቱ የማይደክመው፣ የማይታክተው ጠንካራው ጋዜጠኛ ዜናነህ መኮንን ከኩላሊት ህመም ጋር እየታገለ ከሳምንቱ ቀናቶች ሶስቱን እያሰለሰ ለድፍን አራት ሰአት እጁ ላይ ማሽን ተተክሎ ደሙን እየወሰዱ አጽድቶ ከሚመልስ መሳርያ ጋር ያሳልፋል። ከዚህ በተጓዳኝ ጊዜውን ቀንሶ በሀገሩ ጉዳይ ላይ ንቁ ተሳታፊ ሆኖ እናገኘዋለን።
ዜናነህ ከህብር አዘጋጅ ለቀረበለት ጥያቄ የመጀመርያው ምላሽ ለኢትዮጵያ መንግስት ጠቃሚ አስተማሪም ነው። እንደወታደራዊ ቋንቋ ነገ ይሁን ዛሬ የህውሐት ሀይሎች አዲስ የላንቃዎች ጥቃት የሚፈጸምበት ድንገተኛ ጊዜ “ሰሰአት” አይታወቅም ። ስለዚህ አንጋፋው ጋዜጠኛ በውስጠ-ታዋቂነት መዘናጋት ኢትዮጵያን ያስከፈላትን ዋጋ በማሰብ ይመስላል…”መዘናጋት አስፈላጊ አይደለም” ይላል። ዜናነህ ይቀጥላል… “ለአሁኑ ክርክር ላይጠቅም ይችላል ምክንያቱም ለወዳጅ ወገን ጠቃሚ ስለማይሆን፣ብዙ የምንሰማቸው ነገሮች አሉ ባይሆን ይህንን ወደፊት ልናወራው እንችላለን ወያኔ ብዙ ተመቷል አፋር ላይ ወሎ ላይም ነገር ግን ይህንን እንደ ድል መናገሩ ተገቢ አይደለም።”
የህውሐትን አደገኛም፣አስቸጋሪነትን ሲያመላክት “ወያኔ አፈር ልሶ ሊነሳ ይችላል …”ይሄ ምንም የሚያጠራጥር ጉዳይ አይደለም በማለት ያስረዳል።
 ለዚህ ደግሞ የረጅም ጊዜ ልምዱንም ይጠቅሳል። ፍልስጤም እና እስራኤሎችን ያነሳል። ” ስለዚህ ” በማለት ይቀጥላል…”ስለዚህ በጠላት በኩል ዝምብለን አታሞ የምንመታበት አይደለም ምክንያቱም በዚያ በኩል ሱዳን አለች ሌሎችም ሀይሎች አሉ ስቴትም አለች”…አሜሪካንን ማለቱ ነው።
“የኢትዮጵያን አንድነት ስለማትፈልግ…ደግሞም አይሲስን ያቋቃቋመች ሀገር ነች ያደራጀችም ነች በአንድ እጅዋ ሰላም ትላለች በአንድ እጅዋ ቴረሪስቶችን የምታደራጅ ሀይልአይፈልጉም። ለዜናነህ ትንታኔ ሌላ ሙግት የሚያቀርበው የሬድዮው አዘጋጅ ሀብታሙ አሰፋ አሜሪካ ከሰሞኑ በትግራይ ሀይሎች ላይ የምታሰማውን ” የእርዳታ እህሌን ሰረቁኝ” ስሞታ በማንሳት፣ ይህንን እና መሰል አሜርካ በትግራይ ሀይሎች ላይ ማቅረብዋን በማየት የኢትዮጵያ አንድነት እንዲጠበቅ እንጂ እንዲጠፋ የማትፈልግ መሆንዋን ተቃራኒ ሀሳብ የሚያቀርቡ ወገኖች መኖራቸውን ሬድዮው አንስቷል።
 ዜናነህ ይቀጥላል:-“የአጼ ሀይለስላሴ መንግስት ከፕረዚዳንት ኬኔዲ ጋር ጥሩ ግንኙነት ነበራቸው ነገር ግን ደርግ ከመጣ በሁዋላ አሜርካ የኢትዮጵያን አንድነት አይፈልጉም። Tplf ሲደግፉት የኢትዮጵያን አንድነት ፈልገው አይደለም ። በዚህ ደረጃ በብሄር የተከፋፈለ ህገ- መንግስት ይዞ የቆየ መንግስት መሆኑን እንግሊዞች እና አሜርካኖች ያውቁታል። ወያኔ ዱቄት ሰረቀ ምናምን የሆነ ሳንቲም ወስደህ ወንዝ ላይ እንደመወርወር ነው። እነሱ እንደዛ ሊያስታምሙት ይችላሉ። ስለዚህ ኢትዮጵያዊ መዘናጋት የለበትም። ለኢትዮጵያዊ መፍትሄው ራሱ ኢትዮጵያዊ ነው። “
ዜናነህ በመግቢያዬ ላይ ያነሳሁትን የተኩስ አቁም ጉዳይ በማንሳት አስፈላጊvs አላስፈላጊነቱን በጥልቅ ያነሳል።
“የተኩስ አቁም ስምምነቱ ለኢትዮጵያም የሚበጃትም አይደለም። ደጋግሜ እንዳልኩት ለምን ጦርነቱ ተፈጠረ ነው ?” ሲል ይጠይቃል
“ለምንድነው እነሱ ከሂትለር ጋራ ስምምነት ያልፈጸሙት ?…ለምንድነው ከአፍጋኒስተን ጋራ ስምምነት ያልፈጸሙት ? ተሸንፈው ነው የወጡት። ለሃያ አመታት ያደረሱት ውድመት ቀላል አይደለም…ኢራቅ ውስጥ ያደረሱት!…ለምንድነው ሲርያ ውስጥ ስምምነት የማይፈጽሙት?…አንደኛ tplf ኢትዮጵያዊ አይደለሁም ብሎዋል ከማን ጋር ነው የምትደራደረው ?”
አንጋፋው ጋዜጠኛ ዜናነህ መኮንን የትግራይ ሀይሎች በዳባት የፈጸሙትን ኢ-ሀይማኖታዊ ፕሮፓጋንዳ ሴረኛ ሀሳብ መሆኑን አንስቶ ይተነትናል። ህዝቡን እናንተን አንነካም ችግራችን ከአብይ ጋር ነው ሲሉ ህዝቡን ለማወናበድ የሄዱበትን መንገድ በደርግ ዘመንም ተጠቅመውበት እንደነበር በአጽንኦት ያስታውሳል። ጦርነቱን በእነሱ አውድማ ላይ ማድረግ አለብህ። የመጀመርያ ጦርነቱ ከአማራ ክልል ማስወጣት አለብህ። ጦርነቱን ከተከዜ ማዶ ማድረግ አለበት !! እንዘግበዋለን!!…መገደብ መቻል አለብህ የሰላም ስምምነት የሚባለው ነገር ተወው። የእስራኤሎችን አንድ አባባልም ከዚህ ነጥብ ጋር በማጓደን ይጠቅሳል ሰላም አለ ብሎ የሚያስብ ሰው ካለ እሱ የሰው ፍጥረት ነው ብሎ ለማሰብ ይቸግረናል ይላሉ…”
ጋዜጠኛ ዜናነህ መኮንን የጦርነት ፓለቲካ ጉዳይን ሲተነትነው ስመለከት ያስደንቀኛል። በእውነት ልዩ ኤክስፐርት ነው ምርጥ ጋዜጠኛ ሀገሬ ይህንን ጋዜጠኛ ለምን ይሆን የምትከስረው ? ለምን አሁን ሰው ብሚያስፈልግበት ወቅት በሰው ሀገር ስደት ያለውን ጉምቱ ጋዜጠኛ ለምን አትጠቀምበትም ?
ጋዜጠኛ ዜናነህ መኮንን ከህብር ሬድዮ ጋር ያደረገው ውይይት ሰፊ፣ ጥልቅ እና ግንዛቤን የሚሰጥ ነው። በርካታ ጠቃሚ ጉዳዮች ተተንትነውበታል ሙሉውን እንድትከታተሉት ከዚህ ጽሁፍ ጋር አያየዤዋለሁ ተመልከቱት።
Filed in: Amharic