>

ሰባት ክንፍ ያለው መልአክ እንኳ ብትሆን አንተን አምኜ ለሰከንድ ሽርፍራፊ አብሬህ አልቆምም...!!! (ጎዳና ያእቆብ)

ሰባት ክንፍ ያለው መልአክ እንኳ ብትሆን አንተን አምኜ ለሰከንድ ሽርፍራፊ አብሬህ አልቆምም…!!!
ጎዳና ያእቆብ

የአብይ አህመድ ንግግሮች አንድ አባት በአንድ ወቅት ያሉትን ያስታውሰኛል:: ሀሳሂው መሲህ በባህሪው ሀጢያት ነው ግን ስለ ፅድቅ ቀን ከሌት ይናገራል:: በባህሪው የሰላም ጠላት ነው ግን ቀን ከሌት ስለ ሰላም ይሰብካል:: በባህሪው ጥላቻ ነው ስለ ፍቅር ያወሳል::
ኢትዮጵያዊነት አገልጋይነት መልካምነት ቀናትን በመሰየም ወይም በመምሰል ሳይሆን በመሆን ብቻ የሚመጡ የሚጎለብቱና የሚፀኑ ናቸው:: አብይ አህመድ ሆይ! ማን እና ምን እንደሆንክ እንኳን እኛ ቀርቶ አለም አውቆት ሳለ ዛሬም በንግግር ብዛት ማሳምነው ይኖራል ብለህ እንዲህ አንጀታችንን መጎተትህ ቢቀር መልካም ነው:: ጥሩ ምክር ነውና ውሰደው::
በአንድ ወቅት <<የኢትዮጵያ ፓለቲከኛ እንደሰፈር ዱርዬ ነው:: እንዴት እውነት ተናግሮ እንደሚያሳምን ሳይሆን እንዴት አጭበርብሮ እንደሚያልፍ ነው የሚያስበው>> በማለት እራስህን በሚገባ ገልፀሀል:: በህይወቱ አንድ ቀን የግል ስራ ሰርተህ የማታውቅ ነኝ ብለህ የምታስበውን ሁሉ ካድሬ በመሆን በሴራ ፓለቲካ ውስጥ ከልጅነት እስከእውቀትህ የኖርክ ስለሆንክ ከላይ የገለፅከው ባህሪ ያደግክበትና ጠንቅቀህ የምታውቀው ነው:: እንደሰፈር ዱርዬ ማጭበርበር ብቻ::
ትላንት ዛሬ አይደለምና ኮንቪንስ ወይም ኮንፊውዝድ የሚሆንልህ ኢትዮጵያዊ ቁጥር እየመነመነ መጥቷል:: ዛሬ በዙሪያህ ያሉት የሚታገሉት በሆዳቸው ለጥቅማቸው እንጂ ለአንተ አይደልም:: ሰባተኛው ንጉስ ሆነህ ለሚቀጥሉት ሁለት ወይ ሶስት አስርት አመታት ካንተ ጋር ተጣብቀን እንመዘብራለን ብለው ለግል ጥቅማቸው በዙሪያህ ያሉ እንጂ አማኝ ጠፍቷል:: ምእመናን ቀንሷል::
ቅርንጫፎችህ እየተመለመሉ አንተም ባህሪህ ተገልጦ እርቃንህን ቆመሀል:: ያ ምን ማለት እንደሆነ መገመት ወይም መጠርጠር ትችል ይሆን? ቀኑ ሲያልቅ ከስልጣንህ ወይም ከህይወትህ የቱን ትመርጥ ይሆን? አንድ ሰውና አንድ ጥይት? ወይስ በሀሰት ክምርህ ላይ የቆመ ተስፋ? ማንም ላያምንህ ጉንጭህን ከምታለፋ የጥሞና ጊዜ ወስደህ ብታስብ መልካም ነው::
በማንነታቸው ምክንያት ብቻ የታረዱ ነብሰጡሮችን ደም ፍትህ ከአንተ ትፈልጋለች:: በአማራነታቸው ምክንያት ብቻ የተጨፈጨፉ ህፃናት ደምን ፍትህ ከአንተ ትሻለች:: <<መግደል መሸነፍ ነው>> እንዳልክ የንፁኃንን ደም ስትጋት ለኖርከው ጥላቻ ሲባል ሲፈስ ተሸንፈሀል:: አሁን ያለኸው ጣር ላይ ነው::  ኤርሚያስ ለገሰ አብይ አህመድ የነካው ሁሉ ይሞታል :: እውነት ነው:: በአንድ ወቅት ፈጣሪን ያመሰገንለት አብይ አህመድን ገድለኸዋል::
በንግግሩ የሚያማልለንን አብይ አህመድ ገድለኸዋል::
በተስፋ የሚሞላንን አብህ አህመድ ገድለኸዋል:: አሁን ያለው አልሞት ባይ ተጋዳዩና በጣር ላይ ያለው አብይ አህመድ ነው:: የተናቀውና የምንፀየፈው አብይ አህመድ::
እንኳን አስተካክሎ ሊሰራ ይቅርና በቅጡ ማበላሸት ያቃተው አብይ አህመድ:: በአንድ ወቅት ዶ/ ዳኛቸውን ከማኪቬሊ ምን እንማራለን ብለኸው ነበር:: <<ከመናቅ መጠላት ይሻላል>> ይላል ማኪቬሊ:: መንታ ምላስ: የሰፈር ዱርዬነት: ያመነው እና ሺ አመት ግዛን ያለህን የአማራ ማህበረሰብ ስትክድ ስታስጨፈጭፍ ከመጠላት አልፈህ ተንቀኸል::
ለዚህ ነው እንኳን እንኳን አንተን ወይንም ሆድ አምላኩ የሆኑ ካድሬዎችህን ይቅርና በአገዛዝ ዘመንህ ለማይነገር ሰቆቃ የዳረግካቸውን የአማራ ማኅበረሰብ ወኪሎችን እንኳን ከጎንጅ እንቁም የሚል ጥሪ አንሰማም:: አንቀበልም::
ከጎንህ አንቆምም::
ሰባት ክንፍ ያለው መልአክ ብትሆን አንተን አምኜ ለሰከንድ ሽርፍራፊ አብሬህ አልቆምም::
ኦሮማይ!
Filed in: Amharic