>

 ዐብይ አሕመድና ጦርነቱ፣ ሐበሻን ወደ በሻሻ (መስፍን አረጋ)

 ዐብይ አሕመድና ጦርነቱ፣ ሐበሻን ወደ በሻሻ

መስፍን አረጋ


የወያኔና የአማራ ጦርነት መራዘም ለኦነጋዊው ዐብይ አሕመድ የሚሰጠው ኦነጋዊ ጥቅም ግልጽ ስለሆነ መዘርዘር አያስፈልግም፡፡  ባጭሩ ለመናገር ዐብይ አሕመድ ጦርነቱን ይበልጥ በማራዘም አማራንና ትግሬን ይበልጥ ደም ያቃባል፡፡  በዚህም ሐበሾች ባንድነት ተባብረው የኦነጋውያንን ፀረሐበሻ እቅድ የማክሸፋቸውን ዕድል ይበልጥ የማይታሰብ ያደርገዋል፡፡  በተጨማሪ ደግሞ የሐበሻን ምድር በሻሻ በማድረግ የወደፊቷን ኦሮምያን የመገዳደራቸውን ዕድል ይገድለዋል፡፡  

የኦነጋዊው ዐብይ አሕመድ ዋና ሥራ፣ የቅርብ አማካሪው ሌንጮ ባቲ ኦሮሞ ሦስት ሺ ዓመት ይገዛል ብሎ በትዕቢት የፎከረውን ፉከራ በተግባር መተግበር ነው፡፡  የአማራ ሕዝብ ምርጫ ደግሞ የሌንጮን ፉከራ በፉከራ ብቻ ማስቀረት፣ ወይም ደግሞ በኦሮሞ ወረራ ከምድረ ገጽ እንደጠፉት አያሌ ሕዝቦች ከምድረ ገጽ መጥፋት ነው፡፡  ወደ አፋር ክልል ዝር እንዳይል የተደረገው ወያኔ፣ ወደ አማራ ክልል ባሻው ጊዜ ገብቶ ባሻው ጊዜ እየወጣ የአማራን ሕዝብ ያለ ምንም ተጠያቂነት እንዲዘርፍና እንዲጨፈጭፍ ሙሉ ነጻነት የተሰጠው፣ ዐብይ አሕመድ የነ ሌንጮ ባቲን ፉከራ ለመተግበር በቀመረው ቀመር መሠረት ነው፡፡   

ኦነጋውያን እጅግ ሲበዛ ፈሪወች ናቸው፡፡  እጅግ ሲበዛ ፈሪወች የሆኑት ደግሞ ታሪካቸውን በደንብ ስለሚያውቁ ነው፡፡  ኦነግ ሠራዊት ዕድሜው ከግማሽ ምዕተ ዓመት ያለፈ አዛውንት ሠራዊት ቢሆንም፣ በዚህ ረዥም እድሜው ግን የገጠር ቀበሌወችና አናሳ ከተሞች በድንገት አጥቅቶ ንጹሐንን ጨፍጨፎ ከመሸሽ ባሻገር፣ አንድ ጊዜም እንኳን ፊት ለፊት ተዋግቶም ሆነ አሸንፎ አያውቅም፡፡  አቶ ሰየ አብርሓ ኦነግን ከሳንቲም አንቆጥረውም ያለው የኦነግን ቱሪናፋነት በደንብ ስለሚያውቅ ነበር፡፡    

ሲፍቁት ኦነግ የሆነውን ኦፒዲኦን ለኦነጋውያን የገነባላቸው ወያኔ ሲሆን፣ ሲገልጡት ኦነግ የሆነውን ዐብይ አሕመድን ለስልጣን ያበቃላቸው ደግሞ የአማራ ሕዝብ ነው፡፡  ስለዚህም ለራሳቸው በራሳቸው ምንም ማድረግ የማይችሉት ኦነጋውያን፣ ዓላማቸውን ለማሳካት ያቀዱት ሐበሻን ርስበርስ በማጨፋጨፍ መሆኑ ምንም አያስገርምም፡፡  

ፊሪ ሰው የፈሪነቱን ያህል ጨካኝ ነው፡፡  የኦነጋውያን ዓይነት ወደር የለሽ ፈሪ ደግሞ ጭካኔው ወደር የለውም፡፡  ኦነጋውያን የአማራን ሕዝብ በተለይም ደግሞ በደንብ ስለሚያውቃቸው ሆ ብሎ ከተነሳባቸው ቁርስ የሚያደርጋቸውን የሺዋን አማራ አለቅጥ ይፈሩታል፡፡  ከፍራቻቸው የተነሳ አማራ ቢሞት እንኳን መቃብሩን ፈንቅሎ ይመጣብናል የሚለው ስጋታቸው እንቅልፍ ይነሳቸዋል፡፡  ስለዚህም የአማራ ሕዝብ መቸም ላይነሳ ሙቷል ብሎ በርግጠኝነት እስከሚያምን ድረስ፣ ዐብይ አሕመድ ባማራ ምድር ላይ የሚካሄደውን ጦርነት በቀጥታና በተዛዋሪ መንገድ ያስረዝመዋል፡፡  

ይህ ጦርነት የሚጠናቀቀው፣ ወይ ዐብይ አሕመድ ሲወድቅ ወይም ደግሞ አማራ ሲያልቅ ብቻ ነው፡፡  የዐብይ አሕመድ መውደቅ ወይም የአማራ ማለቅ የሚወሰነው ደግሞ በኦነግ ወይም በወያኔ ሳይሆን በአማራ ድክመትና ጥንካሬ ብቻ ነው፡፡  የአማራ ሕዝብ ከዐብይ አሕመድ አፍዝ አደንግዝ ከተላቀቀ፣ ወያኔና ኦነግ እዳቸው ገብስ ነው፡፡ 

ወያኔ የኢትዮጵያ ችግር ዋናው ምንጭ የነበረው፣ ፈላጭ ቆራጭ በነበረበት በ 27 ዓመቱ የመከራ ዘመን እንጅ ባሁኑ ጊዜ አይደለም፡፡  እደግመዋለሁ፣ አንዳንድ ሰወች ሊነግሩን እንደሚፈልጉት ባሁኑ ጊዜ የኢትዮጵያ ችግር ዋናው ምንጭ ወያኔ አይደለም፡፡  ባሁኑ ጊዜ የኢትዮጵያ ችግር ዋናው ምንጭ የወያኔን ዘረኛ ሕገመንግሥት እንዳለ በማሰቀጠል፣ የትግሬን የበላይነት በኦሮሞ የበላይነት የተካው ጎጠኛው፣ ሸፍጠኛውና ዐምባገነኑ ዐብይ አሕመድ ዓሊ ነው፡፡  ዓይኑን በጨው አጥቦ የሚዋሸው፣ ትናንት የተናገረውን ዛሬ የሚቃረነው፣ በማንነቱ ምክኒያት በሥርሰደድ (chronic) የስነልቦና በሽታ የሚሰቃይ የሚመስለው ኦነጋዊው ዐብይ አሕመድ ከስልጣን ተወግዶ ብቁ፣ ቅን እና አገር ወዳድ በሆነ መሪ ከተተካ፣ የወያኔና የሸኔ ዕድሜ ከሳምንታት አያልፍም፡፡  አቶ ልደቱ አያሌው ወያኔን ባለማውገዙ እንጅ፣ ባሁኑ ጊዜ የኢትዮጵያ ዋና በሽታ በሽተኛው ዐብይ አሕመድ ነው በማለቱ ምንም አልተሳሳተም፡፡         

መስፍን አረጋ:- Email: mesfin.arega@gmail.com

Filed in: Amharic