>

አንዳንድ የወደፊት ውታፍ ነቃዮች (እኔ Willful Fools የምላቸው) የሚሉት አስቂኝ ሃረጎች አሏቸው፦ (ዶ/ር ዮናስ አበራ)

አንዳንድ የወደፊት ውታፍ ነቃዮች (እኔ Willful Fools የምላቸው) የሚሉት አስቂኝ ሃረጎች አሏቸው፦
ዶ/ር ዮናስ አበራ


*….  “ከአብይ ጋር በብዙ ነገር ባልስማማም….. አብይ ከእነ ጥፋቱም ቢሆን….. አብይን በብዙ ድርጊቶቹ ብጠላውም….. ይሉና ጥሩ ሲሰራ ጥሩ ሰርተሃል ማለት ተገቢ ነው….. ያለማድነቅ ንፉግነት ነው” የሚል ይጨምሩበታል። ይሄ መርመጥመጥ ይባላል!!
ሰሞኑን ሌላ ተጀምሮልሃል ደግሞ “ከአብይ ሌላ ምን አማራጭ አለን? እሺ ከእሱ የተሻለ ማን አለ? ማን ጠ/ሚርነቱን ይያዝ ትላለህ” ከሚል ሽባ አስተሳሰብ ወደ “አሁን ወያኔ ላይ ነው ማተኮር፣ አብይ ይደርሳል” ወደሚል ለጅልነት የቀረበ የዋህነት ተሸጋግረናል።
 እንደዚህ ከሚሉ፥ የፖለቲካው አስኳል በቅጡ ካልገባቸው ሰዎች ጋር ፖለቲካ ማውራት ብቻውን ብርድልብስ የማጠብ ያክል አሰልቺ ነው።
“መጀመሪያ የሰሜኑን ጉዳይ እናጠናቅ፥ ከዚያ በአንድ ልባችን በጋራ አብይ ላይ እንዞራለን Be pragmatic!!” ይሉሃል
“ታዲያ ጦርነቱ ካለቀ ወደ አብይ ልትዞር መሆኑን ካመንክ እና እሱም ይሄንን ካወቀ (በደንብ አውቋልም) ጦርነቱን እራሱ አብይ ለራሱ ህልውና ሲል ያራዝመዋል እኮ፥ እያየነውም ያለው እኮ ይሄንን ነው!” ስትለው ጥፍሩን እየበላ ወደላይ አንጋጦ አምፖል አምፖል ያያል።
“ሞተ፥ አበቃለት የተባለው ወያኔ ተንሰራርቶ፣ አቆጥቁጦ እዚህ እስኪደርስ ቆሞ ያየውና ለዚህ ያበቃው እራሱ አብይ አህመድ አይደለም ወይ? በተደጋጋሚ 72 ሰዓት ሰጥነችኋል እያለ time እንዲያገኙ፥ ምሽግ እንዲሰሩ ያደረገው እራሱ አብይ አይደለም ወይ? የጦር መሳሪያ ጥሎላቸው እየወጣ አፍንጫቸው ድረስ ያስታጠቃቸው እራሱ አብይ አይደለም ወይ?” ካልከውማ “በቃ ስለሌላ ነገር እናውራ ባክህ” ይልሃል።
ኧረ ኤዲያልኝ!! መርመጥመጥ ብቻ!! ሰው እንዴት እርም አይልም
Filed in: Amharic