>

"አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ የያዘችው አቋም ምስራቅ አፍሪካ ላይ ሽብርተኝነትን የሚያስፋፋ ነው...!?!"  (የህግ ባለሙያው አቶ ውብሸት ሙላት ገለፁ)

“አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ የያዘችው አቋም ምስራቅ አፍሪካ ላይ ሽብርተኝነትን የሚያስፋፋ ነው…!?!”
 የህግ ባለሙያው አቶ ውብሸት ሙላት ገለፁ

አቶ ውብሸት ሙላት በተለይ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለፁት አሜሪካ ሽብርተኝነትን በግልጽ እንደሚዋጋ ሲናገር ቢቆይም የኢትዮጵያ መንግሥት ሽብርተኛ ብሎ የፍረጀውን የህወሓት ቡድን መደገፉ በምስራቅ አፍሪካ ሽብርተኝነትን የሚያስፋፋ ነው።
አሜሪካ አሸባሪውን ህወሓት መደገፏም ሽብርተኝነትን ለመዋጋት ያላትን ቁርጠኝነት ጥርጣሬ ውስጥ የሚከት ነው ያሉት የህግ ባለሙያው አሜሪካ የወሰደችው አቋምም ሽብርተኝነትን ለመዋጋት የወጡ ዓለም አቀፍ ህጎችንና ስርዓቶችን የሚጥስ ነው ብለዋል።
ኢትዮጵያ ሉዓላዊት አገር በመሆኗና በሀገሪቱም ፓርላማ የተወሰነውን የህወሓትን የሽብር ድርጊት አክብሮ መቀበል ከአሜሪካም ሆነ ከሌሎች ምዕራባውያን ሀገሮች የሚጠበቅ ኃላፊነት ነው ያሉት አቶ ውብሸት ከዚህ በተቃራኒ የሚወሰድ የሽብር ቡድኑን የሚደግፍ አካሄድ አካባቢው ላይ ሽብርተኝነት እንዲነግስ በር የሚከፍት መሆኑን አመልክተዋል።
Filed in: Amharic