>

ለአገር ውስጥ ተፈናቃዮች ፈጣንና ዘላቂ መፍትሔ ያሻል‼ (ኢሰመጉ)

ለአገር ውስጥ ተፈናቃዮች ፈጣንና ዘላቂ መፍትሔ ያሻል‼

 አስቸኳይ ጋዜጣዊ መግለጫ፣ ከኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ‼

 

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ (ኢሰመጉ) በሀገራችን በሁሉም አካባቢዎች ያሉትን የሰብዓዊ መብቶች ሁኔታ በዋናው  ጽ/ቤት፣ ባሉት ስምንት የቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች እና በመላው ሀገሪቱ በሚገኙት አባላቱና ደጋፊዎቹ አማካኝነት በቅርብ እየተከታተለ የተለያዩ ይዘት ያላቸውን የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት ዘገባዎችን ሲያወጣ ቆይቷል አሁንም በማውጣት ላይ ይገኛል፡፡
በሀገራችን ኢትዮጵያ በዜጎች ላይ በሚደርሰው ጥቃት ምክንያት ከመኖሪያ ቀያቸው ተፈናቅለው በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ ይገኛል ይህም ኢሰመጉን በእጅጉ ያሳስበዋል፡፡ ስለሆነም የሚመለከታቸው አካላት በሙሉ በቂ ትኩረት በመስጠት አፋጣኝ እና ዘላቂ መፍትሔ እንዲያበጁ ሲያሳስብ መቆየቱ ይታወሳል። የህውሓት ታጣቂ ኃይሎችን ጨምሮ በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች እየተንቀሳቀሱ ያሉ የታጠቁ ኃይሎች በንጹኃን ላይ በሚያደረሱት ተደጋጋሚ ጥቃት ምክንያት ከሰሜን ወሎ፣ ከደቡብ ወሎ፣ ከሰሜን ጎንደር፣ ከደቡብ ጎንደር፣ ከአፋር እንዲሁም ከቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ ከኦሮሚያ ክልል ከአንዳንድ አካባቢዎች፣ ከደቡብ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች፣ ከሶማሌ ክልል፣ በትግራይ  ክልልና ከተለያዩ የሀገራችን አካባቢዎች ቤት ንብረታቸው የወደማበቸውና ቀያቸውን ለቀው ተፈናቅለው በመጠለያ ጣቢያዎች እና በተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ የአገር ውስጥ ተፈናቃዮች ሁኔታ እጅግ አሳሳቢ ደረጃ ላይ እንዳለ ኢሰመጉ ቀደም ብሎ ሲያደርግ በነበረው የሰብዓዊ መብቶች ሁኔታ ክትትልና ካሰባሰባቸው መረጃዎች ለመረዳት ችሏል፡፡ ታጣቂዎቹ ባደረሱት ጥቃት  ምክንያትም ሕክምናን ጨምሮ የተለያዩ አገልግሎቶች የሚሰጡ መሰረተ ልማቶች ከጥቅም ውጪ መሆናቸውን እና ተፈናቃዮቹ የምግብ፣ የውኃ፣ የመጠለያ እና የህክምና አቅርቦት ችግር ውስጥ እንደሚገኙ ለማወቅ የተቻለ ሲሆን፤ ከተፈናቀሉት ሰዎች ውስጥ ሕፃናት፣ ሴቶች፣ አረጋውያን እንዲሁም የአካል ጉዳተኞች እንደሚገኙና ያሉበት ሁኔታም አሳሳቢ መሆኑን ኢሰመጉ ተገንዝቧል፡፡ በሌላ በኩል በአሁኑ ወቅት ስልክና ሌሎች የኤሌክትሮኒክስ የመገናኛ ዘዴዎች አገልግሎት መስጠት በማቆማቸው ተፈናቃዮቹ አሁን ላይ ያሉበትን ሁኔታ በተገቢው ሁኔታ ለመከታተል አዳጋች ሆኗል…
Filed in: Amharic