የጅቡቲ ነገር ብርቱ ጥንቃቄ ያሻዋል… !?!
(መስቀሉ አየለ)
“በጥቂት ሳምንታት ውስጥ በአፋር በኩል ወርዶ ወደቡን ይቆርጣል” የተባለው የትግራይ ወራሪ ተውሳክ እንደ አዋሽ ወንዝ አሸዋ ላይ ሰምጦ ሲቀር ሃያ አምስት ያህል የሲ-አይ-ኤ ባለስልጣናትን አስከትሎ ሲገሰግስ ጅቡቲ የገባው የባይደን ልዩ መልእክተኛ ጀፈሪ ፊልትማን በግዜው ያንን ሁሉ ግርግር የፈጠረበት ምክንያት አማርኛን አቀላጥፎ ከሚናገረውና ድሬዳዋ ከተወለደው የጅቡቲው ፕሬዝዳንት ምን ተፈልጎ እንደነበር የተለያዩ መላምቶች ሲሰነዘሩ ከርመው ነበር። ይህ ከሆነ አንድ ወር ባልሞላ ግዜ ውስጥ ደግሞ የጅቡቲው ፕሬዝዳንት እስማኢል ኦማር በድንገት ታመመ ተብሎ ከትናት ወዲያ ለከፍተኛ ህክምና ወደ አውሮፓዊቷ ፈረንሳይ ማቅናቱ የተነገረ ቢሆንም ነገር ግን አርባ ስምንት ሰዓት ባልሞላ ግዜ ውስጥ እንደገና የፈረንሳይ ከፍተኛው የውጭ ጉዳይ ልዑክ በዛሬው እለት ጅቡቲ የደረሰው “ሌላ አሻንጉሊት መሪ ለማንገስ ይሆን ወይ ” ብሎ መጠየቅ የእኛ ፋንታ ነው። አንዳንድ ሚዲያዎች ሰውየው “ሳይመረዝ” እንዳልቀረ እየዘገቡ ሲሆን ይህ ነገር መስመሩን ስቶ ሰውየው በህይወት ባይመለስ ግን በቀጠናው በተለይም በኢትዮጵያና በኤርትራ ላይ የሚኖረው አንድምታም ሆነ በአጠቃላይ የቀጠናው የሃይል አሰላለፍ እንዲሁም በጸረ ወያኔ ትግሉ ላይ የሚደቅነው immediate ፈተና ምን ያህል ይሆናል ? ወዘተ… ወዘተ የሚሉት ጥያቄዎች አዲስ አበባና አስመራ ላይ አስቸኳይ መልስ ይፈልጋሉ::
ባለፈው ሰሞን መሰረታቸው ኮሎምቢያ ውስጥ የሆነና በንዘብ የተገዙ ቅጥረኛ ነፍሰገዳዮች በውድቅት ሌሊት መኝታው ቤት ድረስ ዘልቀው በመግባት የሃይቲውን ፕሬዝዳንት በተኛበት ከእነባለቤቱ ገድለው በመሰወራቸው ድፍን የላቲን አሜሪካ ህዝብ ጣቱን በማን ላይ ሲቀስር እንደከረመ ለተከታተለ ሰው የዘፈን ዳርዳሩን መለየት አይችርግረውም….ወገኔ ሰዎቹ እንዳበደ ውሻ አድርጓቸዋል;;
“አባይ ወንዛወንዙ …
ብዙ ነው መዘዙ” አለች ጅጅ……