የነውረኛ ፓርቲ ነውረኛ ቀልድ…!!!
ጎዳና ያእቆብ
በአሸባሪነት ዘመኑ ለፈፀማቸው ወንጀሎች ለፈሰሰው የንፁኃን ደም በማንነታቸው ብቻ ለቀጠፉት ወይም ለተባበሩት ማንነት ተኮር ጭፍጨፋ ለወደምው ንብረት የህግ ተጠያቂነት ሳይኖር ያውም ተራና ተርታ የሆነን ሳይሆን <<ዋና አዛዥ>> የሆነን ግለሰብ <<ሰላማዊ ትግልን ተቀላቀሉ>> የሚል ቀልድ ደስ የምትል የበለፀገች ቀልድ ናት::
ዘንድሮ የዘር ጭፍጨፋ ፈፅሞና ሀገር አውድሞ በነፃ ለመለቀቅ <<ምርጫው ዴሞክራሲያዊ ነው>> ማለት በቂ ነው:: ለነገሩ አብይ አህመድ በአደባባይ << ህዋሃቶችን በመደበኛም ይሁን በኢ-መደበኛ መንገድ የዘረፋችሁትን ይዛችሁ ብልፅግና ተቀላቀሉ ስንላቸው እምቢ በማለት እስትራቴጂካዊ ስህተት ፈፀሙ::>> ብሎ የትግራይ ዘምቻ ህዋሃትን በሚገብሩ ኃይላት ለመተካትና ትግራይን ለማበልፀግ እንጂ <<የህግ ማስከበር ዘመቻ>> እንዳልሆነ በአደባባይ ነግሮናል::
በዙሪያው የሰበሰባቸው የትላንት ኢህአዴግዎች የወንጀለኛ ጥርቅሞች ናቸው:: አብይ አህመድን ሙሴአችን ብለው በመቀበል ከሀጢያታቸው ሁሉ ነፅተው ዳግም ህዝብን በመዝረፍ የታደሱ ወንጀለኞች ሆነው የቀጠሉት::
ብልፅግና ከቻለ በህጉ ፋውል ሳይሰራ እንደሚጫወት ካልቻለም ደግሞ ዳኛው ሳያይ ፋውል የሚሰራ: ያም አልበቃ ወይም አላዋጣ ካለ ደግሞ ዳኛው እያየ ፋውል የሚሰራ መርህ አልባ የማፊያ ድርጅት እንጂ ሀገር ማስተዳደር የሚችል ፓርቲ አይደለም:: ለነገሩ ፓርቲውም እንኳን እስካሁን የፓለቲካ አደረጃጀት የግድ የሚለውን አጠቃላይ ጉባኤ እንኳን ያላደረገና ለማድረግም ሀሳብ የሌለው ህገ ወጥ ፓርትጅ ነው:: እድሜ ለሚደቅሳ ልጅ ወይዘሪት ብርቱካን ጉባኤ አድርጎ አመራሮቹን ላልመረጠ ድርጅት ህጋዊ ሰርተፍኬት በምርጫ እንዲሳተፍ ያደረገችው::
ህግ አለርጂኩ ለሆነ ድርጅት ህጋዊ ሰውነት መስጠት የሚገርም ቢሆንም አመራር በመስጠት ንፁኃንን ሲያሳርድ ንብረት ሲያወድምና አገር ሲያሸብር የነበረን ግለሰብ ብልፅግና አሞግሷልና ካለምንም የህግ ተጠያቂነት <<ሰላማዊ ትግል ተቀላቅሏል>> የሚል ነውረኛ ፓርቲ ነው:: የኢፌድሪ ህገ መንግስት እንኳን በነብስ ግድያ ቶርቸር የዘር ማጥፋት ወይም በሰብአዊነት ላይ ወንጀል ለፈፀመ ይቅርታም ይሁን ምህረት በግልፅ የሚከለክል ቢሆንም ይህ ሰው በስሙ የሚምሉበትና በመቃብራችን ላይ ነው የሚለወጠው የሚሉት ህገ መንግስታዊ ድንጋጌ ተጥሶ ይቅርታም ምህረትም ተሰጥቶታል::
ትንሽ ጊዜ ከሰጠናቸው ገንዘብ ቤትና ሹመቱ የማይቀር ነው:: ይህ ውርደትና ህገወጥነት ነው የብልፅግና ዘመን! ከፊታችን ያለችው ኢትዮጵያ ታጓጓለች የሚባልላት ሀገር በህገ ወጦችና በወንጀለኞች የምትመራ ናት!! መልካም የብል[ፅ]ግና ዘመን:: መቼም በዚህ ደረጃ. ወንጀለኛ የሆነ ፓርትክ እድሜው አጭር እንደሆነ ግልፅ ነው::