>

"የኢትዮጲያ ሁኔታ ያስፈራኛል... !!!" የተመድ ዋና ጸሀፊ አንቶኒዮ ጉታሬዝ ለአልጀዚራ ከተናገሩት (ወንድወሰን ተክሉ)

“የኢትዮጲያ ሁኔታ ያስፈራኛል… !!!”

የተመድ ዋና ጸሀፊ አንቶኒዮ ጉታሬዝ ለአልጀዚራ ከተናገሩት.
 
«በየኢትዮጲያው ጠ/ም/ር አቢይ አህመድ ውሸት በእጅጉ አፍሬያለሁ……….አጠቃላይ የኢትዮጲያ ሁኔታ እጅግ ያስፈራኛል….”
ወንድወሰን ተክሉ

፠ በአጠቃላይ ኢትዮጲያ ችግሮቿን መፍታት ባለመቻሏ በእጅጉ አዝኛለሁ -በእጅጉም ሰግቻለሁ፦
የአልጀዚራው ጋዜጠኛ በቅርቡ ለተመድ ዋና ጸሀፊነት ለቀጣይ አምስት ዓመት እንዲመሩ ለሁለተኛ ጊዜ የተመረጡትን አቶኒዮ ጉታሬዝ በዓለም ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ የግማሽ ሰዓት ቃለመጠይቁ ላይ የኢትዮጲያን ጉዳይ በማንሳት ጠይቌቸዋል።
፨ ጋዜጠኛው «የኢትዮጲያው ጠ/ም እቢይ አህመድ የኤርትራ ወታደሮች ትግራይ አልገቡም ብሎት ነበር። ሆኖም የኤርትራ ወታደሮች ግን ገብተው ንጹሃንን ሲጨፈጭፉ ሲደፍሩና ሲዘርፉ መሆናቸው ሲረጋገጥ በአቢይ ውሸት አላዘኑም?? »
፨ የአንቶኒዮ ጉታሬዝ መልስ « በአጠቃላይ በአቢይና በሀገረ ኢትዮጲያ ጉዳይ በእጅጉ አዝኛለሁ-አዝናለሁ። ኢትዮጲያ ያጋጠሟትን ውስጣዊ ችግሮችን መፍታት ያለመቻሏ እጅግ ያሳዝናል – በእጅጉም ያስጨንቃል። እንደ ኢትዮጲያ አይነት ብዙ ህዝብ ያለው ትልቅ ሀገር ችግሮቹን መፍታት አቅቶት ቢፈነዳ በአጠቃላይ በአካባቢው ሊከሰት የሚችለውን ሰብዓዊ ቀውስ በእጅጉ ያስፈረሃል። እናም አጠቃላይ የኢትዮጲያ ሁኔታ ያስፈራኛል። »
፨ ጋዜጠኛ  «በአንድ ወቅት አሜሪካዊው ጄፍሪ ፌልትማን  ኢትዮጲያ ወደ ሶሪያ አይነት መንገድ እየተጔዘች ነው።ሁኔታቸውን እንደሶሪያዊያን ሁኔታ የህጻናት ጦርነት/ቀልድ አይነት እያደረጉት ነው ብሎ ተናግሮ ነበር።
ኢትዮጲያ እንደሶሪያ የመሆን አደጋ ያጋጥማታል ብለው ያምናሉ??»
፨ የአንቶኒዮ ጉታሬዝ መልስ «ኢትዮጲያዊያን የእርሰበርስ ግጭታቸውንና ዘርፈ ብዙ ችግሮቻቸውን  በጦርነት ከመፍታት ይልቅ ቁጭ ብለው በውይይትና በድርድር መፍታት አለበቸው ብዬ አምናለሁ። ግን ይህንን እይታ ሁለቱም ኋይሎች የገዙት ሀሳብ አይመስለኝም። ባለን መረጃ መሰረት ሁለቱም ጦርነቱን በአሸናፊነት ለመወጣት እንደሚችሉ ያመኑ ናቸው። በእኛ በኩል ግን በሁለቱም ወገን ጦርነቱን አሸናፊ ሆኖ በመውጣት መፍትሄ ያደርጉታል ብለን አናምንም።  ወታደራዊ እርምጃ በአጠቃላይ መፍትሄ አይደለም።
ድራማው ግን የቀጠለ ቢሆንም አንዱ አንደኛውን በወታደራዊ ኋይል ማሸነፍ የሚችል አለመሆኑን ነው የሚታየው። መንግስት ወያኔዎቹን ማሸነፍ አይችልም። ትግራይ ድረስ ዘልቆ ሙሉ በሙሉ ማሸነፍ እንደማይችል በወያኔዎቹ ብርቱ ተዋጊነት ሃይለኝነት ህዝቡን አስተባብረው ተዋጊነታቸው በግልጽ ያሳዩ ናቸውና ጦርነቱን በአሸናፊነት መወጣት አይቻለውም።
በሌላ በኩል ደግሞ ወያኔዎች የቱንም ያህል በውጊያ ቢበረቱና ቢያይሉም አጠቃላይ ኢትዮጲያን ዳግም ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥረው መግዛት የሚችሉም አይደሉም። ኢትዮጲያዊያኖች በወያኔ ዳግመኛ ለመገዛት ፈቃደኞች አይደሉም።
ይህ ሁኔታ ወታደራዊ ኋይልና እርምጃ መፍትሄ ሊያመጣ እንደማይችል በተጨባጭ ያሳያል። ስለዚህም ብቸኛው መፍትሄ ሁለቱም ቁጭ በለው በውይይትና በድርድር መፍታት አለባቸው። እንንደ አለመታደል ሆኑ ከሁለቱም በኩል ለዚህ ዓይነቱ መፍትሄ ዝግጁነት እየታየ ያለመኑ ጉዳይ ነው።
የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦት መስመርን መከፈትን ተከትሎ ይህ አይነቱ ውይይትና ድርድር ይጀመር ይሆናል በሚል ተሰፋ የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦትን መተላለፊያ መስመር መከፈትን ለውይይትና ድርድር በር ይከፍታል ብለን በተስፋ እንድናይ አድርገናል።
የሆነው ሆኖ ሁለቱም ወገኖች መሳሪያዎቻቸውን አስቀምጠው እራሱ የኢትጾጲያ መንግስት የሚመራው ውይይትና ድርድር ብዙም ሳይርቅ በቅርቡ ይጀመራል-ወይም መጀመር አለበት ብለን በጽኑ እናምናለን።
ይህ ሳይሆን ሲቀር የጄፍሪ ፌልትማን ኢትዮጲያ ሶሪያ ትሆናለች ስጋት እውን የማይሆንበት ምክንያት አይታየኝም።
በኢትዮጲያ ውስጥ ያለውን እጅግ ዘርፈ ብዙ ችግሮች መፍታት ያለመቻል በእጅጉ ታላቅ ስጋት ደቅናል። የጠ/ም አቢይ መንግስትና እንደ ሀገርም ኢትዮጲያ ችግሮችን መፍታት ያልቻሉ ሆነዋል። Ethiopia failed to solve its internal problems ይህ ማለት ደግሞ ሀገሪቷ የሲሪያ እጣ እንደ አደጋ ተጋርጦባታል ማለት ነው። እናም በእጅጉ አዝኛለሁ – በእጅጉም  ስለኢትዮጲያ እሰጋለሁ
 The collapse of Ethiopia means  a disastrous to the entire region and tragic for Ethiopians …..»   በማለት መልሰዋል።
   ፠፠፠      ፨፨፨     ፠፠፠
፠ ለእኛ ያልታየው የሀገራችን ያለችበት አደጋና ህዝባችን እያየ ያለበት ሁኔታ፦
የእኛ የኢትዮጲያዊያን ሁኔታ ከእኛው ከባለቤቶቹ ኢትዮጲያዊያን በላይ የዓለም አቀፉን ማህበረሰብ ያስፈራና ያስጨነቀ ሆኖ ሳለ የኢትዮጲያዊያኑን እይታና አረዳድ ስንመለክት ግን ልክ እንደዘመነ ኖህ የጥፋት ውሃ ክስተት ኖህ ከማንም ቀድሞ ከጎርፍ መዳኛ መትከብ ሲሰራ ህዝቡ እየተሳለቀበት ይሰድበው ያንጔጥጠውና ይሰለቅበት ነበር።
የጥፋት ውሃን የፈጠረው ዝናብ መዝነብ ሲጀምርና ጎርፉም እያደገ እያየለ ሲጨምርም ህዝቡ ከደስታና ከዳንኬራቸው ባለመታቀብ ጭፈራውን ያቀለጡት ነበርና አስረሽ ምቺው ለመባል ቻሉ።
በሁለተኛ ደረጃ  ሞኝ ሲመታ ብልህ ያመዋል ሞኝ የሙዝ ዛፍ አናት ላይ ሲወጣ ምድር ላይ ያለው ብልህ ይጨነቃል እንደሚባለው የአብዛኛውን ኢትዮጲያዊ ማህበረሰብ የማስተዋል እይታን የጋረደ ወይም የነጠቀ ኋይልና ወገን ያለበሚመስል ሁኔታ ህዝቡ ማስተዋሉን ተነጥቆ በገደል አፋፍ ላይ እየተንጎማለለ አፉን ከፍቶ የሚጠብቀውን ገደል የማያይ መስሎ ያለበት ሁኔታ ላይ ነን ያለነው።
አለም ስለእኛ ተጨንቆ ስምንት ግዜ ያህል የጸጥታው ምክር ቤት በኢትዮጲያ ጉዳይ ሲመክር ሲዘክር እኛ ኢትዮጲያዊያን ግን ይህ የውጪ ኋይሎች ወረራ ነው። የውጪ ኋይሎች ጣልቃ ገብነት ነው ውስጣዊ ችግሮቻችንን በራሳችን አቅምና ብቃት መቆጣጠር እንችላለን። ችግራችንም እናንተ የውጪ ኋይሎች ሀገራችንን እንደሊቢያ ሲሪያና የመን ለማፈራረስ ያሴራችሁት ሴራ ነው እያልን በድፍን ጅምላዊ ፍረጃ ስናወግዝና ስንተች የምንታይ ሆነናል።
የተመድ ዋና ጸሀፊ አንቶኒዮ ጉታሬዝ በአፍጋኒስታን ጉዳይ የታሊባን ወደስልጣን መመለስን ተከትሎ ምናልባት ታሊባኖች ሀገሪቱን በአግባቡ መምራት ካልቻሉ የህዝብ ቅፍለት ይፈጠራል በሚል ጭንቀት ውስጥ መግባታቸውን አልሸሸጉም።
በኢትዮጲያ ጉዳይ ጣልቃ ለመግባት እየሞከሩ ያሉት አሜሪካና ሸሪኮቿ ምእራባዊያን ለጣልቃ ገብነታቸው መንስኤ አድርገው ያቀረቡት አንዱና ዋነኛው ይህንን ውስጣዊ ጦርነት በአስቸኴይ አቁመን ወደ ውይይትና ድርድር የማንመጣ ከሆነና ግጭቱን በወታደራዊ ኋይል እንፈታለን ብለን ጦርነቱን የምንገፋ ከሆነ ኢትዮጲያ የመበታተን (የመፍረስ ) እጣፈንታ ያጋጥማታል።  የኢትዮጲያ መፍረስ ማለት ደግሞ -ማለትም የ117ሚሊዮን ህዝብ ሀገር መፍረስ ማለት ሊፈጠር የሚችለውን ሰብዓዊ ቀውስ ግዝፈታ የተነሳ ከአፍሪካ ቀንድም አልፎ በመካከለኛው ምስራቅ በአውሮፓና በአሜሪካ ቤሉት ሀገራት ላይ ታላቅ ጫናን የሚፈጥር ነው። በዚህም ግንባር ቀደም ተጎጂ ኢትዮጲያዊያኖች ቢሆኑም ጉዳቱ እኛንም ያጠቃልና ይህ ጉዳት ከመፈጠሩ በፊት ማስቆም አለብን በሚል አሜሪካና ምእራባዊያን ጣልቃ ለመግባት ሲሞክሩ የእኛ ገዢዎች ግን «የለም አማሪካ ኢትዮጲያን ሊቢያ ሲሪያና የመን ለማድረግ ነው የተነሳቺው » የሚል ታፔላ ገጥመው በመጮሃቸው መንጋውም ሆነ ተጎጂውም ህዝብ ምንም ሳይገባው አሜሪካ እጅሽን ከኢትዮጲያ አንሺ እያለ የሚጮህና በገዢዎቹ ምሪት እርሰበርስ ለመጨራረስ የወሰነ መስሏል።
ዓለም እንዳትፈርሱ ሲለን እኛ ደግሞ ምን አገባችሁ ፍርስርሳችንም ይውጣ እያልን ያለን ህዝብ መስለናል።
በኢትዮጲያ መፍረስ ጥቅማቸው እንደማይነካ የሚያውቁትና ስደተኞችን ተቀብሎ የማስተናገድ ታሪክ የሌላቸው ራሺያ ቻይና እና ህንድ በጸጥታው ምክር ቤት ለኢትዮጲያ ያሰቡ እየመሰሉ በሚያስተላልፉት ውሳኔ ተመድ መጫወት የሚገባውን ሚና እንዳይጫወት ችላል።
በነገራችን ላይ የመንግስታቱ ድርጅት የስደተኞች ጉዳይ ኮሚሽን UNHCR  ቌሚ ደንበኛ ሆነው በየዓመቱ ስደተኛን ከመላው ዓለም በመውሰድ ላይ ያሉ ሀገራት
፨አሜሪካ
፨ካናዳ
፨እንግሊዝ
፨ኖርዌይ
፨ስዊድን
፨ሆላንድ
፨አውስትራሊያ
፨ኒውዝላንድ
፨ፊንላንድ
ብቻ ናቸው።
Filed in: Amharic