>

ጦርነቱ ለምን መቆም አለበት....!!! (ሚልዮን አየለች)

ጦርነቱ ለምን መቆም አለበት….!!!

ሚልዮን አየለች

The war should not stop for the sake of the United States, but for the future of Ethiopian citizens
ብዙዎች ጦርነቱ ይቁም ስንል የአሜሪካንን ሀሳብ ተስማምተን አልያም የአውሮፓ ህብረት ሊቀመንበርን ደግፈን ይመስላቸዋል። አልያም ለባለ ትንንሽ አይምሮዎች እና ከሀሳብ ይልቅ መፈረጅ ለሚያምራቸው ንንንሾች የህወሃትን አካሄድ እየደገፍንም ይመስላቸዋል።
አሜሪካ ጦርነቱ ይቁም ወደሰላማዊ ድርድር ልትመጡ ይገባል በላዩ የጦርነቱ አካሄድ አሳስቦኛል ስትል ከብሔራዊ ጥቅሟጋር አመዛዝና ነው ሲቀጥል በቀጠናው ላይ የምትከተለውን የውጪ ፖሊሲዋን የሚያደናቅፍ ባትን እንከን ላለመፈለግ ነው።
ድርድሩን የምናካሄደው አሜሪካን በቀደደችልን ቦይ ከሆነ አደጋው ለመላው ኢትዮጵያ የከፋ መልክ ልይዝ ይችላል። ከዛ ይልቅ በራሳችን ጉዳይ እራሳችን በምናቀርበው የመደራደሪያ አጀንዳ ከሆነ የኢትዮጵያን ጥቅም ባስከበረ የዜጎችን ደህንነት በጠበቀ መልኩ ጉዳዩን ልንቋጨው እንችላለን።
ጦርነቱ የተለያዩ ፍላጎቶች የሚንፀባረቁበት የተለያየ ሀሳብ ያላቸው ጦር ያነገቱበት ከፌደራልም ከክልሉ መዋቅርም ውጪ የእዝ ሰንሰለት የሚንቀሳቀሱ መሳርያ ታጣቂዎች የበዙበት ጦርነት ሆኗል። ይህ አይነት ስርዓት የሌለው የጦር እንቅስቃሴ ጦርነቱን ማሸነፍ እንኳ ቢቻል ለቀጣይ ጦርነት በር የሚከፍት ሆኖ ነው የሚጠናቀቀው። በላዩም በተለይ የለሜኑ ክፍል ወደ አናርኪስትነት የሚለወጥበት ሁኔታዎች ሰፊ ናቸው።
ይሄንን ተያይዞም በሁሉም የሀገራችን ክፍሎች የ ፎልት ላይን ግጭቶች መቀስቀስ ይጀምራሉ ኢትዮጵያ አጣብቂኝ ውስጥ የሚከታት ቀውስ ውስጥ ትገባለች።
በአጠቃላይ ጦርነቱ ወደ ፖለቲካ ድርድር ሊቀየር ይገባል ጥቅምት 2013 ዓ/ም የተደረገው የህግ ማስከበር ዘመቻ በብዙ ስህተት ፌል አድርጓል ከዚህ በኋላ ጦርነቱ በፍፁም ለኢትዮጵያ የሚጠቅማት አይደለም። የጦርነቱ አውድም መልኩን ቀይሯል አሸናፊም ተሸናፊም የሌለበት የእርስ በእርስ እልቂት ውስጥ ነው ኢትዮጵያውያን የገቡት። ስለዚህ ለወደፊቷ ኢትዮጵያ እና ዜጎቿ የሚታሰብ ከሆነ መንግስት ህወሀት አሁን ከያዘው ቦታ በማስለቀቅ የድርድር ቅድመ ሁኔታዎችን በማስቀመት ወደ ድርድር መግባት አስፈላጊ ነው። ይህንን የምናደርገው ለአሜሪካ ስንል ሳይሆን ለኢትዮጵያ ዜጎች እና ለቀጣይ ኢትዮጵያ እጣ ፈንታ ነው።
ድርድር ሲባል ከመሬት ተነስቶ ፅንፍ በረገጠ እና ፍላጎታቸውን በሚያሳካ መልኩ መደራደር አይደለም የፌደራል መንግስቱ በሚያስቀምጠው አጀንዳ ለመደራደር ዝግጁ መሆን። ሁል ግዜም ድርድር የከረረውን ያለዝባል ኢትዮጵያን እናፈርሳታለን እንኳ ብለው ቢደራደሩ አለዝበህ የምትፈልገውን ሀሳብ ማቅረብ ነው።
ድርድሩን በስነ ልቦና የበላይነትለማድረግ የኃይል ሚዛን አስፈላጊ ነው። ነገር ግን እንዳለመታደል ወታደራዊ ዲስፒሊን ያለው ጦርነት አይደለም እየተደረገ ያለው። ፈረንጆች እንደሚሉት ጦርነቱ የህፃን ልጆች ጦርነት አይነት ነው። ይሄ ደግሞ ማባርያ የሌለው የንፁሃን ደምን እለት እለት እየገበርን እንድንኖር ማድረግ ነው።
ጦርነቱን ሁለቱም አካላት ህዝባዊ ማንነት አላብሰውታል  የሰሜኑ ኢትዮጵያ ከሌሎች ከተቀረው ክፍል በስነ ልቦና ይለያያሉ ይሄ ክፍል የጋራ ማንነት እና ስነ ልቦና ይጋራሉ(በእርግጥ ሁሉም የኢትዮጵያ ክፍሎች የጋራ ማንነት አለው)  በተለይም የአልበገር ባይነት፣ የኢትዮጵያ ፈጣሪ እኛ ነን የማለት፣ የደም መላሽነት ማንነት ሁለቱም ጋር በእኩል ይጋራሉ። ያ ተጨማምሮ አደጋውን ከፍ ያደርገዋል። ወደማያልቅ ጦርነት ይሄዳል።
ለዜጎቻችን ስንል ብልህ ፖለቲካዊ ውሳኔ ልንወስን ይገባል።
Filed in: Amharic