>

የሰዎች በሰላም የመኖር ዋስትና ይረጋገጥ!  የኢሰመጉ አስቸኳይ ጋዜጣዊ መግለጫ 

የሰዎች በሰላም የመኖር ዋስትና ይረጋገጥ! 

የኢሰመጉ አስቸኳይ ጋዜጣዊ መግለጫ 
መስከረም 13 ቀን 2014 ዓ.ም
መግቢያ 

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ- ኢሰመጉ እንደ ሁልጊዜው በትግራይ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች ያለውን የሰብዓዊ
መብቶች ሁኔታ በአንክሮ እየተከታተለ ይገኛል፡፡ በዚህም በሰሜን ወሎ ቆቦ እና አካባቢው በቀን 5/13/2013 ዓ.ም በህወሓት ኃይሎች በተፈፀመ ጥቃት ቁጥራቸው ከ500 በላይ ሰዎች መገደላቸውን፣ የእርሻ ሰብልን ጨምሮ የግለሰብ
እና የሕዝብ ንብረት መውደሙን እንዲሁም በርካታ ሰዎች ከቀያቸው ተፈናቅለው ኮምቦልቻ እና ደሴ ከተማ እንደሚገኙ ለኢሰመጉ የደረሱ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡ ኢሰመጉ ስለድርጊቱ አፈፃፀምና አጠቃላይ ስለደረሰው ጉዳት እንዲሁም በሌሎች ዝርዝር ጉዳዮች ላይ ወደፊት ሰፊ ምርመራ የሚያደርግ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ ድርጊቱን በፅኑ ያወግዛል…
Filed in: Amharic