>

"በግፍ በቂሊንጦ እስር ቤት የሚገኙት አቶ ስንታየሁ ቸኮል በፀና ታመዋል" ባልደራስ

“በግፍ በቂሊንጦ እስር ቤት የሚገኙት አቶ ስንታየሁ ቸኮል በፀና ታመዋል”
ባልደራስ


አቶ ስንታየሁ ቸኮል በፅኑ መታመማቸውን ተከትሎ በአስቸኳይ ወደ ሆስፒታል በመሄድ የህክምና አገልግሎት እንዲያገኙ ማረሚያ ቤቱን ቢጠየቁም
ተከልክለዋል።
እስር ቤቱ የህክምና አገልግሎት መስጠት ግዴታው ቢሆንም አቶ ስንታየሁ ቸኮል ግን ህክምና እንዳያገኙ ከልክሏቸዋል ። አቶ ስንታየሁ ቸኮል ከአመታት በፊት ለረጅም ጊዜ በኩላሊት ጠጠር ኢንፌክሽን ታመው መቆየታቸው ይታወቃል። አሁንም ህመሙ ተባብሶባቸው በስቃይ ላይ እንዳሉ ከቤተሰቦቻቸው ለመረዳት ተችሏል።
አቶ ስንታየሁ ቸኮል ቀደም ሲል በፖሊስ ሆስፒታል እና በቃሊቲ ህክምና እየተከታተሉ ቢቆዩም ወደ ቂሊንጦ ከተዛወሩ በኋላ ክትትላቸው ተቋርጦ ነበር።
በማረሚያ ቤቱ ግቢው ውስጥ በሚገኝው መለስተኛ ክሊኒክ ህክምና በመከታተል ከችግራቸው ጋር እየተጋፈጡ እንደቆዩ ይታወቃል።
..” ይሁን እንጂ በአሁኑ ሰዓት ህመማቸው በመባባሱ ከቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ሪፈር ተብለው በፖሊስ ሆስፒታል አልያም ወደ ቃሊቲ እንዲሄዱ ቢጠይቁም
በተደጋጋሚ ጊዜ ክልከላ ተደርጎባቸዋል።
በማረሚያ ቤት የሚገኝ ማንኛውም እስረኛ ህክምና ተከልክሎ የሚቆይበት የህግ አግባብ እንደሌለ ቢታወቅም የቂሊንጦ እስር ቤት አስተዳደሮች ግን
አሻፈረኝ ብለዋል። “ለማረሚያ ቤቱ ህክምና መስጠት ግዴታ እንጅ መብት አይደለም” ሲሉ በህመም የሚሰቃዩት አቶ ስንታየሁ ቸኮል ገልፀው ከተገቢው ሆስፒታል አስቸኳይ የህክምና ዕርዳታ እንዲያገኙም ጠይቀዋል።
ዜጎች የህክምና አገልግሎት እንዳያገኙ መከልከል ፤ በህይወት የመኖር ተፈጥሮአዊ መብትን መንፈግ በመሆኑ ማረሚያ ቤቱ በህክምና አገልግሎት
ዕጦት አቶ ስንታየሁ ቸኮል ለሚደርስባቸው ማንኛውም ጉዳት ተጠያቂነቱን
ይወስዳል።
ፍትህ ፣ ፍትህ ፍትህ…..!!!
Filed in: Amharic