>

ዋ! ኢትዮጵያ...! ይህቺ ሀገርማ እርግማን አለባት...!!! (ኤልያስ ገብሩ )

ዋ! ኢትዮጵያ…!

ይህቺ ሀገርማ እርግማን አለባት…!!!
በኤልያስ ገብሩ 

በግሌ በምዕራፍ አምናለሁ። አንድ ምዕራፍ ሲቋጭ፣ ወደሌላ ምዕራፍ መሸጋገር ጤናማም ተገቢም በመሆኑ አምናለሁ።
የግፍ እስረኝነት በሕወሃት/ኢህአዴግ ዘመን በሽ በሽ ነበር። 2010 ዓ.ም. በመልካም ጎኑ ከማስታውሳቸው ጉዳዮች አንዱ የግፍ እስረኞች ከእስር ቤት መውጣትና የግፍ ክሶች መቋረጣቸው ነበር። ይሄንን ምዕራፍ እንደ ሀገር አልፈነው ሄደናል ብዬ አስቤም ነበር፣ ግን አልሆነም!
ዛሬም እዛው ላይ ነን። እንደ ሀገር እርግማን አለብንምናም እዚያው ውስጥ በተደጋጋሚ እንመላለሳለን። ማመን አለማመን የግለሰቦች የግል መብት መሆኑን ባምንም፣ እንደሀገር ወርደናል! አሳዛኝነት ብቻ አይገልጸንም።
 በውጪ ሀገር ያሉ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ያኔም “እነ እገሌ ይፈቱ!” ብለው ለዓመታት አደባባይ ወጥተዋል። ዛሬም በተመሳሳይ መንገድ አደባባይ ላይ ይገኛሉ።  በግሌ እንደ ሀገር እዝነት ነው የሚሰማኝ።
 የተጠሉ፣ የሰለቹና ሕዝብን ያማረሩ ምዕራፎቻችንን መዝጋትና መቋጨት ዛሬም ድረስ አልቻልንም፣ ያሳዝናል።
 ሕሊና ቢኖረን፣ እንደ አንድ ሀገር ሕዝብ ባፈርን! ከአንዱ ምዕራፍ ወደሌላኛው ከፍ ብለን መሸጋገር አልቻልንም።
 ጥለናት ለምናልፍ ዓለም፣ እርስ በእርስ ክፋዎች የሆንን የእርግማን ሀገር ዜጎች …..!
ዋ! ኢትዮጵያ!
Filed in: Amharic