>

እንቆቅልሽ የሆንሽ ሀገር....!!! (ያሬድ ሀይለማርያም)

እንቆቅልሽ የሆንሽ ሀገር….!!!

ያሬድ ሀይለማርያም

ሚልዮኖች ተርበው ከቤት ከእርሻቸው ተፈናቅለው የወገን ያለህ እያሉ በዋይታ በሰቆቃ በሚጣሩባት አገር የተሿሿሙ ከድሬዎች:-

ከ5 ሚሊዮን ብር በላይ ፈሰስ የተደረገበት የአዲስ አበባ ከተማ አዲስ ምክር ቤት የምስረታ መርሐ ግብር እስከ ዛሬ ከታዩት የምክር ቤቱ ምስረታዎች በበጀትም በጥራትም አቻ የሌለው ሆኖ ተመዝግቧል ‼ – ይልሀል ፋና

ህሊና ቢስነት:: ሚሊዮኖች በርሃብና በስቃይ ባሉበት ወቅት እንዲህ በህዝብ ገንዘብ ይቀልዳሉ:: የወያኔን ወረራ ለመመከት በሚል ብዙ ሰው ትኩረቱን ጦርነቱ ላይ ማድረጉ ለእናንተ የበሰበሰ ስርአት ድጋፍ መስጠት መስሎአችሁ ከሆነ ተሳስታችሁዋል:: 
+++
ግማሽ ጎንሽ በርሃብ ይጠበሳል፣ በጦርነት ይለበለባል፣ መቶ ሺዎች ተፈናቅለው በየሜዳው ወድቀዋል፣ ሕጻናት በየጥሻው ወድቀዋል፣ ብዙዎች በሕክምና እጦት ይማቅቃሉ፣ የድረሱልን ድምጽ በየቦታው ይናኛል፤
ሹማምንትሽ ምክርቤት ለመግባት ልክ እንደ ትምህርት ቤት ዩኒፎርም አሰፍተው አንድ አይነት ሱፍና ቀሚስ ለብሰውና ተጫምተው የሚሽሞነሞኑብሽ፤
እንቆቅልሽ የሆንሽ ሀገር።
የአዲስ አበባ አዲሱ ምክር ቤት አባላት በማን ወጪ ነው እንዲህ አንድ አይነት ልብስ ለብሰውና ተጫምተው ብቅ ያሉት? ወጪው ከመንግስት? ወይስ ከራሳቸው? አገሪቱ ካለችበት አጣብቂኝ አንጻር መልሱ ምንም ሹማምንት እንዲህ ሲሆኑ ውጤቱ ያው ነው። ከመንግስት ካዝና ከሆነ ይበልጥ ያስተዛዝባል። ገና ያላገለገሉትን ሕዝብ መጣንልህ፤ ሳይሆን መጣንብህ ይመስላል።
መልካም የሥራ ዘመን ልል ነበር ግን አያያዛችሁ አያምርምና በቅድሚያ የምትመሩትን ሕዝብ ምሰሉ ማለትን ወደድኩ።  ሕዝቡን ስትመስሉ ሥራችሁም ይቀናል።
Filed in: Amharic