>

"ከንቲባዬ...!!! " (ለሞን አላምኔ)

“ከንቲባዬ…!!! “

ሰለሞን አላምኔ

…. በአ.አ ምክር ቤት ከተሰበሰቡት ቀርቶ #የምኒልክ_ቤተ_መንግስት ከተቀመጡት በላይ ህዝቡ እስክንድር ነጋ መሪየ ነው ብሎ እንደተቀበለ ራሱ ህዝቡ ጠንቅቆ ያውቃል። ለዚህም ነው በሚዲያ ቀርበው ከቀሰቀሱት ፣ በአካል ቀርበው ከቀሰቀሱት በላይ እስር ቤት በግፍ የታሰረው እስክንድር ነጋ በጣም በጣም ለህዝቡ ታማኝ ስለሆነ #ከንቲባዬ ብለው የመረጡት…!!!
 ….
ተረኛ በተረኛው ቢፈራረቅ ፤ ባለጊዜው ሄዶ ባለጊዜው ቢመጣ ፤ ዘራፊው እና ሌባው ሄዶ ሌላ ዘረፊ እና ሌባ ቢመራረጥ ፤ ካራቫት ያሰሩ ተላላኪዎች ሂደው ሌላ ካራቫት ያሰሩ አሸርጋጆች እና አድርባዮች ቢወካከሉ ፤ የኔ ከንቲባ እስክንድር ነጋ ብቻ ነው።
አይደለም በአ.አ ምክር ቤት ከተሰበሰቡት ቀርቶ #የምኒልክ_ቤተ_መንግስት ከተቀመጡት በላይ ህዝቡ እስክንድር ነጋ መሪየ ነው ብሎ እንደተቀበለ ራሱ ህዝቡ ጠንቅቆ ያውቃል። ለዚህም ነው በሚዲያ ቀርበው ከቀሰቀሱት ፣ በአካል ቀርበው ከቀሰቀሱት በላይ እስር ቤት በግፍ የታሰረው እስክንድር ነጋ በጣም በጣም ለህዝቡ ታማኝ ስለሆነ #ከንቲባየ ብለው የመረጡት።
ግራ)(ቀኝ ተመልከቱ ፦ ዛሬም የእስክንድር ነጋ እውነት እና ሀቅ እንደ ፀሀይ ደምቆ ፤ የፒኮኩ መንግስቶች ደግሞ በተቃራኒው የደበቁት ውሸት እና ሴራ እውነት ፍንትው አድርጋ ስታጋልጥባቸው ፤ ህዝብ ቀስ በቀስ ነገሩ ሁሉ እየተገለጠለት ሲመጣ ፤ ለስልጣን ፍለጋ ካራቫት አስረው የለውጡ ሀይል አጋዥ እና የለውጡ ዘብ ፣ የለውጡ ጠበቃ ሁነው ለውጡ እንዳይደናቀፍ በሚል ስሁት አመለካከት በየሚዲያ እየቀረቡ ” አሻጋሪ ተሻጋሪ ትርክት ” ፤ ” ድንቅ ሴት ከንቲባ ” እያሉ ህዝቡን ቃል በተገባላቸው መሰረት ወደ ምንፈልገው ዲሞክራሲያዊ መንገድ ያሻግሩናል አትናገሯቸው እያሉ እውነትን ሲደብቁ የነበሩ ሁሏ ፦ ዛሬ ዋሽተው አታለው ጨርሰው የሚሉት ሁሉ ጠፍቶባቸው የት እናዳሉ አናውቅም።
አንድ አንዶችም ወንበር ፍለጋ ሲያሽቃብጡ የነበሩ ሁሉ የልባቸው ደርሶላቸው ስልጣን አግኝተዋል። ያገኙት ስልጣን ህን #ልዩ_ጥቅምን የሚያበረታታ እና የሚሰራውን ሰነድ ከማረጋገጥ በቀር ከተማዋን #ራስ_ገዝ የሚያደርገውን ሰንድ ካልሆነ የሚለውጡት አንዳች ነገረ የለም። ዳሩ እኛ ለዲሞክራሲ ስንታገል እነሱ ለወንበር ሲታገሉ እንደነበረ ጊዜ ደጉ አሳይቶናል።
” እስክንድር ነጋ እና ደቀ መዙሙሮቹ ” በከፍታቸው ልክ ለህዝብ እንደታመኑ በግፍ እስር ቤቱ ሆነው በአሸናፊነት ስነልቦና አሉ። ምንም እንኳን ህዝቡን መታደግ እየተገባቸው ምንም ማድረግ ባለመቻላቸው እያዘኑ ቢሆንም!!

ከንቲባዬ እስክንድር ነጋ ነው

Filed in: Amharic