>

በአኬል ዳማ ዋ ወለጋ ዛሬም ደም እንደ ውሀ ይፈሳል፤ እምባ እንደ ጎርፍ ይወርዳል...!!! (ጋዜጠኛ መአዛ መሀመድ)

በአኬል ዳማ ዋ ወለጋ ዛሬም ደም እንደ ውሀ ይፈሳል፤ እምባ እንደ ጎርፍ ይወርዳል…!!!

ጋዜጠኛ መአዛ መሀመድ

በምስራቅ ወለጋ ከሞት የተረፉ  ተፈናቃዮች በምግብና መድሃኒት እጦት እየተሰቃዩ ነውበየቀኑ በስልክ የሚነግሩኝ ሰቀቀን እንቅልፍ ነስቶኛል በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋ ዞን የተለያዩ ወረዳዎች በታጣቂዎች የሚፈጸመውን ጥቃት ሸሽተው ከገጠራማ አካባቢዎች ወደ ከተማ የተፈናቀሉ ዜጎች በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ ናቸው።
ታጣቂዎች ከነሀሴ ወር ማገባደጃ ሰሞን ጀምረው በተከታታይ በፈፀሟቸው ጅምላ ጭፍጨፋዎች ሰው እንደከብት እየታረደ ነው  ባለፉት ሰባት ቀናት ብቻ 45 ሰዎች መገደላቸውን ነግረውኛል።
ሰሞኑን  በስለት የተወጉና በአጋጣሚ የተረፉ ተጎጂዎች በህክምና እጦት እየተሰቃዩ ነው አንገታቸው ተቀልቶ ነፍሳቸው ያልወጣ ቁስለኞችን አቅፎ አይን አይን እያዩ ሞትን ከመለመን በላይ ምን ሰቀቀን አለ?በዚህ ሳምንት በሞትና በህይወት መካከል ካሉ 20 ቁስለኞች መካከል የአንድ ሰው ህይወት አልፏል።
ሀሮ እና ኪራሙ በተባሉት ከተሞች ተጠልለው የሚገኙት ነዋሪዎች የምግብ እርዳታ በአስቸኳይ እንደሚሹ ነው ግድያውን ሸሽተው የተፈናቀሉት የጥቃት ሰለባዎች የሚናገሩት፡፡በአካባቢው ዘግናኝ ግድያዎች እየተፈፀመ ነው ህፃናት ሳይቀር በአሰቃቂ ሁኔታ ታርደዋል ።
በአሁኑ ወቅት ኪራሙ ወረዳን ከቡሬ እና ነቀምቴ ከተሞች ጋር የሚያገናኙ ዋና ዋና መንገዶች በመዘጋታቸው ከአካባቢው ሙሉ በሙሉ ለቀው መሄድ አለመቻላቸውን ነግረውኛል። ገዳዮቹ እንደሚፈልጉት ካለንበት አካባቢ ለቅቀን ነፍሳችንን ማትረፍ ነው የምንፈልገው ቢሉም መንገድ ከየት መጥቶ።ለነገሩ ሰሚ ጠፍቶ እንጂ በኪራሙ ወረዳ፣ ቦቃና ውልማይ በተባሉ ቀበሌዎች ሰሞኑን ቢያንስ 29 ሰዎች መገደላቸውን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ሪፖርት አድርጎም ነበር።
Filed in: Amharic