>

ከባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ የተሰጠ አስቸኳይ መግለጭ...!!!

ከባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ የተሰጠ አስቸኳይ መግለጭ…!!!

 

 

ጉዳዩ ፡- የአቶ ስንታየሁ ቸኮል የህክምና መብት ክልከላን ይመለከታል !
 
~ ለኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን /ኢሰመጉ/
~ ለኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ጉባኤ/ ኢሰመኮ/
 
አዲስ አበባ
የፓርቲያችን አመራር የሆኑት አቶ ስንታየሁ ቸኮል በሃሰት ክስ ተመስርቶባቸው ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት በእስር ላይ ይገኛሉ፡፡ አቶ ስንታየሁ ቸኮል  በሃሰት የሽብር ወንጀል መከሰሳቸው አልበቃ ብሎ ለህመማቸው የተሻለ ህክምና እንዳያገኙ ተደርገዋል፡፡ በኩላሊት ህመም  የሚሰቃዩት አቶ ስንታየሁ ቸኮል የተሻለ ህክምና አግኝተው ከህመማቸው እንዲያገግሙ ህክምና ማግኘት እንዲችሉ ማረሚያ ቤቱን ደጋግመው ቢጠይቁም ጥያቄቸው ተቀባይነት ሳያገኝ ቀርቷል፡፡ ከዚህ የተነሳ በኩላሊት ህመም ምክንያት ሌት ተቀን እየተሰቃዩ ቆሞ እንኳን ቤተሰባቸውን ማነጋገር እያቃታቸው ይገኛል፡፡
አንድ ዜጋ ህክምና የማግኘት መብቱ በማናቸውም ሁኔታ ውስጥ ሊጠበቅላቸው ይገባል፡፡ ነገር ግን አቶ ስንታየሁ ቸኮል ይህ መብታቸው የተነፈገ ስለሆነና ህመማቸው ከቀን ወደ ቀን እየበረታ ስለሆነ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን አቶ ስንታየሁ ቸኮል ህክና የማግኘት መብታቸው እንዲጠበቅላቸው የበኩሉን ከፍተኛ ድጋፍ እንዲያገኙ እንዲደረግ በትሀትና እንጠይቃለን፡፡
ከሠላታ ጋር
ጌታነህ ባልቻ /ኢንጅነር)
ም/ፕሬዘዳንት
Filed in: Amharic