>

ዶ/ር ይልቃል ከፍአለ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሆነው ተመረጡ...!!! (ዋልተንጉስ ዘ-ሸገር)

ዶ/ር ይልቃል ከፍአለ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሆነው ተመረጡ…!!!

ዋልተንጉስ ዘ-ሸገር

*…. ሳይጀመር የተጀመረው የአማራ መከራ…
 
ዶ/ር ይልቃል ከፋለ ይባላሉ። ትውልድና ዕድገታቸው በምዕራብ ጎጃም ዞን ደቡብ አቸፈር ነው። ጀግናና ምሁር ይውጣልህ ተብሎ የተመረቀው የአቸፈር ህዝብ ሙሉ ስብዕና እንዲላበሱ ከማድረግ ባለፈ በዕውቀትም እንዲበለፅጉ መነሻ ሆኗቸዋል።
ዶ/ር ይልቃል ከፋለ እርጋታና አስተዋይነትን የተካኑ፣ ትዕግስትና ትህትና አብረዋቸው ያደጉ፣ አድማጭና በሃሳብ የበለፀጉ ምሁር ናቸው።
ዶ/ር ይልቃል ከፋለ የሁለተኛ ዲግሪያቸውን በሶሻል አንትሮፖሎጅ ከአዲስ በአበባ ዩኒቨርሲቲ ተምረዋል። የሶስተኛ  ዲግሪያቸውን  በሶሻል አንትሮፖሎጅ በህንድ ሀገር ታዋቂ ዩኒቨርሲቲ ተመርቀዋል።
ዶ/ር   ይልቃል ከፋለ በጎንደር መምህራን ትምህርት ኮሌጅ መምህርነት አስተምረዋል። በደብረማርቆስ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ከመምህርነት እስከ ዲንነት የዘለቀ አገልግለዋል። የደብረማርቆስ ዩኒቨርስቲ ምክትል ፕሬዝዳንትነት እስከ ፕሬዝዳንትነት በማገልገል መሠረቱ እንዲፀና የአንበሳውን ድርሻ ተወጥተዋል። በዚህም ከፍተኛ የመሪነት ልምድ ያላቸው ታላቅ ምሁር በአሁኑ ጊዜ የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮን በኃላፊነት ሲመሩ ቆይተዋል።
ዶ/ር ይልቃል ከፋለ እውቀትን ከእርጋታና ትህትና ጋር የተላበሱ፣ አስተዋይና አርቆ አሳቢ ምሁር ሲሆኑ የክልሉ የትምህርት ስርዓት ችግሮችን ለመፍታት ሌት ከቀን የሚሰሩ፣ የክልሉ ተማሪዎች ተወዳዳሪዎች እንዲሆኑ ተግተው የሚሰሩ፣ በክልሉ የዳስ መማሪያ ክፍሎችን እንዲከስሙ እየተጉ ይገኙም ነበረ።
ሳይጀመር የተጀመረው የአማራ መከራ…
Filed in: Amharic