>

አንጋፋዉ የፊልም ባለሙያ ሃይሌ ገሪማ ተሸለሙ...!!!  (ሙሉቀን አለምነህ)

አንጋፋዉ የፊልም ባለሙያ ሃይሌ ገሪማ ተሸለሙ…!!!

    ሙሉቀን አለምነህ

የኦስካርን ሽልማት በመስጠት የሚታወቀው ‘ዘ አካዳሚ ኦፍ ሞሺን ፒክቸር አርትስ ኤንድ ሳይንስስ’ በጉጉት ሲጠበቅ የነበረውን ሙዝየም መክፈቻን አስመልክቶ ከፍተኛ ሽልማቱን ለአንጋፋው ፊልም ሰሪ ኃይሌ ገሪማ አበርክቷል።
በጥቁሮች የሲኒማ ታሪክ ላይ ከፍተኛ ስፍራ ያላቸው ኢትዮጵያዊው ኃይሌ ገሪማ ‘ዘ አካዳሚ ሙዝየም ኦፍ ሞሺን ፒክቸርስ’ የቫንቴጅ ሽልማት የመጀመሪያው ተሸላሚ ሆነዋል።
እንደ ‘ሳንኮፋ’ እና ‘አሽስ ኤንድ ኤምበርስ’ ከሚባሉ ምርጥ ፊልሞች በስተጀርባ ያሉት አንጋፋው የፊልም ዳይሬክተር ኃይሌ የሎስ አንጀለሱ ሙዝየም መክፈቻን አስመልክቶ ቅዳሜ ዕለት ባደረገው ሥነ ሥርዓት ላይ ነው ሸልማቱን የሰጣቸው።
ኢትዮጵያዊው ኃይሌ ገሪማ ‘ቫንቴጅ’ የተባለውን ሽልማት የተሸለሙበትን ምክንያት አስመልክቶ ሙዝየሙ እንዳስታወቀው “በሲኒማ ዙሪያ ዋነኛ ትርክቶችን በመገዳደርና አውድ በማስያዝ የረዳ አርቲስትና ምሁር” በሚል እንዳከበራቸው አስታውቋል።
Filed in: Amharic