>
5:16 pm - Saturday May 24, 6960

ደጃዝማች ገረሱ ዱኪ  (አባ ቦራ) ታሪክን ወደኋላ

ደጃዝማች ገረሱ ዱኪ  (አባ ቦራ)

ታሪክን ወደኋላ 

ደጃዝማች ገረሱ ዱኪ ከአዲስ አበባ ጅማ በሚወስደው መንገድ 114 ኪ.ሜ በምትገኘው በወሊሶ ከተማ በ 1905 ዓ.ም. ከአባታቸው ከአቶ ዱኪ ጉልማና ከእናታቸው ከወ/ሮ ወርቄ ኤልሞ ተወለዱ።
በወርሃ ሚያዝያ 1928 ዓ.ም የኢትዮጵያ ዋና ከተማ አዲስ አበባ በፋሺስት  ኢጣሊያ ጦር እጅ  ወደቀች ፤ወረራውን ተከትሎ ብዙዎች የውጭ ሀገር ሰዎች ኢትዮጲያ እንደ ሀገር የመቀጠሏ ታሪክ  አከተመላት  ሲሉ በደፍረት የተናገሩበትና የፃፊበት ጊዜ ነበር።
ይህ ግምት ግን በኢትዮጲያውያን ዘንድ ቦታ አልነበረውም ፤  ኢትዮጲያዊን  በዘር፣ በሀይማኖትና  በፓለቲካ ሳይከፋፈሉ ለአንድ  አላማ ተሰልፈው   የሀገራቸውን  ነጻነት እውን ለማድረግ ቆርጠው ተነሱ  ፤ደዣዝማች ገረሱ ዱኪ ወይም በፈረስ ስማቸው አባ ቦራ በዚህ ረገድ ከሚታወሱ  የሀገር፤ የክፋ ቀን ደራሽ ጀግኖቻችን መሀከል  አንዱ ናቸው ።
ፋሺስት ጣልያን ሀገራችንን ለሁለተኛ ጊዜ በወረረበት ወቅት የተጠበቀውን ጦርነት መነሻ በማድረግ በየክፍለ ሀገሩ የዘመተው የኢትዮጵያ የጦር ሠራዊት በጦር ሚኒስቴሩ ስር ሆኖ በ1928 ዓ.ም. ከማይጨው እስከ ተንቤና ሰቲት ድረስ ግጥሚያዎች አድርጎ ብዙ ጀግኖቻችን ተሰውተዋል።
በዚህ ጦርነት….
ደጃዝማች በየነ(አባ ሰብስብ)
ቢተወድድ መኮንን ደምሰው
ደጃዝማች መሸሻ ወልዴንና ሌሎችም ጀግኖች የጦር መሪዎች ስለ ሀገራቸው ሲሉ ህይወታቸው አልፏል። በዚያን ግጥሚያ ባላንባራስ (በኋላ ደጃዝማች) ገረሱ ዱኪም ይገኙ ነበር፤ እንዲያውም ቃፊር ሆነው በተንቤ የመጀመሪያውን ጥይት የተኮሱት እርሳቸው ነበሩ።
ከዚያም በጦርነቱ ፋሺስት በወረራ ወቅት ለጠላት ገብረን አናድርም ካሉ ጀግኖች አርበኞቻችን አንዱ ደጃዝማች ገረሱ ነበሩ፤ ደጃዝማች ገረሱ ቆራጥ አርበኞችን አስከትለው በጠላት ላይ የመጀመርያ ድላቸውን ተቀዳጁ ከነዚህ አምስቱ አንዱ ልጅ ገነነ በዳኔ ናቸው። ደጃዝማች ገረሱ (አባ ቦራ) ፋሺስት ጣልያንን እሳቸው ባሉበት ከደቡብ ኦሮሚያ እስከ ኦሞ ወንዝ መቀመጫ አሳጡት ገበሬዎችን አሰባስበው በደፈጣ ውጊያ ቁም ስቅሉን አሳዩት። የእርሳቸው ጀግንነት ከደቡብ ምዕራብ ሸዋ እስከ ጅማ ድረስ ብዙ ሺ ወጣቶችን አነሳስቶ ጫካ አስገባ። ጀግናው አርበኛ ገረሱ (አባ ቦራ) በዛ የሞት ሽረት ውጊያ ላይ ገና ለጦርነት ያልደረሰውን የ 13 ዓመት ልጃቸውን ተፈራ ገረሱን በጦርነት አሳትፈዋል፤ ሀገር ከምንም ይቀድማል በማለት ብላቴናው ልጃቸውን ጀግንነት አስተምረውታል፤ ዘመናዊ ጦር የታጠቀውን ፋሺስት እያስበረገጉ ተስፋ አስቆረጡት።
የእኚህን ጀግና አርበኛ ታሪክ የሚዘክር ሙዚዬም ከወሊሶ 1.ሜ. በሚገኘው ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን አጠገብ ይገኛል እንዲሁም በእዛው በወሊሶ ከተማ በስማቸው የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተሰይሞላቸዋል።
 መድፍና ጠመንጃ ጥይት ሲጓረሱ 
  አሳላፊ ነበር የማሩ ገረሱ ክብርና ሞገስ ከወራሪዎች ነፃ ሀገር ላስረከቡን ጀግኖች አርበኞቻችን🙏
Filed in: Amharic