በቃ ይበቃሃል ከዚህ ውጣ ብሎ አሰናበተኝ “
አቶ ታዲዮስ ታንቱ
ላለፉት ጥቂት ለማይባሉ ወራት ከሕግ አግባብ ውጪ በእስር ላይ የቆዩት አረጋዊውና አንጋፋው የታሪክ ምሑር አቶ ታዲየኖስ ታንቱ ከተያዙ ጊዜ ጀምሮ አንድም ቀን ፍርድቤት ሳይቀርቡ፣ ክስም ሳይመሰረትባቸው፣ ፖሊስም ቃላቸውን ሳይቀበል፣ የታሰሩበትም ሳይታወቅ ከርሞ በዛሬው ዕለት በድንገት ከወህኒ ተፈተው ከቤተሰቦቻቸው ጋር መቀላቀላቸው ተሰምቷል።
” …የሆነ የባለ ሥልጣን ካለሁበት ዘብጣያ መጣ… ጠራኝ… አነጋገረኝም… በቃ ይበቃሃል ከዚህ ውጣ ብሎ አሰናበተኝ ” ነው ያሉት አሉ አቶ ታዲዮስ ታንቱ።
*…. በነገራችን ላይ ጋሽ ታዲዮስን አላሰርኩም ያለው ኮማንደር ደረጄ አርብ ፍርድ ቤት ቀርቦ እሳቸው እዛ እንደነበሩ ሰዎች ምስክርነት ይሰማበታል። በጣም የሚገርመው ነገር ከመስከረም 11/2014 ጀምሮ እስከትላንት ድረስ ከነበሩበት ገላን ፖሊስ መምሪያ አስወጥተው ስሙ የማይታወቅ ማጎሪያ ውስጥ አቆይተው እንደፈቷቸው ነግረውኛል። ባይፈቱ ኖሮ እኔ ጋር የሉም ለማለት መሆኑ ነው ለማንኛውም ጠበቃቸው Addisu Getaneh እና ጉዳዩን ጉዳዬ ብላችሁ ድምፅ የሆናችኋቸው ሁሉ ምስጋናው የእናንተ ነው።
እሳቸው እውነትን ከመናገር በስተቀር ወንጀል አልሠሩምና የሚከሱባቸው ምክንያት ቢያጡ አንድ ሰው በጸጥታ አካላት በተያዘ በ48 ሰዓት ውስጥ ፍርድ ቤት መቅረብ እንዳለበት የተደነገገ ሕግ ቢኖርም ለዚህ ሕግ መከበርና ለዜጎች መብት መጠበቅ ዴንታ የሌለው አገዛዙ ያለምንም ክስ ሁለት ወር ይሁን ሦስት ወር አስሮ ማሰሩ ብቻ ሳይሆን ቤተሰብ እንዳይጠይቃቸው ያሉበትን ቦታ ሰውሮ በዚህ መልኩ ሰብአዊ መብታቸውን ገፎ ሲያንገላታቸውና ሲያስጨንቃቸው ቆይቶ አገዛዙ ጋሽ ታዴዎስ ታንቱን ማምሻውን እንደፈታቸው ታውቋል!!!
በነገራችን ላይ አገዛዙ ብዙ ጣጣዎቹን ስላጠናቀቀ “እንቅፋት ይሆኑኛል!” ብሎ ፈርቶ ያሰራቸውን እነ እስክንድርንም በቅርቡ መፍታቱ አይቀርም!!!
ችግሩ ንጹሐኑን እነ እስክንድርን ሲፈታ ወንጀለኞችን እነ ጃዋርንም አብሮ የሚፈታ መሆኑ ነው ችግሩ!!!
አገዛዙ እነ እስክንድርን ለእነ ጃዋር ማባያ አድርጎ ያሰረበት ምክንያት እነ እስክንድርን በመያዣነት ይዞ ቆይቶ እነ ጃዋርን መፍታት በፈለገ ጊዜ “እነ እስክንድርን እንድፈታላቹህ የእነ ጃዋርን መፈታትም ተቀበሉ!” ብሎ መደራደሪያ ሊያደርጋቸው ስላሰበ ነበር አጋሮቹ እነ ጃዋር በአደባባይ የታየና በመቶዎች ለሚቆጠሩ ንጹሐን ወገኖቻችን ግድያና በቢሊዮኖች ለሚቆጠር ንብረት ውድመት የሚያስጠይቅ ከፍተኛ ወንጀል ሠርተው ማሰር ግድ ሲሆንበትና ለይስሙላ እነሱን ሲያስር እነ እስክንድርንም ያለ አንዳችም ጥፋት አራቱንም ለቃቅሞ ያሰራቸው የነበረው!!!
እነሱ መቸ ግፍ ይፈሩና???
እንኳን ለቤትዎ አበቃዎ!