>
5:33 pm - Wednesday December 5, 2857

በ7ኛው ንጉስ በበዓለ ሲመቱ ላይ  እርኩስ ጋብቻውን በቅዱስ ፍቺ ደምድሟል (ዶ/ር ለማ)

በ7ኛው ንጉስ በበዓለ ሲመቱ ላይ  እርኩስ ጋብቻውን በቅዱስ ፍቺ ደምድሟል

ዶ/ር ለማ


የሰባተኛው ንጉስ እና የ30 አመቱ አምባገነን ኢሳያስ እርኩስ ጋብቻቸው በትላንትናው እለት ቅዱስ ፍቺ ያደረጉ ይመስለኛል። ደግሞም ነው።

ብዙዎች በጉጉት ሲጠብቁት የነበረው ከ ጠ/ም አብይ ንግስና ይልቅ የኤርትራው ኢሳያስን በመስቀል አደባባይ ከፍ ብሎ ከአብይ ጎን ቆሞ ማየትን ነበር።

ይህ ግን ምኞት እንጂ እውን መሆን አልቻለም። 7ኛው ንጉስ በአለም መድረክ ላይ ከፍ ብሎ እንዲታይ የረዳው አስተሳሰቡ ወይም ስራው ሳይሆን ኢሳያስ ነበር።

ለብዙ ዘመናት በኢትዮጵያ እና በኤርትራውያን መካከል የነበረውን የጥል ግድግዳ ያደረመሰው አብይ በራሱ ሳይሆን ኢሳያስ ለበቀሉ ጥማት ይሆን ዘንድ ነበር።

ምንም ነገር ሳያስብ እና ጥቅሙን ትኩር ብሎ ሳያይ የማይንቀሳቀሰው ኢሳያስ ወያኔን ለመበቀል አንዱ መንገዱ 7ኛው ንጉስ ነበር። ይሄንንም አልሞ ተጠቅሞበታል።

በጥቂቱም ቢሆን በቀሉን ያሳካው ኢሳያስ ያሰበው ሁሉ ግን አልተሳካለትም። 7ኛው ንጉስ አዎ የኤርትራ ሰራዊት ወደ ኢትዮጵያ ድንበር ገብቷል።

ብሎ ካመነበት ጊዜ አንስቶ ኢሳያስ በ7ኛው ንጉስ ላይ ጥርሱን ነክሶበት ቆይቷል። ይህ ብቻ ሳይሆን በድጋሚ ለመአቀብ ዳርጎታል።

በቀሉን እንጂ የኤርትራን ልዩ ጥቅም የማያስቀድመው ኢሳያስ በአንድ ትልቅ ጄኔራሉ ላይ መአቀብ መጣሉም የበለጠ አበሳጭቶታል።

ብዙ ተደራራቢ የ7ኛው ንጉስ ስህተቶች የበለጠ ኢሳያስን እያናደደው መጥቷል። በተለይ ደግሞ መከላከያው ከትግራይ ክልል መውጣቱ በጣም ቆጭቶታል።

በርካታ ጄኔራሎቹን በዚህ ጦርነት ያጣው ኢሳያስ እንዳሰበው አልሆነለትም ብዙ ወታደሮቹ አልቀዋል። በድጋሚ ኢኮኖሚው ላሽቋል።

ይህ ብቻ ሳይሆን በጎንደር ትልቁን ጄኔራሉን በቅርቡ በተደራጁ ፋኖዎች አጥቷል። ብዙ ወታደሮች ገንደር ላይ በጎንደር ፋኖ ተገለዋል።

ታዲያ በዚህ ጦርነት ብዙ ነገሩን ያጣው ኢሳያስ በ7ኛው ንጉስ በዓለ ሲመት ላይ ይገኛል ብሎ ማሰብ በራሱ ጅልነት እና አላዋቂነትም ጭምር ነው።

ሰማይ ዝቅ ምድር ወደላይ ከፍ ብትል እንኳን የኢትዮጵያን ከፍታ የማይፈልገው ኢሳያስ በትላንቱ የ7ኛው ንጉስ በዓለ ሲመት ላይ መገኘት ሞቱ ነበር።

ኢሳያስ መቼም የኢትዮጵያን ከፍታ አይፈልግም። ፈልጎም አያውቅም። ኤሳያስን ጨምሮ ብዙ ኤርትራውያን በኢትዮጵያውያን ብዙ በደል ደርሶባቸዋል።

ከዛሬው ወዳጅነት ይልቅ ውስጣቸው ያለው የድሮው በቀል እና ስቃይ እንጂ የፕሮፖጋንዳው ፍቅር አይደለም። ብዙ የማይረሱት በቀል ውስጣቸው አለ።

ይህ ሁሉ ተጠረቃቅሞ እነሆ በትላንትናው ቀን በ7ኛው ንጉስ በዓለ ሲመት ላይ የ 3 አመቱ እርኩስ ጋብቻ ቅዱስ ፍቺ አድርጓል። ቀጣዩን አብረን የምናየው ይሆናል።

Filed in: Amharic