>

"አዲስ መንግስት፤ ወይስ ሣልስ ዕዳ...???" (ባልደራስ)

አዲስ መንግስት፤ ወይስ ሣልስ ዕዳ…???”

ባልደራስ


“የአዲስ አበባ ልጆች በሙሉ የሸሌ ልጆች ናቸው፤እናታቸውን ጠርተው አባታቸውን አይደግሙም።።ኢትዮጵያ መፍረስ አለባት።”
(ይህንን ያሉት ከታች በምስሉ የሚታዮት “የአዲሱ መንግስት” የህዝብ ተወካይ ግለሰብ ናቸው)
*…. ሰውየው ገና ወንበር ከመያዙ ሶስት ሰርገው የገቡ ሚንስትሮች አሉ ሲል’ ለመጠቆምም ጠሚው እንዲያቀርበው ተናግሩኣል። መቸም የጠቀሳቸውን ሰዎች ብንገምት፣ አሀዱ ትምህርት ሚንስትሩ ብለን ክሌቱ ስንል የአብኑ በለጠ ሞላ ብለን ሰልስቱ ስንል’  ደግሞ የኦነጉ ሚንስቴር ? ? ያው እንደ አሜባ የተባዙ አስር አይነት ኦነግ ስላለ እንደማይስማሙ በማወቅ ነው።
 በግልፅ በአደባባይ በሚዲያ ፊት ቀርቦ 10 ሚሊየን የአዲስ አበባ ኗዋሪን የተሳደበን፣አገር ትፍረስ እያለ በውጭ ተቀምጦ ለብዙ ንፁሃን ኢትዮጵያዊያን ዕልቂት ተጠያቂ የሆነን ግለሰብ፣ አዲስ አበባ ከተማ በሚገኝ ም/ቤት የህዝብ እንደራሴ ተብሎ ተቀምጦ ማየት ህመም ነው።በዚህ ግለሰብ መነፀር ብቻ የቀጣይ አመታት የኢትዮጵያን ህዝብ ዕዳ አሻግሮ ማየት በቂ ነው።
ይህ ግለሰብ ተቀፍድዶ በህግ መጠየቅ ሲገባው “ትፍረስ” ባላት ኢትዮጵያ ዋና ከተማ፣”የሸሌ ልጆች” ብሎ በሰደብን የአዲስ አበባ ኗዋሪዎች መኖሪያ በሚገኝ ም/ቤት ተቀምጦ አይኑንን በጨው አጥቦ ዳግም ሲያቀረሽ  ማየት ስቃይ ነው።
አሁንም እንላለን መሰል ግለሰቦች ተቀፍድደው በህግ የሚጠየቁበት ስርዓት የሚመጣበት ጊዜ እሩቅ አይደለም።ነገር ግን  በጠቅላይ ሚኒስትሩ የሰርክ ውሸቶች ደንዝዘህ ከሆነ የዛሬው የፓርላማ ዉሎና ሹመት የቀጣይ አመታት ሳልስ ዕዳህን ቁልጭ አድርጎ ያሳይሀል።
  “ንጉሳችን”እያሉ የጠቅላይ ሚንስትሩን ጀርባ እያከኩ ሲያላግጡ ከዋሉበት ም/ቤት “የተለያዮ ሃሳቦች ተንሸራሽረው ፣ለሙግትና ክርክር ቀርበው በነፃነት ውይይት ተደርጎባቸው መፍትሄ አምጥተው አሁን ኢትዮጵያ ከገባችበት የህልውና አደጋ ትወጣለች ብሎ ማሰብ የመጨረሻ ጅልነት ነው።
ላለፉት ሰላሳ አመታት ትሀነግ /ህዎሓት)በኢትዮጵያ እና በአማራ ህዝብ ጥላቻ  ማንቁር እየፈለፈለ ባሳደጋቸው ግለሰቦች ወጭ ወራጅነት ኢትዮጵያ አሁን ከጠለቀችበት የመፍረስ አደጋ ትወጣለች ብሎ ማሰብ ሰው አለመሆንን ይጠይቃል።
ዛሬ የተሾሙትን 98 % የካቢኔ አባላት እና ሿሚያቸውን ስንመለከት ላለፉት 27 ዓመታት ለትህነግ/ህዎሓት ፍፁም ታማኝ አሽከር የነበሩ ናቸው።በተጨማሪም ላለፋት ሶስት አመታት በለውጥ ስም ኢትዮጵያ አሁን ለገባችበት ምጥ መሪ ለሆኑት ሿሚያቸውና  እና ድርጅታቸው ተረኛው ኦህዴድ/ኦዴፓ አቤት ወዴት የሚሉ ፍፁም ታማኝ ተላላኪዎች መሆናቸው እየተመለከትክ ኢትዮጵያ”ትበለፅጋለች” እያለ ሌት ተቀን የሚያቀረሽብህን ግለሰብ አምነህ የምታላዝን ከሆነ አንተ ፍፁም ከንቱ ነህ።
ሌላው ትልቁ ህመም ደግሞ “ለኢትዮጵያ መፍረስ ዋነኛው ሰነድ ሕገ መንግስቱ ነው፤ ለአማራው፣ለጉራጌው ፣ለኦሮሞው ፣ለትግሬው  እና ለሌሎችም ንፁሃን መታረድ ምክንያቱ ይሄው ሰነድ ነው። ስለዚህ በዚህ ህግ እንኳንስ ልንመራ ልናየው አንፈልግም።” ሲሉ የነበሩ የተቃዋሚ   የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች በዚህ ሕገ መንግስት አቅራቢነት ሹመት ሲቀበሉ ሲታይ ካልደነገጥክ ችግር ስላለብህ ታከም።
በኢትዮጵያ ህዝብ ስም እየማሉ “የዜግነት ፖለቲካ እናራምዳለን፤ኢትዮጵያን ከገባችበት የዘር ፖለቲካና መከፋፋል አውጥተን፣ በኢትዮጵያዊ አንድነት የሚያፀና ፖሊሲ ገንብተን፣አገራችንን አሁን ከወደቀባት የመጠፋፋት አደጋ እናወጣታለን።” ሲሉ የነበሩ ጡረተኛ ፖለቲከኞች በዘር እና በብሔር በተመሰረተ የመንግስት አወቃቀር ውሰጥ በፊት አውራሪነት ሲማገዱ ስታይ ቅሽሽ ካላለህ በቃ ዝም በል።
በኢትዮጵያ ሕገ መንግስ ፣በኢትዮጵያ ፖለቲካ ፣በኢትዮጵያ ምጣኔ ሀብት እና ማህበራዊ ሕይዎት በሴራ ተገልሎ፣ በሀሰተኛ የታሪክ ትርክቶች ምክንያት እየተሳደደ፣እየተፈናቀለ፣እየተገለለ እና እየተወገዘ የዘር ማጥፋት ሲፈፀምበት የነበረውን የአማራ ማህበረሰብ ቀጣይ ተጨማሪ ዕዳ የዛሬው የፓርላማ ውሎ ያመላከተ ነው።በተለይም በስሙ እየማሉ እየተገዘቱ እንወክልሃለን በሚል የፖለቲካ ፓርቲ አቋቁመው ሲታገሉ የነበሩ ግለሰቦች መዳረሻን ያሳወቀ እና የለየም ነበረ።
አማራው እና ኢትዮጵያ እንዲሁም አዲስ አበቤ ላለፋት 30 ዓመታት የገጠማቸውን ዕልቆ ቢስ መከራ በውል የሚረዱት አካለትን ጨምሮ ሌሎችም “የገጠመን የህልውና አደጋ ም/ቤት ውስጥ ሁለት ሆኖ በመቀመጥ ወይም በዘር በተደራጀ የመንግስት መዋቅር ውስጥ የቢሮ ሃላፊ ሆኖ በመቀመጥ የሚፈታ ነው።” ብለው ትናጋቸውን ሲያላቅቁ መመልከት ዕርግማን ነው ያስብላል።
በተለይም በየዋህነት አልያም በቅንነት ወይም ደግሞ ባላዋቂነት አሁን ላይ በኢትዮጵያ “አዲስ መንግስት”ተመሰረት ሲሏችሁ አሜን ብላችሁ ቀጣይ መጭ ጊዚያትን ተስፋ የምታደርጉ  አካላት እርማችሁን አውጡ።  “አዲስ መንግስት” ሳይሆን የመጣው የትህነግ ሃሳብ በኢትዮጵያ መለያ ተጠቅልሎ “አዲስ፣የሣልስ ምዕራፍ ዕዳ ነው።
በውጭ አገራት የሚኖሩ የኢትዮጵያን ሰላም በራሳቸው ምቾትና ጥቅም፣በራሳቸው ሆድ መሙላትና መጉደል እየለኩ “ንጉስ ሆይ አበጀህ፣!ደግ!” አያሉ የኢትዮጵያን ህዝብ መከራ የሚያበዙ የዲያስፖራ አባላት በዕጅጉ የሚያፍሩበት ቀን ሩቅ አይሆንም።እስከዚያው ድረስ ግን ቢያንስ ዝም በማለት ያነገሳችሁትን የኢትዮጵያ ሳልስ ዕዳ ተመልከቱ።ከቻላችሁ በድርጊታችሁ ተፀፅታችሁ ይቅርታ በመጠየቅ ሰው ሁኑ።
የተጀመረው ሁሉን አቀፍ ሰላማዊ ትግል ከምንጊዜው በላይ በተቀናጀ እና በተናበበ መልኩ ተጠናክሮ የሚቀጥልበት ትክክለኛ ምዕራፍ  አሁን ነው።
በኢትዮጵያ ስለ ዕውነተኛ ዴሞክራሲ ግንባታ ሲሉ ለዓመታት ዋጋ የከፈሉ ዛሬም በዕስር ቤት ያሉ ትክክለኛ መሪዎችህን ለይተህ በማገዝ  ትግሉን ተቀላቀል።ቁልፉ ያለው በዕጅህ ነው።
*  ወይ አዲስ አበባ ወይ አራዳ ሆይ! 
የሹሼ ልጅ ብሎ የሰደበሽን ሶዬ ፓርላማ ሲታይ
ድልና ሰላም ለኢትዮጵያ!!
ድል ለጭቁኖች!!
መስከረም 2014
ወግደረስ ጤናው
Filed in: Amharic