በየደረጃው ያሉ የመንግስት ኃላፊዎች የሚወስዷቸው እርምጃዎች በሕግ አግባብ ሊፈተሹ ይገባል!
መስከረም 27 ቀን 2014 ዓ.ም
መግቢያ
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ(ኢሰመጉ) በሲቪል ማህበራት አዋጅ ቁጥር 1113/2011 በዳግም ምዘገባ ቁጥር 1146 ተመዝግቦ፣ ከማንኛውም የፖለቲካ ቡደን፣ ከሃይማኖት፣ ከብሔርና ከጎሳ ተፅዕኖ ነፃ ሆኖ የተቋቋመ፣ በገለልተኝነት እና በህጋዊነት በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኝ አገር በቀል የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች ድርጅት ሲሆን ላለፉት ሶስት አስርት
ዓመታት በአገራችን የተለያዩ አካባቢዎች የሚፈፀሙ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰትን እያጣራ የመፍትሔ ኃሳቦችን ያካተተ
መግለጫ በማውጣት ለሚመለከታቸው አካላት ይፋ ሲያደርግ ቆይቷል፤ አሁንም ይህንኑ በማድረግ ላይ ይገኛል:፡
እንዳሉ ሲረዳ ችግሮች ተከስተው ሰብዓዊ እና ቁሳዊ ጥፋት ከማስከተላቸው በፊት አስቸኳይ መፍትሔ እንዲሰጣቸው
ለሚመለከታቸው አካላት ሁሉ የማሳወቅ እና ስለተወሰዱ እርምጃዎች ክትትል የማድረግ ሥራ ይሰራል፡፡
በዚህ መንፈስ ኢሰመጉ በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልል በጋሞ ጎፋ ዞን ቁጫ ወረዳ ስላለው የሰብዓዊ
መብቶች ሁኔታ ክትትል ሲያደርግ ቆይቷል፤ አሁንም በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ በሚያደርጋቸው ክትትሎችም ከመስከረም 1/2014 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት ተከታታይ ቀናት በቁጫ ወረዳ፣ በቁጫ አልፋ ወረዳ እና በሰላም በር ከተማ አስተዳደር ስር በሚገኙ የተለያዩ ቀበሌዎች እና አካባቢዎች ላይ (ማለትም በደሌ-ከይሴ ቀበሌ፣ ጫሌአ ቀበሌ፣ ጋሌ ቀበሌ፣ ዳሆ ቀበሌ፣ ቦላ ቀበሌ፣ በቁጫ ደሌ ወይዛ ቀበሌ እና በቁጫ ጫባ በለስ ከተማ ለአብነት የተጠቀሱ) እንዲሁም በጋሞ ዞን በተለያዩ ወረዳዎች ሰዎች ያለ በቂ ሕጋዊ ምክንያት በፀጥታ አካላት ለእስር እየተዳረጉ ስለመሆኑ፣ ድብደባ እንደሚፈፀምባቸው፣ በሕግ በተመላከተው መሰረት ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ ለረጅም ጊዜ እንደሚታሰሩ እንዲሁም የመንግስት ሰራተኞች በሕግ ከተቀመጠው ሥርዓት ውጪ ከስራ እንደሚሰናበቱ፣ ሕገ-ወጥ የሥራ መደብ ዝውውሮች
እንደሚፈፀሙ፣ ሰራተኞች ደሞዝ ያለአግባብ መያዝ እና ከህግ ውጪ በሆነ መልኩ ከስራ መደብ ዝቅ ማድረግን
የመሳሰሉ ተግባራት እየተፈፀሙ እንደሆነ የሚያመላክቱ መረጃዎች ለኢሰመጉ ደርሰውታል…