ደጀኔ አሰፋ
ጉቴሬዝ – አፈረ!!!!!!
አሜሪካ እንግሊዝ አየርላንድ ለ 9ኛ ጊዜ ተሸማቀቁ!!!!!
ጉቴርዝ የአሜሪካ ተላላኪ ሆኗል:: አሜሪካ አልሳካላት ያለውን ኢትዮጵያን የማንበርከክ እቅድ ለማስፈጸም ባለፈው ሴረኛው ፌልትማን ጉቴሬዝን ሄዶ ካገኘው በኃላ ይሄው በግልፅ የአሜሪካ ትሮጃን ሆርስ መሆኑን አረጋገጠ:: አበስኩ ገበርኩ!!!!!
– አሜሪካ ምን ስለፈለገች ነው ይህን ሁሉ የምትዳክረው
1ኛ) በድርድር ላይ የተመሰረተ ተኩስ አቁም –
ትርጉሙም አሸባሪው ጁንታ በህግ እንዳይጠየቅ ብቻ ሳይሆን ተመልሶ መንግስትነት እንዲቀዳጅ
2ኛ) ያልተገደበ የሰብዓዊ እርዳታ ወደ ትግራይ ይድረስ –
ትርጉሙ አሜሪካ እና እንግሊዝ ከዚህ በፊት ለጁንታው እንዳደረጉት አይነት ወታደራዊ እና መረጃ ድጋፍ ዛሬም ፍተሻ ሳይደረግ እንዲገባ ክፍት ፈቃድ ይሰጥ
3ኛ) በትግራይ የጾታዊ ጥቃት ጅምላ ጭፍጨፋ …ወዘተ እየተፈፀመ ነው…..
ትርጉሙ አብይ እህመድን በጦር ወንጀል እንከስሃለን በሚል ማስደንገጥ እና እጅ መጠምዘዝ…
4ኛ) መሰረታዊ አገልግሎቶች (ቴሌ ባንክ ኤሌክትሪክ.. በጀትም ጭምር….) ለትግራይ እንዲለቀቅ –
ትርጉሙም ጁንታው ኢትዮጵያን እንዲያፈርስ የኢትዮጵያን ሃብት እና ንብረት ይጠቀም ማለት ነው::
——
•• በዚህ ሰአት ጦርነቱ ያለው በአማራ ክልል ላይ ቢሆንም ትግራይ ብቻ የእኛን ትኩረት ማግኘት አለባት በሚል (all are equal, but some …. George Orwale) እንዲል ሃያልነታቸውን ማሳየት:: እፍረት አልባዎች!!!!
— የዚህ ሁሉ ንትርክ ግብ ምንድን ነው???
1ኛ) ኢትዮጵያን በማስጨነቅ የኢትዮጵያን መንግስት የአሜሪካ ባሪያ እና ተላላኪ ማድረግ
2ኛ) የኢትዮጵያ መንግስት የአሜሪካ ባሪያ እና ተላላኪ ማድረግ ካልተቻለ ኢትዮጵያን ማፍረስ
3ኛ) የኢትዮጵያ መንግስት የአሜሪካ ባሪያ እና ተላላኪ ማድረግ ካልተቻለ ወይም ገፋ ብሎ ኢትዮጵያን ማፍረስ ካልተቻለ …ራሽያ እና ቻይና በኢትዮጵያ እና በቀጠናው (በተለይ በቀይ ባህር) ላይ የሚኖራቸውን ተፅዕኖ ማኮሰስ:: || ይህን ግብ በሚገባ ለመረዳት የኢትዮጵያ ጠላት የሆነው እና በአፍሪቃ የሲአይኤ ሃላፊ የነበረው ጁድ ዴቨሞንት – የአሜሪካ እና የአፍሪካ ግንኙነት ስልት አዘጋጅ ሆኖ በባይደን አስተዳደር አሁን ዳግም መመረጡ ሁነኛ ማሳያ ነው:: ፎሬይን ፖሊሲ ዛሬ ይዞት የወጣውን እዩት:: https://foreignpolicy.com/ 2021/10/05/biden-africa- strategy-national-security- council-counterterrorism- china-democracy-agenda/ )
4ኛ) የኢትዮጵያ መንግስት የአሜሪካ ባሪያ እና ተላላኪ ማድረግ ካልተቻለ ወይም ገፋ ብሎ ኢትዮጵያን ማፍረስ ካልተቻለ ደግሞ ቢያንስ አንዲት ድሃ አገር ምዕራባዊያንን በተለይ ሃያሏን አሜሪካንን እምቢ በማለቷ ካልቀጣናት ሌሎች የምስራቅ አፍሪቃ ሃገራትና አፍሪካ ከኢትዮጵያ ስለሚማሩ ኢትዮጵያን በማእቀብ : በክልከላ ከዚያም በቀዝቃዛ ጦርነት ስልት ኢትዮጵያን ከዓለም የተገለለች ማድረግ… የአፍሪቃ ምሳሌ እንዳትሆን ስሟን ማጠልሸት : የአፍሪቃ መሪዎችና AU ከኢትዮጵያ ጎን እንዳይቆሙ ማስፈራራት (bullying)… በኢኮኖሚ ማዳከም … የምስራቅ አፍሪቃ ሃገራት ትስስርን መበጣጠስ… አብይን ከኤርትራ እና ከሶማሊያ መሪዎች ማራቅ… የኢትዮጵያን ውጤቶች እና በጎ ጅምሮች እንዳላዩ መተው (overlook ማድረግ) …. የሚዲያ ትኩረት መንፈግ ….ወዘተ የሚሉ ናቸው::
ይሄን ስናውቀው ኖረን…. ኖረን…. ኖረን…. ዛሬ
ጉቴሬዝም እውነተኛ ማንነቱን ዛሬ በድጋሚ አሳየ:: ይህን ስንጠብቀው ነበር:: ምንም አዲስ ኩነት አይደለም:: በጁንታው ስለተያዙት የእርዳታ ማመላለሻ መኪኖች ከማውራት ይልቅ በአፋር ክልል የትግራይ እርዳታ እየተጎተተ ነው ሲል በአሜሪካ እና እንግሊዝ ከሚደገፉት እንዲሁም በአይርላንድ ከሚመከሩት የጁንታው አክቲቪስቶች እና ሎቢስቶች የተቀበለውን ወሬ ቁምነገር አድርጎ ለማቅረብ ተገደደ:: ጉቴሬዝ:: አይኑን በፎስፎረስ ያጠበ ይመስላል:: ጨው በስንት ጠዓሙ::
ዶክተር አብይ UNንን ሁለት ጊዜ ምላሽ በመጠየቁ አሜሪካ መናደዷን በጉቴሬዝ እንግሊዝኛ ውስጥ ማየት ቀላል ነው:: በዚያ ላይ እንኳን ደስ ያለህ ያላለውን በህዝብ የተመረጠ መንግስት… ጭራሽ ዶክተር አብይ ከተናገረው ውስጥ አንዷን ቃል መዞ ስለ ብሄራዊ ድርድር ያወጋል:: Congratulations ያላልከውን ጠ/ሚኒስትር (I welcome PM’s speech… ) አይባልም!!!! ስለ ዲያሎግ ለማውራት ቅድሚያ እውቅና ይስጥ!!!! ካልሆነ ያሳፍራል!!! Shame on Antonio Gutteres!!!!!
ጉቴሬዝ ሰው ነበር:: ፌልትማንን ካገኘው ወዲህ ወደ ፈረስነት ተቀየረ:: ፈረስ ምስኪን የቤት እንሰሳ ነው:: ያደርሳል እንጅ አይዋጋም:: ፈረስ እንደ ሰው ሆኖ የተባለውን ቢያወጋ ኢትዮጵያውያንን ሊያስፈራ ከቶ አልቻለም!!!! እንደ አባት ሃገር ራሽያ አይነት እውነተኛ ወዳጆቿም ብርቱ ጋሻ ናቸው!!!! ..የትግራይ ጉዳይ የኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ መሆኑን ዛሬም ዳግም አረጋግጣለች!!!! ኢትዮጵያውያን አዲስ መንግስት ስለመሰረታችሁ Congratulations ብላለች!!!! ኢትዮጵያ የውስጧን ጉዳይ ለምፍታት አቅም አላት:: ያንን አቅም በምልአት አልተጠቀመችም!!!! ተመድ ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር ተቀርርቦ ይስራ:: ራሽያ የኢትዮጵያን የግዛት እና የህዝቧን አንድነት ሉአላዊነት እና የፖለቲካ ነፃነት ዛሬም ትደግፋለች…. ወዘተ በሚሉ መስረታዊ መርሆች የአሜሪካንን የእንግሊዝን የአየርላንድን እና የተላላኪዎችን ሴራ በታትናዋለች!!!!! ራሽያን እውዳለሁ!!!! የራሽያን አምባሳደር እወዳታለሁ!!! Russian Embassy in Ethiopia – Посольство России в Эфиопии Russian Foreign Ministry –
የራሽያ ወዳጅነት እንደተጠበቀ ሆኖ … ለፈረሱም ለጋላቢውም ለላኪውም ግን ኢትዮጵያ መልስ አላት!!!! ምላሿም የእውነት እና የእውቀት ልምጭ ነው!!!!! በትህትና ቃል ትገርፋለች!!!!! ወደ ውስጥ ዘልቆ ይገባል!!!! ላኪውም አርጩማው ያሸንፈዋል!! ፈረሱም ልምጩን መቋቋም ያቅተዋል!!!! እንደ ሜክሲኮ እና ቬትናም ያሉ ከጉዳዩ የራቁ እና የአሜሪካ ተፅዕኖ ያረፈባቸውም ግራ ይገባቸዋል!!! እንደ ኬንያ ያለ (ሌባ መንግሥት እየተባለ ቅርቃር ውስጥ የገባ) ወርሃዊ የ UNSC መሪ የተደረገ ደግሞ) እንቦጭ ስለሆነ በላኪዎቹ ላይ የሚሰነዘረውን ልምጭ ማስቆም ባይችል ፈረሱ እፎይታ እንዲያገኝ እድል ይሰጣል:: ላኪዎቹ አየር እንዲያገኙ ፋታ ይፈልጋል:: ስብሰባውም ይበተናል::
ይሄው ነው!!!!
ዛሬ የሆነውም ይሄው ነው!!!!!
ጀግናው ልጃችን ታዬ አፅቀስላሴ በለስላሳ አንደበት በሃቅ ልምጭ በኢትዮጵያዊ ጨዋነት የተላላኪዎችን ስብሰባ በትኖታል!!!!! የራሽያን ውለታ በቃላት መግለፅ አይቻልም!!!! የኢትዮጵያ ህዝብ እና የኢትዮጵያ አምላክ ደግሞ የኢትዮጵያን መሻገር የኢትዮጵያን ማሸነፍ እና የኢትዮጵያን ከፍታ ያረጋግጡታል!!!!!! የወጉንም ያስወጉንም በአይናቸው ያዩታል!!!!! አይቀርም!!!!!
አባት ሃገር ራሽያ ምስጋናችን ብዙ ነው!!!!!!
ጀግናው ልጃችን አምባሳደር ታዬ ዘመንህ ይለምልም!!!!!
ኢትዮጵያ የሃያላኑ መፋረጃ!!!!! የክፋዎች መቅጫ!!!!!!