>

የሊቀሰይጣኑ ኦርቶዶክስን አፍራሽነት (ወንድወሰን ተክሉ)

የሊቀሰይጣኑ ኦርቶዶክስን አፍራሽነት

ወንድወሰን ተክሉ

*… የሊቀሰይጣኑን ዳንኤል ክብረት ጸረ ኦርቶዶክሳዊ ስራ በገሀድ ሲገለጥ-ዳንኤል መንበረ ፓትሪያርኩን ለሁለት እየከፈለ ነው!
*….. የኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በርስጣዊ ይሁዳው ዳንኤል ክብረት ከመንፈሳዊ አገልግሎት ወደ የካድሬ አገልጋይነት እይተቀየረች ነው።
፠ የኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ፓትሪያርክ ብጹእ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ በሌሉበትና ቅድሱነታቸውን አቡነ መርቆሪዎስን ብቻ ነጥሎና ለይቶ ወደ አቢይ አህመድ ጽ/ቤት በመውሰድ እራሱን አቀናብሮ የደረሰውን የውዳሴ ስብከት በእነዚህ አዛውንቶች አንደበት እንዲቀርብ ሲደረግ ቅዱስ ሲኖዶሱን ለሁለት ለመክፈልና እርሰበርስ እማይተማመን መንፈስ ለመፍጠር ነው ብሎ የማያስብ ኦርቶዶክሳዊ አማኝ ካለ የቤተክርስቲያኒቱን ህገ ደንብና ቀኖናን ፈጽሞ እማያውቅ ባይተዋር መሆን አለበት።
፠ በቅዱስ መርቆሪዮስ የሚመራ ክሊክ መፍጠርና ይህንንም ክሊክ በመንግስት በኩል ተቀባይነት ያለው ማድረግ ዋና ዓላማ በአባቶች መካከል መከፋፈልን ለመፍጠር ባለመ መልኩ መሆኑን እማይረዳ አማኝ ይኖራል ብሎ አይጠበቅም።
፠ አጠቃላይ ቤተክርስቲያኒቷን የፋሺስቱ አቢይ መንግስት አወዳሽ እና አገልጋይ በማድረጉ ሚና ግንባራ ቀደም ፊት አውራሪ ሆኖ ለሚሰራው ሊቀሰይጣኑ ዳንኤል ክብረት እጅ ስር እንዲሆን ማድረግ የቤተክርስቲያኒቱን መንፈሳዊ ገጽታ አምክኖና አክስሞ የፖለቲካ ማስፈጸሚያ የካድሬ ማእከል ማድረግ ማለት ጽሆናል።
ሊቀ ሰይጣኑ ዳንኤል ክብረት  እስከዛሬ ከፈጸማቸው ጥፋቶችና ወንጀሎች ይበልጥ አሁን ዛሬ እየፈጸማቸው ያሉት ተግባራቶች አጠቃላይ የኦርቶዶክስን አንድነታዊ ህልውናን  ያናጋና የሰነጠቀም ተግባር በመሆኑ ህዝበ ምእመን ቤተክርስቲያኑ በካድሬ ሴራ ስትፈራርስ በዝምታ ማየት አይገባውም።
Filed in: Amharic